Breaking News
Home / Amharic / ጀነራል አሳምነው ፅጌ ቀድሞ የተረዳዉና ያስጠነቀቀዉ የኦሮሞ ወረራና መስፋፋት ጉዳይ!

ጀነራል አሳምነው ፅጌ ቀድሞ የተረዳዉና ያስጠነቀቀዉ የኦሮሞ ወረራና መስፋፋት ጉዳይ!

ጀነራል አሳምነው ፅጌ ቀድሞ የተረዳዉና ያስጠነቀቀዉን ጉዳይ አሁንም ያልገባዉና ያልተረዳ አማራ ካለ፣ ለአቅመ መረዳት የማይበቃ አይምዕሮ ያለዉ መሆን አለበት፣ አሁን ሁሉም ግልፅ ነዉ። ኢትዮ 360 ሚዲያ ላይ አንዳንዴ ሐብታሙ አያሌው የ16ኛው ክ/ዘመን አደጋ በድጋሚ በኢትዮጵያ ላይ አንዣቧል የሚለውን ህዝቡ ይሄን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አሁን እየሆኑ ካሉት ሁኔታዎች ጋር አገናዝቦ በንቃት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በንቃት መረዳት ብቻም በቂ አይደለም ድርጊቱን ማስቆም አለበት።

በ16ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ምን ሆነ የሚለዉን ብዙ የታሪክ መጽሐፍትና ታሪክ አዋቂዎች ስላሉ ያንን እንድታዩ እመክራለሁ፡፡ በ16ኛዉ ክ/ዘመን ኢትዮጵያ በእርግጥ ፈርሳ ነበር። በ16ኛዉ ክ/ዘመን የግራኝ አህመድን ወረራ ተከትሎ የተስፋፋዉ የኦሮሞ ተስፋፊ ብዙ ነባር ነገዶችን ዉጦ በማጥፋት ኢትዮጵያን አፈራርሶ ለዘመነ መሳፍንት ዳርጓታል። እስከ 19ኛው ክ/ዘመን ፅንታዊቷ ኢትዮጵያ አንድ አልነበረችም። አንድ የተጠናከረ ዘዉዳዊም ሆነ ሌላ መንግስት አልነበራትም። የአካባቢያዊ ገዥዎች የነገሱበትና የተስፋፉባት እርስ በእርስ የሚዋጉባት ሀገር ነበረች። የመሳፍንት ዘመን የሚባለዉም የጦር አበጋዝ መሳፍንቶች የገነኑባት፣ ሴንትራላዊና ማዕከላዊ መንግስት የማይቆጣጠራቸዉ ማዕከላዊ መንግስት የፈረሰባት ሀገር ነበረች።
ሀገሪቱም ስለፈረሰች፣ ማዕከላዊ መንግስቷም ስለተዳከመ በተበታተነ ሁኔታ ዘመነ መሳፍንት በተባለ ተበታትና ስትተዳደር ቆይታ ድንገት በተነሱት አጼ ቴዎድሮስ በጀመሩት ኢትዮጵያን እንደገና አንድ የማድረግ ዘመቻ ግማሽ ያህሉን ኢትዮጵያ የመለሱትና አንድ ያደረጉ ንጉስ ናቸዉ። ለዚህም ከብዙዎች ጋር ተዋግተዋል፣ ይሄም ፍልሚያና ጦርነት ንጉሱን በጨካኝነት ስማቸዉ የሚጠራ ንጉስ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ያም ሁኖ ኢትዮጵያን በአንድ እግሯ እንድትቆም ያደረጓት ንጉሥ ሲሆኑ ከእሳቸው በሁዋላ ፈለጋቸዉን የተከተሉት አጼ ሚኒሊክ ናቸዉ። እሳቸዉ ደግሞ ሂደቱን በማስቀጠል ኢትዮጵያን ዳግም የመመለሱን ዘመቻ በጦርም በጥበብም አጠናክረዉ በመቀጠል አጠናቀቁትና ኢትዮጵያ በሁለት እግሮቿ ቆመች፡፡

አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን ዳር እስከዳር አንድ አደረጓት። አፄ ምኒልክ በኢትዮጵያ ታሪክ አይደፈሬነት የብዙዎች አርአያ የሆነዉን ለአድዋ ድልም አበቋት።
የዘመናችን የብሔር ብሔረስብ የተዛባ ትርክት የፈጠራቸዉ ጽንፈኛ ኦሮሞ ብሔርተኞች ታሪኩን በትክክል አያውቁትም። ስለዚህ ከሚነገራቸዉ የሃሰት ትርክት በመነሳት በምኒልክ ላይ በጎ አመለካከት የላቸዉም። በዚህም አለም ያወቀላቸዉንና የመሰከረላቸዉን የንጉሱን በጎ ምግባሮች ሁሉ ጥላሸት በመቀባት ሲባዝኑ የሃሰት የማይመጥኑ ቧልቶችን በመፈብረክ ተጠምደው ራሳቸዉን ትዝብት ላይ ጥለዉ ይገኛሉ። የሃሰት ትርክታቸዉ እንዳሸነፋቸዉ መቀበል አቅቷቸዉ የታሪክ ግንብ ከሆኑት ከምኒልክ ጋር እየተጋጩ የአይምሮ በሽተኞች በመሆን በመባዘን ላይ ይገኛሉ። እንዲሁም ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የተፈጠረችው በ19ኛው ክ/ዘመን ይመሰላቸዋል። አፄ ቴወድሮስና አፄ ምኒልክ የፈረሰችዋን ጥንታዊት ኢትዮጵያ መመለሳቸውን አይረዱም። አፄ ምኒልክ ወደደቡብ ሰራዊታቸዉን ሲልኩ አዲስ ሀገር ለማቅናት ትሄዳላችሁ ብለዉ አያዉቁም ሰራዊታቸዉን ሲልኩ የሚሉት “የአባቶቻችንን ሀገር ለማስከበር ነዉ ምትሄዱት” ነበር የሚሉት በዚህ መመሪያ ነዉ ሰራዊታቸዉ የሚልኩትና የሚያዘምቱት እንጅ አዲስ ግዛት ለማስፋፋት ብለዉ አልነበረም። ይህ አባባላቸዉ ከጦሩ ጋር አብረው ዘምተዉ ከነበሩት ሩሲያዊ አሌክሳንደር ብላቶቪች (With the armies of Menelik ii, From Entotto to the River Baro. ) መጽሐፍ የተገለፀ ነዉ። እነዚህ በተሳሳተ ትርክት የተሞሉ ብሔርተኞች ምኒልክ አዲስ ቅኝ ግዛት አድርገዉ እንደያዟቸዉ አድርገዉ በመቁጠር ኢትዮጵያን ሊያጠፏትና እንደገና ሊያፈርሷት ይፈልጋሉ፡፡ ራሳቸዉን በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያዩት በተሳሳተና በተዛባ ሁኔታ ነዉ።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜዎች ምስቅልቅሏ ወጥቶ ያዉቃል። በጣም የተመሰቃቀለችበትና አያሌ ቤተክርስቲያናት፣ አያሌ ቅርሶች የወደሙበት፣ ብዙ ሊቃውንት የተገደሉበት ስለ የኢትዮጵያ የመከራ ዘመን የዮዲት ጊዜዉ ብዙ ታሪክ የሚነግረንና የሚያስተምረን ነዉ። ከዚያ በሁዋላ ለሁለተኛ ጊዜ አያሌ ቤተክርስቲያናት የተቃጠሉበትና የወደሙበት አስቸጋሪዉና ከባዱ ዘመን የሚባለዉ የግራኝ አሀመድ በትክክለኛ ስሙ ( ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አልጋዚ 1507_1543) ነዉ።

ስለ ኢማም አህመድ ወረራና የግዛት ዘመን ብዙ ይወራል ብዙም ተጽፏል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን የለዋወጠዉና ያናወጠዉ የዲሞግራፊ ለዉጥ የፈጠረዉ ግን እሱን ተከትሎ የተስፋፋዉ የኦሮሞ ወረራ ወይም መስፋፋት ነዉ። የኦሮሞ መስፋፋት በጣም አዉዳሚ አካባቢን ሙሉ በሙሉ የሚያወድምና የሚለውጥ የሚያወድመዉን አዉድሞ የተረፈዉን ሴቶችንና ህፃናቱን በጉዱ ፌቻና በሞጋሳ ወርሶ ገርባ/ ገባር የሚያደርግ ማንነትን የሚቀይርና የሚያጠፋ ነበር። በዚህ ወረራ ወደ 22 የሚደርሱ የራሳቸው ማንነት የነበራቸው ኢትዮጵያዊ ነገዶች ጠፍተዋል ይህ አማራንም ይጨምራል የሸሸዉ በመትረፉ አልጠፋም እንጅ፣ አብረው ተዉጠዋል። የአሁኑ ኦሮሞ እነዚህን ሁሉ የዋጠና በውስጡ ኦሮሞ አድርጎ የያዘ ነዉ። ግን ስለዚህ ብዙ አይነገርም፣ ከዚህ ታሪክ ስንነሳ አሁን ኦሮሞ ነን በምንል ዉስጥ የተወረሰ ከሃያ በላይ ማንነት በውስጣችን እንዳለ መርሳት የለብንም።

በእዉነት ለመናገር ኢትዮጵያን ከግራኝ አህመድ ወረራ በኃላ እንድትበታተን ያደረጋት የኦሮሞው ወረራና መስፋፋት ያስከተለው የማንነት መቀየር፣ ጭፍለቃና መዋጥ አንዱ ነዉ። ይሄዉም ማንነት መቀየሩ በኃይልና በወረራ የሚካሄድ በመሆኑ በገዳ ሥራታቸዉ በዬ ስምንት አመቱ ሉባዉ ለመቀየር ስልጣን በሚቀያየሩበት ወቅት ለዚህ ዝውውር ደግሞ አዲስ አጓራባች ነገድን በመዉረር ግዛት ማስፋት አንዱ በመሆኑ አጓራባች ነገዶች ወዮላቸዉ፣ በዬ ስምንት አመቱ ወረራ ይካሄድባቸዋል። በወረራዉም የሚገሉትን ገለዉ ከሞትና ከሽሽት ተርፈው የያዙትን ህፃናቶችና ሴቶች ደግሞ ይወረሳሉ። በዚህ ወረራ ጊዜ የሚችል እየሸሸ ወደ ተራራና ለኑሮና ለእርሻ አመቺ ወዳልሆነ ቦታ ለመስፈር ይገደዳል፡፡ ይህን በአግባቡ ባለመናገራችን “ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል” እንዲሉ ይኸው አሁን ፅንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች በዚህ መልክ በወረራ ያያዙትን ሁሉ የራሳቸው ብቻ እንደሆነ በመቁጠር፣ ሌሎች ያሏቸውን መጤ ሲሉ ይሰማል። በዚህ መልክ ሲሳደድ፣ ሲጨፈለቅና ሲዋጥ፣ ሲገደል የነበረን ህዝብ ይሄን ሁሉ በደል ትተው እነሱ ተበዳይ እንደነበሩ ይቆጥራሉ። ይሄዉ አሁን ደግሞ በእነዚህ ኃይሎች ኢትዮጵያን ዳግም እንደ 16ኛው ክ/ዘመን ለመበታተን ቋፍ ላይ ደርሳለች። እነዚህ ራሳቸዉን እንደተበዳይና ተጨቋኝ በመቁጠር በሌላው ላይ በሰሩት የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ በፈጠረባቸዉ ጥላቻ መሰረት ሁሉም ለእኛ በሚል ስግብግብ መንፈስ ታንኩንም ባንኩንም በእጃችን አስገብተናል ብለዉ፣ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሰይጣናዊ ሂደቱን ጫፍ አድርሰውታል፡፡ ለዚህም የአብይ አህመድ የከንፈር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ትወና በእጅጉ ረድቷቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ልንረዳ የሚገባን ይህ የአብይ አህመድ ትወና ራሱ እንዳለዉ ” የሚፈልጉትን እያጫወትህ ወደ ምትፈልገዉ ዉሰዳቸዉ” ወይም ” አያ በሬ ሆይ እሳር እሳሩን እንጅ ገደሉን ሳታይ ” እንደሚለው ነዉ።

ከወያኔ ህወሓት ጋር የተካሄደው ጦርነትና የጦርነቱ ሂደትና በአጠቃላይ አሁን እየሄደ ያለበትን ሁኔታ፣ በጦርነቱ አፋርና አማራ ባልታሰበ በወያኔ ህወሓት የወረራ ጦርነት መዉደምና መደቆስ፣ በደንብ ታስቦበት የተፈፀመ እንጅ በድንገት የተከሰተ አይደለም። ድንገተኛ የሚሆነው ለአፋርና ለአማራ ብቻ ነዉ። አፋርና አማራ አቅማቸው ከተዳከመ በሁዋላ፣ ጦርነቱን አስቁሞ በጓዳ ከጦርነቱ ሰለባዎች ከአፋርና ከአማራ ዉጭ እየተካሄደ ያለዉ ድርድር፣ የሚያሳየን ብዙ ያልተነገሩና ያልተተገበሩ፣ ሊተገበሩ የታቀዱ ነገሮችን በግልፅ የሚያሳይ ነዉ። አፋርና አማራ በባህሪያቸዉና በስነልቦናቸዉ በኢትዮጵያ ላይ ቅሬታ ማያቀርቡ ኢትዮጵያዊነትን ወደዉ የተቀበሉ፣ የሚወዱ፣ ኢትዮጵያዊነቱን የሚወድ ህዝብ ያለባቸዉ ሀገሮች ናቸዉ። ይሄም ይመስላል በሁለቱ ኢትዮጵያ ጠል አካላት በጦርነት እንዲደቆሱ የተደረጉት። ምንም እንኳን አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ የኦሮሞ ተረኛ መንግስት በስልጣን ከወያኔ ህወሓት ጋር አለመግባባት ቢኖርም፣ በአላማ አንድ አይነት በእስትሬጂ አንድ ናቸዉ፣ ማለት የእስትራቴጅ አጋሮች ናቸዉ። ወያኔ ህወሓትና ኦነግ ያወጡትን ዜግነትን የነፈገና ያነሳ ህገ መንግስትም እኩል ይጋራሉ። ስለዚህ ለስልጣናቸዉ አስጊ በማይሆን ሁኔታ ወያኔ ህወሓት እንድትኖ እንጅ እንድትጠፋ አይፈልጉም። ወያኔ ህወሓት እንዳትሞት ይፈልጋሉ። የህወሓትን ጨርሶ መጥፋት በፍፁም አይፈልጉም ጦርነቱንም ያስቆሙበት ዋና ምክንያት ህወሓት እንዳትጠፋ ስለሚፈልጉ ነዉ። ምክንያቱም ህወሓት ለአማራ ባለዉ ጥላቻ አማራውን በወያኔ ህወሓት እያስፈራሩ ወጥሮ ለመያዝ ይጠቅመናል ብለዉ ያስባሉ። እንዲሁም በዚህ መልክ ብቻ ነዉ ኦሮሞያን የመመስረቱ ሂደትና አማራን የማጥፋቱ ሂደት የሚሳካዉ ብለዉ ያምናሉ፡፡ አሁን ከወያኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ነዉ። በድርድሩ የራያና የወልቃይት ጠገዴና ሰቲት ሁመራ ጉዳይ እንዳለበት ሁሉ የአዲስ አበባ ጉዳይም አለበት። ይሄ ታላቋ ኦሮምያና ታላቋ ትግራይን የመመስረቱን ፕሮጀክት እንዲያግዝ ተደርጎ እየተቀመረ ያለ ድርድር ነው እየተካሄደ ያለዉ።
ለትግሬዎች መገንጠልን እንዲያው ለአፋቸዉ ይሉታል እንጅ ከልብ በቁጥር አንድ አጀንዳቸዉ የያዙትና የሚፈልጉት ሳይሆን በታሳቢነት በሪዘርብ የያዙት ነዉ። እስከቻሉና እነሱ የመምራት እድል ካገኙ በኢትዮጵያ ዉስጥ መኖርን ይመርጣሉ፣ ያለፈው የ27 ዓመት የግዛት ዘመናቸዉም ያሳየን ይሄን ነዉ። ለዚህ ምክንያቱ ከተገነጠሉ እንደ ልባቸው በመላዉ ሀገሪቱ በገነቧቸዉ ካምፓኒዎች አማካይነት መዝረፍ አያስችላቸዉም። ከተገነጠሉ ደግሞ ከአማራም ከኤርትራም፣ ከአፋርም አይናቸዉ ያረፈበትን እንደ ሀገር ለመኖር ያስችለናል የሚሉትን መሬት አስፋፍተዉ ይዘዉ መሆን እንዳለበት ያምናሉ። አጋዚያን የሚል የሀገር ምኞትም አላቸዉ ግማሽ ኤርትራን ያካለለ። ነገር ግን አሁን ባለዉ ሁኔታ የግድ የኦሮሞዎቹን ፍላጎት ለጊዜውም ቢሆን ማሟላት እንደስልት ወሰደን እንጠቀምበት የሚል ጨዋታ አላቸዉ ይመስላል። በዚህ ጨዋታ አብይ አህመድ ወልቃይትንና ራያን ለእኛ ለትግሬዋች ከተሰጠን በአስተማማኝ በማይታረቅ ደረጃ ከአማራ ጋር እንዲጣላ ያደርገዋል። ይሄም ከአብይ የተጣላዉን አማራ በሰላም አብረን እንኑር ብለን በማባበልና በማሳመን የአብይ አህመድን የኦሮሙማ መንግስት የጋራ ጠላት በማድረግ ከአማራው ጋር ሁነን አራት ኪሎ ለመግባት አያቅተንም የሚል እቅድ ሳያስቡ አይቀርም። በቅድሚያ ግን አማራዉን ከኤርትራ ጋር ያለዉን ግንኙነት መዝጋት መቻል አለብን ብለዉ ያምናሉ። በዚህ ሁለቱም አንድ አይነት እምነት አላቸዉ፣ አማራና ኤርትራ በድንበር እንዳይገናኙ በማድረጉ ሂደት ያምኑበታል። ለዚህም ነው አብይ አህመድ ኦሮሙማ ወልቃይትን ለህወሓት ትግሬ የሚሰጠዉ፡፡ ህወሓቶች ደግሞ ይህ አማራዉን ለወደፊት በአብይ አህመድ ኦሮሙማ ላይ በምንከፍተዉ ዘመቻ ያለ አማራጭ ከእኛ ጋር እንዲያብር ማድረግ ያስችላል ብለዉ ያምናሉ። ይሄን ማድረግ የምንችለው ዘግተን አማራዉን አማራጭ ስናሳጣዉ ብቻ ነዉ የሚል የጠና እምነት አላቸዉ። ኦሮሙማዉ አብይ አህመድ ደግሞ ወያኔም ተመልሳ አራት ኪሎ ለመግባት ግፊት ካደረገችና ካስቸገረች፣ ትግራይን በመግፋትና በማስገደድ እንዲገነጠሉ አደርጋለሁ ወልቃይትና ራያን በእጇ ካስገባች ለመገንጠል አታቅማማም የሚል ግምት አለዉ። እንዲሁም የራሱን የኦሮሙማ መንግስት በሚመሰርትበት ጊዜ ኤርትራ አማራን እንዳትረዳ ስለሚፈልግ አማራን ከኤርትራ እንዳይገናኝ ማድረጉን ያምንበታል፡፡

ወያኔ ህወሓቶች መገንጠሉን ትተው ገፍተዉ ከመጡበት የአብይ አህመድ ኦሮሙማ ችግሩን ለመቋቋም የግብፅንና የአሜሪካን እርዳታ ለማግኘት ማጎብደድ ይሞክ ይሆናል፣ በዚህም ችግሬን እታደጋለሁ ብሎ ሊያሰብ ይችል ይሆናል። ሆኖም አሁን እንደ መንግስት ወዳጅነቱ ከቱርክ ጋር ነዉ፣ ቱርክና ግብፅ ደግሞ ወዳጅ ሀገሮች አይደሉም። ነገር ግን ቀላል የማይባሉ የግብፅ ሊንክ ያላቸዉ የኦሮሞ ኦሮሙማ ፓለቲከኞችና ሙስሊሞች አሉ። የግብጽ ዋና ፍላጎት ደግሞ የአባይ የህዳሴ ግድቡ ጉዳይ ነዉ። ግድቡ በአማራ እጅ እንዲሆን አይፈልጉም፣ እንዲሁም አማራ ሌላ ግድብ የመገንባት አቅም እንዲኖረው አትፈልጉም። ግብፅ ግድቡን ለኦሮሚያ ለመስጠት ነዉ የምትፈልገዉ። አማራ የራሱን መንግስት ቢመሰርት እንኳን የአማራ መንግስት የሚሆነዉ መተከልን፣ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራንና ራያን ያጠቃለለ አይሆንም፣ ከነዚህ ዉጭ ነዉ፣ ሌላ ያገዉ የክልልነት ጥያቄም ሊያጋግሉት ይችላሉ። ስለዚህ አማራ ወደ ዉጭ መውጫ በር የሌለው በተዘጋ ቤት ዉስጥ ያለ ደካማ መንግስት ስለሚሆን በአባይ ላይም ሌላ በፕላን የታሰቡትን ግድቦች መገንባት አቅም የለዉም ይሄን ማድረግ በፍፁም አይችልም የሚለዉን ታሳቢ ያደረገ ነዉ።
ለግብፅ አሁን እየተገነባ ያለዉ የሕዳሴ ግድብ ብዙም የማይጎዳ ነዉ። ከተገነቡ ሌሎች ከአባይ ላይ ሊገነቡ የታሰቡት በእቅድ ላይ ያሉ የግድብ ፕላንና ፕሮጀክቶች አሉ። (ማንዳየ፣ በቂ አቦ፤ ካራዶቢ) የሚባሉ። እነዚህ ለመስኖ ሊያገለግሉ ስለሚችሉ ግብፅ እንዳይገነቡ ለማድረግ የምትችለዉን ሁሉ ታደርጋለች፡፡

እንግዲህ ከላይ ያልሁትን በደንብ ለተረዳ አሁን “በህግ ማስከበር” ስም ፋኖ እንዲጠፋ የተፈረደበት ምክንያት ግልፅ ነዉ። የሚገርመዉና የሚያሳዝነው ደግሞ በአማራ ስም ተሹመዉ የአማራን ጥቅም እናስጠብቃለን የሚሉ፣ የመንግስት ባለ ስልጣናት ለዚህ ህገወጥ ህግ ማስከበር ዋና ተባባሪዎች መሆናቸዉ ነዉ። የፌዴራል ኃይሎች ስለፈለጉ በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ ገብተዉ እንደፈለገ እንዲያደርጉ የሚፈቅድ ህግ የለም። በግድ እንዲገቡ ለማድረግ ደግሞ ሁኔታዎች የሚያስገድድባቸዉ ሁኔታዎች አሉ፣ አሁን በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለዉ ፋኖን የማጥፋት ኦፕሬሽን ከፌደራል የወረደና ትቂት የክልሉ መሪዎች የተቀበሉት ምንም ህጋዊ መሰረት የሌለው ነዉ። በክልሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የሰአት እላፊ የሚያሳዉጅ የተፈጠረ ምንም በቂ ምክንያት የለም። ጉዳዩም የህግ ቅደም ተከተሉን ተከትሎ የተካሄደ አይደለም። ይህ የክልሉ ህዝብ ጥያቄ፣ ፈቃድና ፍላጎትም አይደለም። ይህ በሃይል በአማራ ህዝብ ላይ በኦሮሙማ መንግስት አማራን ለማዳከም፣ የአማራን ሃይልና አቅም ለማሳጣት አላማ ያደረገ ህገወጥ ኦፕሬሽን ነዉ። ይህ ከህወሓት ጋር በጓዳ ከሚያደርጉት ድርድር ጋር የተያያዘ የጋራ ስምምነት ያለዉ ጉዳይ ነዉ። የአማራን ፋኖ ትጥቅ ማስፈታትና ማጥፋት ህወሓት ወያኔም የምትስማማበት ነዉ። በአማራ ይሄን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያደረጉ በሌላ በኩል ደግሞ እያካሄዱያት ያለዉ ዘመቻ፤ በአዲስ አበባ ብንመለከት የክፍለከተሞች ወረራ፣ የዲሞግራፊ ለዉጥ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ በየት/ቤቶች የኦሮሚያን ባንዲራ መስቀልና የክልሉ መዝሙር እንዲዘመር ተማሮችን ማስገደድ ይህ ሁሉ የታላቋን ኦረሚያ የመመስረቱ ፕሮጀክት አካል ነው፡፡ ይህ ግልፅ ያልሆነለትና ግራ ለተጋባ ህብረተሰብ ጉዳዩን በአግባቡ ካልተረዳና ካልገባዉ አደጋ ላይ ነዉ ያለዉ። ይህ ምን ቸገረኝ ተብሎ በግድየለሽነት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። የሁሉንም በር የሚያንኳኳ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነዉ። ህዝብ ጉዳዩንና አላማውን ከተረዳና አደጋዉ ከገባው ብቻ ነው እያንዳንዱን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እየተከታተለ እንደአመጣጡ ሊታገለዉና ሊገታዉ፣ ሊያስቆመዉ የሚችለው።
ለምን ይሄን እንደሚያደርጉ አላማቸውን ካልተገነዘብን የሚደርጉት ነገር ግራ ካጋባን፣ ድርጊቱም እንደቀላልና አላፊ አድርገን ከቆጠርን፣ እለታዊና ተራ ነገር አድርገን ዝም ካልን፣ በሁዋላ መቋቋም ከማንችለዉ ችግር ላይ እንወድቃለን።

በኃላ ሁሉን ነገር አጠናቀዉ አንዴ ኢትዮጵያን መናድ ከጀመሩ ናዳዉን ለመሸከምና ለመቋቋም አልተዘጋጀነምና ሰለባ ከመሆን አንድንም። በዉጭ ካለንም ኢትዮጵያ ስትበታተን እያየን ቁሞ ከመቆዘም ውጭ ምንም ማድረግ አይቻለንም፡፡
አሁን አብይ አህመድ! አብይ አህመድ የምትል የአይምዕሮህ ህዳጣ የሆንህ አማራ እሱ በድንቅ ትወናው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ አፍርሶ ታላቋን ኦሮሚያ መሰረተ ተብሎ ሃውልት ሲሰራለት እያየህ ከመብገን ዉጭ ሌላ ምን ማድረግ ትችላለህ። ማድረግ በነበረብህ ጊዜ ማድረግ ያለብን ማድረግ አልቻልህም፣ ህዝብን ክደሃል፣ በካህዲነትህም ለዚህ መከራ አብቅተኸዋል፡፡
አሁን አንድ አማራ አንድ ለኢትዮጵያ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ ምንም ምርጫ የለዉም፣ ፋኖ እንዳይጠፈ የሚችለውን ሁሉ ከማድረግ ዉጭ። አብይ አህመድና ህወሓት በሰላም ስም በጓዳ እያደረጉት ያለዉ ምስጢራዊ ድርድር ኢትዮጵያን የሚፈርሳት መሆኑን ለሕዝባችን ማሳወቅ ይገባል።

ሌላዉ ፋኖን ማገዝ በፍጥነት ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ጋር ሁሉ በመተባበር ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ እንዳደረግ። የአብይ ኦሮሙማን መንግስት በሁሉም ዘርፍ መታገል ይገባል። በፋኖ በሚችለዉ ሁሉ ኃይሉንና አመራሩን በማጠናከር ነጣ ወረዳዎችን እንዲፈጥር መታገል አለበት። በተለይም ቀለበት ዉስጥ ላለመግባት ከኤርትራ ጋር በመተባበር የወልቃይትን ከኤርትራ መገናኛ በነፃ ወረዳነት መቆጣጠር ይኖርበታል። አሁን ያለዉ አለም አቀፋዊ ሁኔታ ከነበረው የተሻለ ነዉ። አሜሪካ መራሹ አለም በአለም ላይ የፈለገውን የሚያደርግበት ጊዜ አይደለም። የሩሲያና የቻይና አሊያንስ ይበልጥ እየተቀራረበ ስለመጣ የአለማቀፋዊ ጅኦፖለቲኩን እየቀየረዉ ነዉ። በአለም ላይ ያሉ እስትራቴጅግ የጆግራፊ አቀማመጥ ያላቸዉ ሀገሮች ከድሮ የበለጠ የሃያላኑን ትኩረት ስበዋል ኤርትራ ከሩሲያ ጋር ያላት ግንኙነት መልካም ነዉ። ኢትዮጵያ የታወቀ የለየለት አቋምም የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲም፣ የፖለቲካ መርህም ያላት ሀገር ነች፣ “መደመር” የሚለዉ የአብይ ገተትም ከሽንትቤት መጥረጊ ወይም ከኪወስክ መጠቅለያ ወረቀትነት ያለፈ ጥቅም ሰጭ አይደለም። አማራው ደግሞ በምዕራቡ አለም ምንም ቢሆን እርዳታ የማያገኝ፣ ደመ መራራ ህዝብ ነዉ ጠፋም ለማ አሁን ባለዉ ሁኔታ እርዳታ የሚያገኘው ከኤርትራ ብቻ ነዉ።

Check Also

ሰሎሞን ካሳ ማነው? Who is Solomon Kassa?

አንከር ሚዲያ እንደዘገበው .. ለማታውቁት ሰለሞን ካሳ ይባላል ., ወንጀለኛው የሆነው ይህ ሰው የህዝብ ድምፅ …

የአድዋ በአል በለንደን ከተማ በደማቅ ተከበረ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.