Breaking News
Home / Amharic / መንግስት የዜጎችን በየትኛውም አካባቢ የመኖርና ንብረት የማፍራት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን ሊያከብር ይገባል

መንግስት የዜጎችን በየትኛውም አካባቢ የመኖርና ንብረት የማፍራት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን ሊያከብር ይገባል

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዙሪያ ሱሉልታ ከተማ ልዬ ሰሙ ቀርሳ በሚባል አካባቢ  ከነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከለሊቱ 11፡00 ጀምሮ ብሔራቸውን መሰረት ተደርጎ እየተለዩ ቤታቸው እየፈረሰባቸው ይገኛል፡፡ በቦታው ብዛት ያላቸው የታጠቁ ኃይሎችን በማስፈር በሰው ኃይልና በሎደር ቤት እያፈረሱ ሲሆን ለምን ብለው የጠየቁ ብዙ ሰዎችም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የተቀሩትም ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ባሉበት ታግተው ይገኛሉ፡፡ ዜጎች በላባቸው ያፈሩትን ኃብትና የሰሩትን ቤት በማንነታቸው ምክንያት ማፍረስና ዜጎችን በክረምት ለጎዳና ህይወት መዳረግ ፍፁም ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም መንግስት ዜጎች በየትኛውም ቦታ በዘር፣ በኃይማኖት እና በማንነታቸው ልዩነት ሳይደረግባቸው የመኖርና ንብረት የማፍራት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን በአስቸኳይ እንዲያስከብርና ሰብአዊ ቃውስ እንዳይደርስ የመከላከል ስራ እንዲሰራ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ይጠይቃል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!!

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.