Breaking News
Home / Amharic / Amhara Bank Mutual Fund. How to buy share.

Amhara Bank Mutual Fund. How to buy share.

By: Letenah Ejigu Wale

በገቢ ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል የአማራ ባንክ አክሲዮንን እንዴት ሊገዛ ይችላል ? መልሱ Mutual Fund ነው ። በጣም ወሳኝ አጀንዳ ስለሆነ በትኩረት አንብቡት !!!

የተወሰኑ ወጣቶች አንድ ሰው ሊገዛ የሚችለው ዝቅተኛ የአማራ ባንክ አክሲዮን መጠን አቅማችን ስላልቻለ ከ10,000 ብር ወደ 5,000 ብር ወይም 3,000 ብር ብታወርዱልን ብለው ይጠይቃሉ ። ነገር ግን ይህን ማድረግ አይቻልም ። ይህም የሆነበት ምክንያት የአማራ ባንክ አክሲዮን ለመሸጥ ብሄራዊ ባንክ ላይ ሲያመለክት የአክሲዮን ሽያጭ መረጃን የያዘ ዶክመንት አቅርቧል ። በዚህ ዶክመንትም ዝቅተኛውን እና ከፍተኛውን የአክሲዮን ግዢ እናም ሌላም መረጃ ለብሄራዊ ባንክ ገልጿል ። ይህ ዶክመንት በብሄራዊ ባንክ ፀድቆ ወደስራ ከተገባ በኋላ መቀየር አይቻልም ። አማራ ባንክ አሁን ላይ ወደ አክሲዮን ሽያጩ ስለገባ የአክሲዮን ሽያጩን ዶክመንት አደራጆቹ እንደፈለጉ የሚቀይሩት ነገር አይደለም ። እና ወጣቶች ይህንን ተረዱት ። ያው ዝቅተኛውን አክሲዮን 10,000 ብር ራሱ የሆነው ብዙ በገቢ ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል እንዲሳተፍ ስለተፈለገ ነው ።ነገር ግን ወደ 10,000 ብርም ዝቅ ብሎ የአማራ ባንክን አክሲዮን መግዛት አልቻልንም ብለው ወጣቶች ይኸው እዚህም እዚያም ይጠይቃሉ ።

ለዚህ ችግር የማቀርበው መፍትሄ Mutual Fund የሚባል ተቋምን መፍጠር ነው ። ሃሳቡ ለአገራችን አዲስ ሊሆን ይችላል ። በአደጉት አገራት ግን በደንብ የሚሰራበት ነው ። Mutual Fund ሀሳቡ ምን መሰላችሁ ? የህብረተሰቡን በጣም ትናንሽ ቁጠባ ሰብስቦ በትላልቅ ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ በገቢ ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል በትላልቅ ኩባንያዎች በተዘዋዋሪ መንገድ ባለአክሲዮን የሚሆንበትን እድል የሚፈጥር ተቋም ነው ። ከዛም ከትላልቅ ኩባንያዎች ለMutual Fund የሚሰጠውን የትርፍ ክፍፍል ወይም ሌላ ጥቅም የድርጅቱን አስተዳደራዊ ወጭን ሸፍኖ ገንዘቡን ለአባላቱ ያከፋፍላል ። ስለዚህ ይህን ተቋም አሁኑኑ ወጣቶች ተደራጅተው ከፈጠሩት ከ 10,000 ብር ባነሰ የእያንዳንዱ አባል መዋጮ ሁሉም ወጣት የአማራ ባንክ ባለአክሲዮን እና መስራች መሆን ይችላል ። እና ይኸ ወርቅ ሀሳብ አይደለም ጓዶች ?

ስለዚህ ወጣቶች ዳይ አፍጥኑት ። ይህን ሀሳብ አሁኑኑ ተግብሩት እና በተዘዋዋሪ መንገድ የአማራ ባንክ ባለአክሲዮን ሁኑ ። የ Mutual Fundን ሀሳብ ወደመሬት ለማውረድ የሚከተለውን ስራዎች ተራ በተራ ስሩ ።

1. መጀመሪያ በየአካባቢያችሁ ተደራጁ ። መደራጀቱን አሁኑኑ ጀምሩት ። ወይም ያሉትን የወጣት ማህበራት አደረጃጀቶች ተጠቀሙ ። መደራጀት ለፖለቲካ ወይም ማህሰራዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚም እጅግ ወሳኝ ነው ። አክሲዮን ማህበር መመስረት ማለት ለኢኮኖሚ ለውጥ መደራጀት ማለት ነው ። አከተመ!!! ሰለዚህ ተደራጁ ተደራጁ ተደራጁ !!!

2. ከተደራጃችሁ በኋላ በየአቅራቢያችሁ በሚገኝ ንግድ ቢሮ ሂዳችሁ አክሲዮን ማህበር በፍጥነት መስርቱ ። ንግድ ቢሮዎች የአክሲዮን ፈቃዱን ቶሎ ስጧቸው ።

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሰረት አንድ አክሲዮን ማህበር ለመመስረት ዝቅተኛ የሚያስፈልግ የሰው ብዛት 5 ሰዎች ሲሆን ፤ ዝቅተኛ ካፒታል ደግሞ 50,000 ነው ። የአንድ አክሲዮን ዋጋ ደግሞ እስከ 10 ብር ዝቅ ማድረግ ይቻላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማህበር መመስረት ቀላል ነው ጓዶች ። አክሲዮን ማህበር መመስረትን አትፍሩት ።

የንግድ ህጉን ይዘን እስቲ በአንድ ቀበሌ የሚከተለውን Mutual Fund ለምሳሌ ያህል እናቋቁም ። ለምሳሌ አንድ ወጣት በግሉ ለአክሲዮን ግዢ ማዋጣት የሚችለው ከፍተኛው ብር 500 ነው እንበል ። ያ ማለት ከ500 ብር በላይ ማዋጣት አይችልም ማለት ነው ። ስለዚህ የ50,000 ካፒታል ያለውን Mutual Fund ለመመስረት 100 ወጣት በቂ ነው ። ነገር ግን ለአክሲዮን ግዢ አንድ ወጣት 1000 ብር ማዋጣት ከቻለ ግን ድርጅቱን በ50 ወጣቶች መመስረት ይቻላል ማለት ነው ። ስለዚህ አንድ ወጣት ከፍተኛ ማዋጣት የሚችለውን አቅሙን ካወቅን በስንት ወጣቶች ድርጅቱ ሊመሰረት እንደሚችል ማወቅ ቀላል ነው ።

ለምሳሌ በአንድ ቀበሌ 2000 ወጣት ተሰባስባችሁ ብትደራጁ እና አንድ ወጣት 1000 ብር ማዋጣት ቢችል 2,000,000 ብር ሰበሰባችሁ ማለት ነው ። ይህን ብር ይዛችሁ እንደ ድርጅት ከፍ ያለ የአማራ ባንክን የአክሲዮን ድርሻ ልትገዙበት ትችላላችሁ ። እና ነገሩ እንዲህ ቀላል ነው ። ለወጣት አባሎቻችሁ አክሲዮን ስትሸጡ ድርጅታችሁን ለመመስረት የሚያስፈልገውን አስተዳደራዊ ወጭ ለመሸፈን 5% አካባቢ ተጨማሪ ኮሚሽን ልትሰበስቡ ትችላላችሁ ።

ከላይ ለምሳሌ አንድን Mutual Fund ወጣቶች ተሰባስበው በቀበሌ ደረጃ ሊመሰርቱት ይችላሉ ። ነገር ግን የ Mutual Fund ራዕይ እንዳይጠብ እና ካፒታሉም ውስን እንዳይሆን ከቀበሌ ወጥተን በከተማ ፤ ዞን ፤ ክልል ፤ አገር አቀፍ ደረጃ ሊመሰረት ይችላል ። ለምሳሌ ካልተሳሳትኩ ባህር ዳር 17 ቀበሌ አለ ። ከእያንዳንዱ ቀበሌ አክሲዮን የሚገዛ 2000 ወጣት ብናገኝ ፤ የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1000 ብር ቢሆን የሚሰበሰበው ጠቅላላ 34 ሚሊየን ብር ይሆናል ( 17 ቀበሌ * 2 ሚሊየን ብር በቀበሌ)። አያችሁት አይደል የመደራጀት ጥቅም !!!

በዚህ Mutual Fund አንድ ሰው መግዛት የሚችለው ዝቅተኛ የአክሲዮን ብዛት አንድ አክሲዮን ነው ። የ Mutual Fund አላማው በገቢ ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል በተዘዋዋሪ መልኩ በትላልቅ ኩባንያ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲሳተፍ ስለሆነ አንድ ሰው መግዛት ያለበትን ዝቅተኛ የአክሲዮን መጠን ከአንድ አክሲዮን በላይ ካደረግነው በገቢ ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል አገለልነው ማለት ነው ። እንዲህ ከሆነ ድርጅቱ አላማውን ይስታል ማለት ነው ። እናም አንድ ሰው መግዛት ያለበት ዝቅተኛ የአክሲዮን ብዛት ከአንድ አክሲዮን መብለጥ የለበትም ።

በዚህ Mutual Fund አንድ ሰው መግዛት የሚችለውን ከፍተኛ የአክሲዮን ብዛት ከ 5 አክሲዮኖች ባይበልጥ ጥሩ ነው ። ከ 5 ከበለጠ ጥቂቶች ይህንን Mutual Fund ይቆጣጠሩትና ድርጅቱ በገቢ ዝቅተኛው ማህበረሰብን መወከሉን ይተዋል ። Mutual Fundም ይጠለፋል ። ስለዚህ የድርጅቱ አላማ እንዳይጠለፍ የከፍተኛው የአክሲዮን ግዢ መጠን ብዙ መሆን የለበትም ። ከ 5 አክሲዮኖች ባይበልጥ ጥሩ ነው ባይ ነኝ ።

የህግ ባለሙያዎች የዚህን ድርጅት የመመስረቻ ፅሁፉ ለወጣቶች ቶሎ ፃፉላቸው ። በነፃም ቢሆን ፃፉላቸው ። የሚመሰረተው አክሲዮን ማህበር Mutual Fund ነው ። በመመስረቻ ፅሁፉ ውስጥ የዚህ ድርጅት ስራው እና አላማው በሚለው ውስጥ የምትፅፉት የሚከተለውን ነው ። ድርጅቱ የህብረተሰቡን ትናንሽ ቁጠባ አሰባስቦ በትላልቅ ኩባንያዎች ላይ አክሲዮን ይገዛል ። ከዚያም ከተገዛው አክሲዮን ላይ የሚገኘውን ጥቅም አስተዳደራዊ ወጭውን ቀንሶ ለድርጅቱ ባለአክሲዮኖች (በዚህ ምሳሌ ለወጣቶች) ያከፋፍላል ። በቃ Mutual Fund ስራው ይኸ ነው ። አለቀ ደቀቀ !!! ትንሽ ብርን ይዞ በትላልቅ ኩባንያዎች ኢንቨስት የማድረግ ችግርን መፍትሄ የሚሰጥ እጅግ ዘመነኛ ተቋም ። እና ምን አለፋን ። እሱን መስርተን መገላገል እና ወደ ሃብት ጎራ የሚደረገውን ጉዞ መጀመር ነው!!!

ይህን Mutual Fund የተባለ ድርጅት የሚያስተዳድረው ግን በሙያው የሰለጠነ ሰው መሆን አለበት ። በፋይናንስ ፤ አካውንቲንግ እና ተመሳሳይ ዘርፎች ቢያንስ ዲግሪ እና ልምድ ያለው መሆን አለበት ።

Mutual Fund በጣም ብዙ ጥቅሞች ያሉት ወሳኝ ተቋም ነው ። ወደፊት ስለ Mutual Fund አይነቶች ፤ ስለጥቅሞቹ ወዘተ እፅፋለሁ ። አሁን ፀጥ ብላችሁ ወደ ድርጅቱ ምስረታ ሂዱማ !!!

ወጣቶች አፍጥኑት ብር አይናቅም !!! አሁኑኑ ስራውን ጀምሩት ። ምንም ጊዜ አታጥፉ እሽ ። ልዩነቱን ታዮታላችሁ ። የኢኮኖሚ አብዮቱ ተፋፍሞ ይቀጥላል !!!

Letenah Ejigu Wale

Check Also

አማራና ትግሬ ተስማሙና ኦሮሙማን መክቱ። – ሞጣ ቀራንዮ

https://fb.watch/f-ipLpwPrZ/ Related Posts:አማራና ኦሮሞ አትጣሉ። ተዋደዱ !አማራና ትግሬ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የኦሮሞ ክልል አስተዳደር …

ማስጠንቀቂያ ለከንቲባ አዳነች እቤቤ!

Related Posts:የጃዋር ሞሃመድ የዜግነት አወዛጋቢ ጉዳይ. ጃዋር ማስጠንቀቂያ ተሰጠው !

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.