Breaking News
Home / News / Advice to Dr. Ambachew

Advice to Dr. Ambachew

ዶ/ር አምባቸውና ቲሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ እነዚህን አማካሪነት ቦታዎች በልዩ ትኩረት ሰጥቶ ቢተገብራቸው ለአማራ ህዝብ ባለውለታ ሆኖ ማለፍ ይችላል፦

1.#የሴኩሪቲ_ጉዳይ አማካሪ፦ እዚህ ላይ አራት አይና ንስር ሰው የሚያስፈልግበት ነው።የዚህ ዘርፍ ሰው በዋናነት በሚሊታሪና ደህንነት ልምድ ያለው፣በወጣቱ ጋር በቀላሉ ሊግባባ የሚችል፣ ጥሩ ስብዕና ያለው #ጎልማሳ ቢሆን ይመረጣል።

2.#የኢኮኖሚ ጉዳይ አማካሪ፦ እዚህ ላይ በተለይም የክልሉን የሀብት አማራጭ የሚተነትን፣ባለሀብቶችን የሚስብ፣ሚዲያ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር፣ፌደራል ላይ የእርዳታና ብድርን ሴራ የሚያውቅ፣ ጥሩ ተግባቦት ክህሎት ያለው #ጎልማሳ ያስፈልገዋል።

3.#የወቅታዊ_ጉዳይ አማካሪ (ይህ ዘርፍ በዋናነት ክልላዊ እና ሀገራዊ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ፣ማህበራዊ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያተኩር ሆኖ ተለዋዋጩን ፖለቲካ እና ማህበራዊ እና ሜንስትሪም ሚዲያውን የሚከታተል፣ አሰላለፍን የሚቃኝና የሚያማክር ያስፈልገዋል።እዚህ ላይ ግዴታ በእድሜው በጣም #ወጣት የሆነ ሰው ቢሆን ጥሩ ነው።
እዚህ ላይ ወቅቱን ያል

4.#የዘላቂ_ፖለቲካ ጉዳይ አማካሪ (ይህ ዘርፍ የወቅቱን የሀገር ቤት የየቃውሞና የድጋፍ እንዲሁም የየክልሎች የፖለቲካ አሰላለፍ፣የምስራቅ አፍሪካ አተያይ፣የምዕራባውያን አሰላለፍ በቅርበት የሚያማክር)
በፖለቲካ፣በፀጥታና በዘላቂ ልማት ትንተና ላይ ልምድ ያለውና የሀገራትን ግንኙነት የሚያጤን #በእድሜው እና #በልምዱ #በሰል ያለ ቢሆን ይመረጣል።

ከተለያየ ወገን ሀሳብ አሰባስበን ብቁ የሆኑ አማራዎችንም ጥቆማ ለማድረግና ለመተባበር ዝግጁ ነን።

N.B. እነዚህ አማካሪዎች ከነባሮቹ ውጭ መሆን አለባቸው።ነባሮቹን ማስቀጠል ለክልሉ ህዝብ የሚፈይደው ምንም ነው።

ለመጠቆም የወደድኩት ይዘነጉታል ብየ ሳይሆን ምናልባትም ስለዘገዩና ይህንን ማድረግ ባለመቻሉ የታዩ የተወሰኑ ክፍተቶች አሉ።

በተረፈ ማህበራዊ ሚዲያውን ከአምስት ቀን አንድ ቀን ቢጎበኝ/ሞኒተር የሚያደርግለት ቢኖርም ጥሩ ነው።ያው ባለፉት አራት አመታት ኢትዮጵያ የምትመራው በማህበራዊ ሚዲያው መሆኑ ይታወቃል።
good views ayalew

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.