Breaking News
Home / News / Opinion from Amhara Activist.

Opinion from Amhara Activist.

ማብራሪያ ስለመስጠት /የግሌ ነው/

የክርስቲያን ታደለVS ዶ/ር አምባቸው የትላት እሳቤና የአማራ ቀጣይ የቤት ስራ !!!

የሰሞኑ የከሚሴና የሰሜን ሸዋው የአማራ መጠቃት አመት ሙሉ ዝግጅት የተደረገበት ነው ለዚህ ደግሞ የሰሜን ሸዋ ዞን የፀጥታ መምሪያ ምስክርነት ሰቷል ዛሬ ላብራራ የፈለኩት የሁለቱን ሰዎች አገላለጽ ነው በመጀመሪያ ጥቃቱ የተፈፀመብን በኦሮሚያ ልዩ ሃይልና በመከላከያ ስውር ጥምረት ነው በዚህ ሰዓት የኦነግ ሃይል የሚባል ነፃ መሬት የያዘ ቡድን የለም
1. ቀደም ብለን እንደሰማነው ኦህዴድ ከኦነግ ጋር ባደረገው ስምምነት የኦነግ ሰራዊት የኦሮሞ ልዩ ሃይል ሊሆን ነው ይህም 1500 ሰራዊት ካምፕ ገብተው ሰልጥነው ተቀላቅለዋል

2.ቀሪዎቹ በወለጋ የነበሩት ደግሞ ከጦርነቱ እና ከበቂ ባንክ ዝርፊያ በኋላ ድጋሚ ተስማምተው ልዩ ሃይሉን ተቀላቅለዋል 
3.ኦነግ ከኦህዴድ እውቅናና ድጋፍ ውጭ በዚህ ልክ ታጥቆና በተሽከርካሪ የሚጓጓዝበት ነፃ መሬት የለም

4. ኦህዴድ በኦነግ ስም ብአዴንን ለመበጥበጥ ሲፈልግ እነጃዋርና ዳውድ ኢብሳ እንኳን እንዳይጠየቁ አዲስ አበባ ካለው የኦነግ አመራር ጋር ተለያይተናል የሚል ድራማ ሰሩ

5. በተግባርም የኦሮሞ አንዳንድ ባለስልጣናት እና ፓለቲከኞች በአዴፓ ላይ በተለይ በዶ/ር አምባቸው ላይ ዛቱ የአመራር ለውጡንም አጥብቀው አወገዙ

6. የዶ/ር አምባቸው ከአብንና ከአማራ አክቲቪስቶች ጋር መናበብና መሞጋገስ ለኦህዴድ ፓለቲከኞች እና ለግንቦት 7 አለቅላቂወች የእግር እሳት ሆኗል። በግልፅም ፎክረዋል

ስለዚህ ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያትና ጥምረት ኦዴፓ/ኦህዴድ/ በአማራ ላይ ጦርነት ከፍቷል ።

የሁለቱ መሪዎች እይታ

ሀ. ክርስቲያን ታደለ በገፁ የጠቆመን 
በኦሮሚያ ልዩ ሃይል የታገዘ በህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው እንደ አመጣጡ በህዝብ እንመልሰዋለን ብሏል ይህ ለኔ የተጠና እና በሳል ጥቆማ ሲሆን አንዳንዶቻችሁ ግን የብሔር ትንኮሳ ብላችሁታል ጉዳዩ ግን ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሞከረውን ኦህዴድ ተጠያቂ ለማድረግ ነው ።

ለ. የዶ/ር አምባቸው መግለጫ 
መግለጫው አጭርና ማጣፊያ የለለው ለተባሰና ለተወረረ ህዝብ ብሶት የማያክም ንግግር መሆኑ አይካድም። ምክንያቱም መግለጫ ፓለቲከኛውን ሰው ብቻ ሳይሆን ሌላውን ህዝብም ያማከለ መሆን ነበረበት ነገር ግን የፕሬዘዳንቱ ጉዳይ በሶስት አቅጣጫ ፈተና ወስጥ ወድቀዋል መግለጫውም ይህንኑ ጉዳይ በጥንቃቄ ለማለፍ እና ወደ ተግባር የተገባውን ስራ ላለመግለፅ ይመስላል ።

አጣብቂኞቹን ላብራራ

1. ከአዴፓ ጉባኤ ጀምሮ አንተን ሊቀመንበር አናደርግም ወደ ጦርነት ትከተናለህ የሚለው አሮጌው የብአዴን ቡድን እና አፍቃሪ ህወሃቱ ጫጫታ እና ሴራ አሁንም ከጀርባ እየወጋቸው መሆኑ እና የአመራር ሪፎርም እሰራለሁ በማለታቸው ከምንወጣ በግርግር እንቆያለን ብሎ በማሰብ የተያዘው ሴራ እንዲሁም እኛስ ብለን ነበር ይሄው አጋጨን የሚለው የውስጠ ድርጅት አሉባልታ

2.የኦዴፓ በዶ/ሩ እና ዬሃንስ ቧያለው ጥምረትና አሰላለፍ ላይ የገባው ስጋት እና አዴፓን ለማንበርከክ የተያዘው እቅድ

3. የአማራ አክቲቪስቶች እና የተፎካካሪ ፓለቲከኞች ፈጣን የነፃነት ፍላጎት እና የዘመናቱ የጭቆና ምሬት ናቸው

በእኔ እይታ 
የሰሞኑን ጥቃት የዶ/ር አምባቸው እና ቡድናቸው የውስጥ እይታ ጉዳዩን ኦነግ ለተባለ ባለቤት አልባ ቡድን መስጠት ሳይሆን የፈለጉት ከጀርባ ለሚያስፈፅመው እና አንዳንዶቹም በይፋ ለሚሳተፉበት ኦህዴድ ሲሆን እንደ ክርስቲያን እሳቤ ግልፅ ግምገማ ለማድረግ የፈለጉ ይመስላል መሆንም አለበት ።
ስለዚህ አንዳንዱ የነቀፌታ ጉዳይ ጊዜና ጉልበትን ታሳቢ ማድረግ አለበት ባይ ነኝ ። በዚህ ሰዓት አዴፓ እኛ እንደፈለግነው ጉዳዩን በኦነግ አመካኝቶ ተራ ጉዳይ ማድረግ ወይም በኦዴፓ/ኦህዴድ/ አመካኝቶ ያለቅድመ ዝግጅት ወደ ጦርነት መግባት ታሪካዊ ውርደት ሊያስከትል ይችላል። በሌላ በኩል አዴፓ በፓለቲካ ግምገማ ሌሎች ፓርቲወችን አሳትፊ ኦዴፓን እገጥማለሁ ከሚል የስራ አስፈፃሚ ግምገማ ጊዜ መጠበቅ ይመስላል።

አስቸኳይ መፍትሄ እና መሆን ያለበት

1. ማንም ሰው በልመና ሊያከብር ወይም ሊያርፍ አይችልምና ሰፊ ልዩ ሃይልና ምልስ ወታደሮችን አሰልጥኖ ማዘጋጀት 
2. በቂና የቡድን መሳሪያዎችን ከወዳጅ ሃገራት በስምምነት አሊያም በስውር ማስገባት 
3. በየወረዳው ሁሉንም የግልም ይሁን የመንግስት ታጣቂ በነፃ በወረዳ ደረጃ ማሰልጠን 
4. ሰልጣኝ ሲመለመል በርሃማ ወረዳዎች ላይና ልምድ ያላቸውን በስፋት ማሰልጠን 
5. የፀጥታ ስምሪት ሲሰጥ ህዝብን የማይጎዳ ነገር ግን እጣቱን የቀሰረውን ሁሉ ያለይሉኝታ መቁረጥ የሚችል ትዛዝ ያስፈልጋል 
6. በየዞኑና ወረዳዎች በክልልና ደህንነቶች አማራን የማይመጥን አድሃሪ አመራርን እና የፀጥታ መሪን በፍጥነት መቀየር ህዝብ የማይደራደርበት ጉዳይ ነው 
7. በመጨረሻም አማራ በሁሉም መመዘኛ አሸናፊ መሆኑን ማመን እና በድፍረት መስራት ይሉኝታን ታጥቦ መድፋት አዋጭ ነው።

ማጠቃለያ ; እና ማሳሰቢያ

1. መደማመጥ መተባበር ለአማራ ትንሽም ቢሆን የሚሰራውን ማክበርና በተገቢው እና ተስፋ በማያስቆርጥ መልኩ መተቸት ተገቢ ነው ስንጣላ እንድንታረቅ መሆንም አለበት 
2. ከአንድ ላይ የምንቆምበት የማይቀር ጦርነት መኖሩን መገንዘብ እና አማራን ከውርደት ለመታደግ በጋራ መስራት

3. የፓርቲ እና የግል ጥቅምን ወደ ጎን በመተው በአማራነት መደራጀት እና ማሰብ ታሪካዊ ግዴታ ነው።

4. የአማራን የውስጥ ሰላም እና አንድነት መጠበቅ የአሸናፊነታችን ግማሽ መንገድ ነው።

5. በየትኛውም መለኪያ ሲያጠፋም ይሁን ሲያለማ መሪን መከተል ግዴታ ነው መሪ የለለው ትግል ውጤቱ ባዶ ነው።

6. የምንከተለው የትግል መስመር የአብን ወይም የአዴፓ የማታገያ መስመር ብቻ ነው ከዚህ ውጭ ያለው የግለሰብ አስተያየት ለያዥና ለገራዥ የሚያስቸግር ነው ። 
የአንዳቸውን ጥሪ መቀበልና የቀሪውን ጉዞ ማክበር እልል የተባለለት የፓለቲካ ትርፍ ነው ።

ደግሜ ልንገራችሁ መስመር እና መሪ የለለው ትግል ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ብቻ ነው በአንዴ እና በአንድ ጉዳይ ክርስቲያንና ጋሻውን በሌላ ሳይድ አምባቸውን እና ዬሃንስን እኩል መሳደብ ከሁለት ያጣ ጎመን መሆን ነው ። እኔን ያልገባኝ ሁለቱንም አጣጥለን እኛን ፈጣሪ መቶ ሊመራን ነው ???

ዛሬ እየሆነ ያለው ጥፋት ሁሉ የትላንት ስህተትና ከንቱነት የ27 ዓመቱ የአመራር በክትነት ነው በትላቱ ስህተት የዛሬን ሰው በአግባቡ መተቸት እና በልኩ መደገፍ እንጅ ማሳደድ እና መጥላት ትርፉ መሪአልባነት ብቻ ነው። በእርግጥ የብአዴን ጉዳይ ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው። አበቃሁ !!

ስለእውነት ነውና ትግላችን ይቀጥላል !!!

Check Also

ልደቱ አያሌው ከኤርፖርት እንዲመለስ ተደረገ!

የአብይ አህመድ አስተዳደር እልም ያለ አምባገነን መንግስት ከወያኔ የባሰ ነው:: ቺግሩ በሁሉም ሰው ላይ ሊደርስ …

ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የዉይይት መድረክ እነሆ ! እንዳይቀሩ !

Related Posts:ለአማራ ምሁራን ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የቀረበ ጥሪ !ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ –አብን ብሔራዊ ምክር ቤት …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.