Breaking News
Home / News / ከንቲባው ድምፃቸው ጠፋ!

ከንቲባው ድምፃቸው ጠፋ!


የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር መሃሪ ታደሰ ለ15 ቀን እረፍት ቤተሰብ ጥየቃ ብለው አሜሪካን ቢጓዙም ሳይመለሱ ወራት እያስቆጠሩ ነው አሁን ላይ ደግሞ መረጃ የሚያደርሱበትን በግላቸው የሚጠቀሙበትን የፌስ ቡክ አካውንት ዲ አክቲቪ አድርገዋል ይህ ነገር አጋጣሚ ነው ወይስ እንጠርጥር

ከተማዋ ከ2009 ዘጠኝ ወዲህ ከንቲባ ሲሾም ሲሻርባት የረባ ስራ ትልልቅ የመሰረተ ልማት ዝርጋታወች በሚያስፈልጋት ልክ ሳይገነባላት የሄደን ዳቦ ቆርሳ ስትሸኝ የመጣን ርችት ተኩሳ ድግስ ደግሳ ስትቀበል እድሜዋን እየፈጀች ነው ባለችበት እያረጀች ሳትለማ እየተበላች ኖሮን ተያይዛዋለች

ጥያቂየ ዶክተሩ ይመለሳሉ በዛው ይቀራሉ ነው እንደምናየው ሌሎች ከተሞች ፕሮግራም ቀርፀው የሚለሙ ልማቶች ላይ ተወያይተው ከተማቸውን ለማልማት ስራ ላይ ናቸው የእኛ ከንቲባ ከከተማዋ ከራቁ ወራት ተቆጥሯል

ከተማዋ እውቀት ብቃት እንዲመራት ሆና ከአዴፖ እስረኝነት ነፃ ብትወጣ መልካም ነው የማንም አቅመ ቢስ በከተማ ነክ ዘርፍ እውቀት የሌለው ከተለያየ ዘርፍ እያመጣችሁ ከተማዋን ማዘረፍ ወደ ሁዋላ ማራመድ ልታቆሙ ይገባል ።

ዶክተር መሃሪ ከመጡ መልካም ነው እንጠብቃለን ከቀሩስ ማንን ከየትኛው ቦታ አምጣችሁ ልትሾሙ ይሆን የአማራ ብልፅግና ፖርቲ ከተማዋን ቁልቁል ይዞ የሚወርድ አሰራርን በከተማዋ ላይ ከመተግበር ታቀቡ ከየትም ለቃቅማችሁ ሹማችሁ ከተማዋ የውር ድንብስ ጉዞ እንድትጓዝ አትፍረዱባት ።

Check Also

የትግራይ ተወላጅ ነዋሪዎች ቤት እየገቡ ማሰር ማፈን!

የታጠቁ የበዳዲና (ብልጥግና ) ሰዎች የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ በአዱስ አበባ የትግራይ ተወላጅ ነዋሪዎች ቤት …

የአባይ ግድብ ሲሞላ !

Related Posts:የመጀመሪያው ዙር የአባይ ግድብ የዉሃ ሙሌት!አሜሪካ የአባይ ግድብ በዉሃ አንዳይሞላ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች !

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.