Breaking News

TimeLine Layout

March, 2020

  • 13 March

    ዓባይ በካይሮ ከተማ እንዲህ ተንጣሎ ይታያል ! ፎቶዉን ተመልከቱና ፍረዱ።

    የኢትዮጵያና የግብፅ የቃላት ጦርነት በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ላይ 11 March 2020 ብሩክ አብዱ የግብፅ መንግሥት የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ግድቡ ወደ ግብፅ የሚፈሰውን የውኃ መጠን በመቀነስ፣ የታችኞቹ የተፋሰስ አገሮች ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ያሳድራል ስትል በተደጋጋሚ አቤቱታ ያሰማል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም የሚቀርቡበት ትችቶች በጥናት …

    Read More »
  • 12 March

    የድያስፖራ ባንክ ሊከፈት ነው

    አቶ ጋሻው የትዋለ ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ሲያገኙ፣ ኔዘርላንድስ ከሚገኘው ማስትሪች ስኩል ኦፍ ማኔጅመንት በፕሮጀክት አፕሬዛል፣ እንዲሁም ማኔጅመንት ዲፕሎማ፣ አውስትራሊያ ከሚገኘው የካንቤራ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ የታክስ አስተዳደር የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ በማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ በኮርፖሬት ቢዝነስ ስትራቴጂ፣ በፕሮጀክት ፕላኒንግና ማኔጅመንት በርካታ ሥልጠናዎች ተከታትለዋል፡፡ በኢንግሊዝ፣ በኔዘርላንድስና በቤልጂየም፣ እንዲሁም በአፍሪካ በኡጋንዳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በኬንያና በታንዛኒያ የተከታተሏቸው የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውን ይናገራሉ፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችንና የኮርፖሬት ቢዝነስ ስትራቴጂዎችን በዋናነት የንግድ፣ የታክስ፣ የፋይናንስ፣ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ የዳበረ ልምድ አላቸው፡፡ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ክልሎችን በመወከል፣ ከዓለም ባንክና ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የጥናትና የባለሙያዎች ቡድን ጋር በቅርበት በመሥራት፣ የአገሪቱን የታክስና የፋይናንስ ጉዳዮች ከአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት አንፃር በማጥናትና በመገምገም የፖሊሲ ሐሳቦችንና ስትራቴጂዎች ላይ የዳበረ ልምድ አላቸው፡፡ የኢትዮጵያን የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ፕሮጀክት በማዘጋጀትና ፕሮግራሙን በመምራት፣ እንዲሁም እንዲተገበር በማስተባበር ተሳትፈዋል፡፡ በአጠቃላይ ከ27 ዓመታት በላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችንና የኮርፖሬት ስትራቴጂዎችን ከማመንጨት ልምዳቸው በመነሳት፣ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ከሐሳብ ጀምሮ አሁን እስከሚገኝበት ደረጃ ድረስ በአደራጅነትና በመሥራችነት የሚሳተፉት አቶ ጋሻው፣ የሚመሠረተው የዳያስፖራ ባንክ ዓላማዎቹንና የወደፊት እንቅስቃሴዎቹን በተመለከተ ብርሃኑ ፈቃደ አነጋግሯቸው የሚከተለውን አጠናቅሯል፡፡ ሪፖርተር፡– የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ባንክ ማቋቋም ለምን አስፈለገ? አቶ ጋሻው፡– ከማክሮ ኢኮኖሚ የዕድገትና ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አንፃር ፈጣን፣ ዘላቂነትና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት በማምጣት የአገሪቱን የመካከለኛ ገቢ ራዕይ እ.ኤ.አ. በ2025 ዕውን ለማድረግ ሲታሰብ፣ በአንድ በኩል የአገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚ እየጨመረ መምጣቱ በሌላ በኩል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት መኖሩ፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክን ለማቋቋም እንደ ዋና ገፊ ምክንያት ተደርጎ ተወስዷል፡፡ በመንግሥት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያም የማክሮ ኢኮኖሚው ቁልፍ ችግር የውጭ ምንዛሪ እጥረት መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ አመልካቾችን በተመለከተ የፊስካል ፖሊሲውና የሞኒተሪ ፖሊሲው መስተጋብር የተጣጣመ አለመሆን ዋናው ቁልፍ ችግር ሲሆን፣ በዚህ ረገድ በተለይ የወለድ ምጣኔ፣ የዋጋ ግሽበት ምጣኔ፣ የቁጠባ ምጣኔ፣ የታክስ ምጣኔ፣ የኢንቨስትመንት ምጣኔ፣ የጉልበትና የገበያ ዋጋ ምጣኔና የጥቁር ገበያ ምጣኔ፣ የተጣጣመና የተመጣጣነ አለመሆን ነው፡፡ በአጠቃላይ የምርት ፍላጎትና አቅርቦት፣ የገንዘብ አቅርቦትና ፍላጎት፣ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና ፍላጎት የተጣጣመና የተመጣጣነ አለመሆን የማክሮ ኢኮኖሚው ቁልፍ ችግር ነው፡፡ በመሆኑም የአገሪቱን የኢኮኖሚ ምኅዳርና የውጭ ምንዛሪ ቋት ለማስፋት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ማቋቋም አስፈልጓል፡፡ በሌላ በኩል አንዱ ቁልፍ ችግር የድህነት ጉዳይ ሲሆን፣ በዚህ ረገድ ዝቅተኛ ገቢ ዝቅተኛ ቁጠባ፣ ዝቅተኛ ቁጠባ ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት፣ ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት ዝቅተኛ ገቢ የሆነውን የድህነት አዙሪት አከርካሪውን ለመስበር መሠረተ ሰፊ የሆኑ አዋጭ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ፋይናንስ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ክምችትን ለመጨመር፣ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንክ አክሲዮን ማኅበርን ለማቋቋም አስፈልጓል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የዓለም ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር፣ ከኢንዱስትሪ መር ወደ አገልግሎት ዘርፍ መር፣ አገልግሎት ዘርፍ መር ወደ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መር፣ ከቴክኖሎጂ ዘርፍ መር ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ መር በፍጥነት በመሸጋገር ሒደት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት አገሪቱ የጀመረችውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የለውጥ ጉዞ ወደፊት ማራመድ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ የብልፅግና ጉዞን ወደፊት ለማራምድና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አብዮት በማቀጣጠል ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሽግግር በፍጥነት ለማምጣት የትውልደ ኢትዮጵያውያውን ዳያስፖራዎች የልማት ተሳትፎ በባንኩ ምሥረታ ጉልህ ሚና የሚጫወት መሆኑ ከዓለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ ተለዋዋጭ የኢኮኖሚ ሁኔታ አንፃር፣ በተለይም ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በሒደት ላይ የምትገኝ ስለሆነ ሰጥቶ በመቀበል መርህ የማክሮ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ዘርፉን ደረጃ በደረጃ ለነፃ ገበያው በሯን ክፍት በማድረግ፣ ተጠቃሚነቷን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ባንኩን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ለባንክ ኢንዱስትሪያችን የቴክኖሎጂ ፍላጎት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዓለም የደረሰችበትን ከፍተኛ የባንክ ኢንዱስትሪ የቴክኖሎጂ ደረጃ በመተግበር የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ የባንክ ኢንዱስትሪውን የፈጠራና የሙያ ብቃት ጥራት ፍላጎት፣ የባንክ ኢንዱስትሪው ዓለም …

    Read More »
  • 12 March

    ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ (Neurologist in Amsterdam) የአስራት ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ!

    የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ መቋቋሙን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ባለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት አማራ-ጠል ኃይሎች የፈጠራ ትርክቶች ደርሰውና የአማራን ሕዝብ ድምጽ-አልባ አድርገው ለከፍተኛ ጉዳት ዳርገውት ኖረዋል። ይሁንና ሕዝባችን ድምጽ እንዲያገኝ አሥራት በተቆርቋሪ ልጆቹ ተመስርቶና በአማራ ሕዝብ ወዳጅ ኢትዮጵያውያን ተደግፎ ለፍትሕ፣ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ ድምጽ በመሆን ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ይህንን …

    Read More »
  • 12 March

    የአብን አመራሮች አሜሪካ ገቡ !

    አሥራት ዜና:- መጋቢት 2፣ 2012 ዓ.ም. የአብን አመራሮች ሊ/መንበሩ ረ/ፕሮፌሰር በለጠ ሞላና ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ ከሰዓት ዋሽንግተን ዲሲ የገቡ ሲሆን በዳላስ ኤርፖርትም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አመራሮቹ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ከነዋሪው ጋር በአማራ ጉዳይ ውይይት እንደሚያደርጉ ገልፀው ማንኛውም ሀሳብና ጥያቄ ያለው ሁሉ በየ ስብሰባ ቦታዎች በመገኘት ሐሳቡን እንዲያካፍል፣ ጥያቄዎችን እንዲያቀርብና አብንን …

    Read More »
  • 11 March

    የአዲስ አበባ ጉዳይ በጣም ያስፈራል። አንብቡና ለዘመዳችሁ ንገሩ !

    ሰላም ባይኖርም ሰላም ልበላችሁ ውድ አንባቢያን ነገሩ የተፈጸመው ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012ዓ.ም ነው፡፡ ጀሞ ሁለት በሚባለው አካባቢ  አንዲት አነስተኛ ቡና ቤት ውስጥ የተከሰተ አስፀያፊ ድርጊት ነው፡፡ ባለቡና ቤቷ ለስምንት ዓመታት በሥራ ፍለጋ ያለምንም ሥራ ስትንከራተት ቆይታ አክስት አጎቶቿ ተባብረው አንዲት ቡና ቤት ይከፍቱላታል፡፡ በዚያ መተዳደር ከጀመረች ጥቂት ወራት አለፉ፡፡ …

    Read More »
  • 9 March

    የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ለ30ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ የፖሊስ ኃይል አባላትን ዛሬ አስመርቀ ! ለዉጡ ይሄ ነው እንዴ?

    የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በቡልቡላ ማሰልጠኛ ማእከል ለ30ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ልዩ የፖሊስ ኃይል አባላትን ዛሬ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት እንደሚያስመርቅ የክልሉን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ Biniam Shemelis ሌሎችም ክልሎች ከዚህ ልምድ በመውሰድ አቅማቸውን በማጠናከር የህዝባቸውን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ይገባል ። ለኢትዮጵያ ግን የሚጠቅመው አንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብቻ ነበር።ነገር ግን …

    Read More »
  • 9 March

    All Ethiopian Unity Party (AEUP) opposition party merge with Bale Adera.

    March 6, 2020 Two Prominent opposition parties announced on Friday that they had formed a coalition ahead of the upcoming Ethiopian General Election in August 2020. All Ethiopian Unity Party (AEUP), one of the oldest opposition political party in the country initially founded by Professor Asrat Woldeyes as All Amhara …

    Read More »
  • 7 March

    ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ

    በኢትዮጵያ 2 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል! የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ተመሳሳይ ምልክት የታየባቸው ሁለት ሰዎች በለይቶ ማቆያ ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቋል። ለ910 ሰዎች የጤና ክትትል እየተደረገ ነው ያለው ኢንስቲትዩቱ፥ ስምንት አዳዲስ ጭምጭምታዎች ደርሰውት በኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ ህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማጣራት ተደርጓልም ብሏል። ከእነዚህ ውስጥ …

    Read More »
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.