Breaking News
Home / Amharic / አቶ ፀጋ አራጌ ትኩዬ እውነቱን አፈረጡት!

አቶ ፀጋ አራጌ ትኩዬ እውነቱን አፈረጡት!

አቶ ፀጋ አራጌ ትኩዬ ‼️
****************
ዋጋ ከፍሎ ከአማራ ህዝብ ጎን በመቆም ታሪኩን በወርቅ ቀለም ጽፎ ለማለፍ የሚወስን ፍለጋ ስንባጅ አንድ የአሳምነው ትንፋሽ ሳናገኝ አልቀረንም። ሌላ ቁርጠኛ ብቅ ይል እንደሁ ደግሞ በተስፋ እንጠብቃለን።
ሰውዬው እውነትን ተጋፍጠው በአማራ ህዝብ ስነ ልቦና ልክ ከፍታቸውን አስተካክለው ለመገኘት ቆራጥ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል ማለት ይቻላል።
*****
አቶ ፀጋ አራጌ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ አቶ ደመቀ መኮንን በሚመራው ስብሰባ ላይ በአማራ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ጅምላ ጭፍጨፋ አውግዘው የአማራ ባለስልጣናት ከፍርሃት እና አድርባይነት እንዲወጡና ህዝባቸውን እንዲታደጉ ጠይቀዋል።
አቶ ፀጋ አራጌ “በፓርቲያችን ብልጽግና ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የህግ ጥሰትና የአሰራር መዛነፍ እንዲስተካከል ስለመጠየቅ” በሚል ርዕስ ለፓርቲው የቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በቀጥታ፣ በግልባጭ ለፓርቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ደብዳቤያቸውን ማስገባታቸው ታውቋል።
አቶ ጸጋ አራጌ ለኦዲት ኮሚሽን ያቀረቡት ደብዳቤ የተለያዩ የህግ ጥሰቶችን የሚያነሳ መሆኑንም ተመልክቷል። በተለይም የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ በደንቡ የተሰጠው ስልጣንና ተግባር አካሉ ሳያውቀው ሙሉ ለሙሉ መጣሱን አመልክተዋል። ማዕካላዊ ኮሚቴው ማንም አካል በማያውቀው መንገድ ሁለት መደበኛ ስብሰባ አልፎበት ሶስተኛው መደበኛ ስብሰባን ለማሳለፍ በመንደርደር ላይ መሆኑንም አሳውቀዋል።
በአንጻሩ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አብይ አህመድ የፓርቲውን ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነውን የፓርቲ ተቋም የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባን በማጠፍና በመተው በህግም፣ በአሰራርም ሆነ በሞራል የማይመለከታቸውን ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን በመሰብሰብ የፓርቲውን የፖለቲካና የትግል መድረክ ሆን ብለው የማቀጨጭ አቅጣጫ ተከትለዋል ይላሉ። ይሄም የፓርቲውን ቁመና በእጅጉ ጎድቶታል በማለት አቶ ጸጋ አራጌ ይከሳሉ።
የፓርቲው ጉባኤ በሁለት አመት ተኩል መካሄድ እንዳለበት በህግ ቢቀመጥም ማዕከላዊ ኮሚቴው በማያውቀው ሁኔታ ለሶስት አመት ተኩል እንዲራዘም ተደርጓል ይላሉ። በአሁን ሰአት ደግሞ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለማንኛውም አካል ውክልና ባልሰጠበት ሁኔታ ህገወጥ አዘጋጅ ኮሚቴ በማን እንደተቋቋመ የማይታወቅ የጉባኤ ዝግጅትን እየመራ ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ አካል የማያውቀውን ሰነድ ቀጥሎ ላሉ የመዋቅር አባላት እያወረደ በማደናገር ላይ ነው ሲሉም ይከሳሉ።
በፓርቲው ውስጥ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እየቀረ በጸረ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እየተተካ ነው ይላሉ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ጸጋ አራጌ። ሁሉም ነገር በግለሰብ የግል ፍላጎትና በተናጠላዊ እንቅስቃሴ እየተሰራ በመሆኑ ፓርቲው የግለሰብ ተንቀሳቃሽ ንብረት እስኪመስል ድረስ ተቋማዊ ህልውናውን እስከማጣት ሊደርስ የሚያስችል የህልውና አደጋ ተደቅኖበታል ብለዋል።
የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ አቶ ጸጋ አራጌ የቁጥጥርና የኢንስፔክሽን ኮሚሽኑ በ48 ሰአታት ውስጥ የጽሁፍ ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ ፓርቲዎችን ለማስተዳደር ስልጣን ለተሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማቅረብ የሚገደዱ መሆኑን በደብዳቤያቸው ላይ አሳውቀዋል።
የ48 ሰዓታት ማስጠንቀቂያ የሰጡበት ደብዳቤ ከስር ተያይዟል።
#ሼር በማድረግ ለህዝብ እንዲደርስ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ !!
 

Check Also

የፓርላማ ተወካዮች ፀረ አማራ የሆኑ ዝርዝር ከነስልክ ቁጥራቸው

Related Posts:የህዝብ ተወካዮች ስልክ ቁጥር ዝርዝር።ይሄ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው ሀንጋሳ ኢብራህም የሚባለው ኦህዴድን ብልጥግናን ወክሎ …

የህዝብ ተወካዮች ስልክ ቁጥር ዝርዝር።

ሼር ይደረግ! የህዝብ ተወካዮች የምክር ቤት በነገው እለት በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀውን የእልቂት አዋጅ ለማፅደቅ …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.