Breaking News
Home / Documents / Categories

Categories

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ –አብን ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ !

***

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ –አብን መላው የአማራ ሕዝብ ከተደቀነበት የኅልውና ስጋት ተላቆ በወርዱና በቁመናው ልክ ፍትኃዊ ድርሻውን ፤ ዘላቂ መብትና ጥቅሙን እንዲያስከብር የተደራጀ ትግል ለማድረግ ዓላማው አድርጎ የተመሰረተ አማራዊ አደረጃጀት ነው፡፡ አብን ከተመሰረተበት ከሰኔ 3/2010 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ የአማራ ሕዝብን ትግል ወደፊት የሚያራምዱ እንቅስቃሴዎችን አድርጓል፡፡ ከእነዚህ መካከል በበርካታ ቦታዎች የአማራን ሕዝብ የማንቃት እና የማደራጀት ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ በበርካታ ከተሞች እና ወረዳዎች ሕዝባዊ ውይይቶችን እና የአደባባይ ስብሰባዎችን አከናውኗል፡፡ ከአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ ካሉ ድርጅቶች ጋር ለመስራት በጎ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በውጭ አገር የሚኖሩ አማራዎችን በማንቃትና በማደራጀት ትግሉን ለመደገፍ የበኩላቸውን ን ሚና እንዲወጡ ጥረቶች ተደርገዋል፤ በመደረግም ላይ ናቸው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ–አብን ብሔራዊ ምክር ቤት ንቅናቄው ካሉት 3 ዋና ዋና ሥልጣን ተቋማት አንዱ ሲሆን ተቀዳሚ ተግባሩም የንቅናቄውን የሕግ አውጭነት ሚና በመያዝ ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ እንዲሁም የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት የበጀት እና ዕቅድ አፈፃፀም ክንውን መገምገም እና ማፅደቅ ነው፡፡

በዚህ ስልጣኑ አግባብ ከጥቅምት 3/2011 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 4/2011 ዓ.ም ድረስ ሁለተኛውን መደበኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ ጉባኤው፡-

ሀ) የሥራ አስፈፃሚውን የ4 ወራት የሥራ ክንውን ሪፖርት በማድመጥ ተወያይቶና ገምግሞ አፅድቋል።

ለ) የንቅናቄውን ያለፉትን የ4 ወራት የፋይናንስ ሪፖርት በማድመጥ ተወያይቶና ገምግሞ አፅድቋል።

ሐ) የ2011 በጀትና ዕቅድ ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይቶችን በማድረግ አፅድቋል፡፡

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.