Breaking News
Home / Amharic / ወያኔዋ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) ከሥልጣኗ ተወገደች !

ወያኔዋ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) ከሥልጣኗ ተወገደች !

እጅግ መረን በለቀቀ ሁኔታ የኢትዮጵያን የመንግሥት ሥልጣን ተቆጣጥሮ የነበረው የተገንጣይ ወንበዴዎች ቡድን እና በዚሁ የተገንጣይ ቡድን ስም አገር ሲገዛ የኖረው ትህነግ/ህወሓት በአሁኑ ወቅት በሚኒስትሮች ም/ቤት ያለው ኅልውና ሊከሰም ጥቂት ነው የቀረው።

የጠ/ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ፣ የመከላከያ (ኤታ ማዦር ሹም)፣ የማስታወቂያ (በኋላ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተባለው) ወዘተ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በብቸኝነትና በማንአለብኝነት ለበርካታ ዓመታት ሲቆጣጠር የነበረውን የተገንጣይ ቡድን በሚኒስትሮች ም/ቤት ትወክለው ነበረችው ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ከሥልጣኗ ተወግዳለች። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የላከውን መረጃ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አማርኛ ልሳን በፌስቡክ አረጋግጧል።

የህወሓት የፖሊትቢሮ አባልና የደብረጽዮን ምክትል የሆነችው ፈትለወርቅ (ሳሞራ የኑስ ባወጣላት የበረሃ ስሟ “ሞንጆሪኖ” ተብላ የምትጠራው) በሚኒስትሮች ም/ቤት የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ብቸኛ ተወካይ ነበረች።

ሌላኛዋ የህወሓት አባል ያለም ጸጋዬ የትህነግ የሥራ አስፈጻሚ አባል ባትሆንም ህወሓትን በሚኒስትሮች ም/ቤት የምትወክል ብቸኛዋ ሆና ቀጥላለች።

ህወሓት ጠፍጥፋ በሠራቻቸው ፓርቲዎች የመሠረተው ኢህአዴግ የተባለው ድርጅት ወደከርሰ መቃብር ከወረደ በኋላ አባልና አጋር የተባሉት ፓርቲዎች በሙሉ በመዋሃድ ብልጽግና ፓርቲን ሲመሠርቱ ትህነግ/ህወሓት ብቻዋን አልቀላቀልም በማለት እንደስሟ ተገንጥላ ቆይታ ነበር። በመጨረሻም ብልጽግናን አልቀላቀልም፣ ንብረቴን መልሱልኝ በማለት መግለጫ ማውጣቷ ይታወሳል።

የፌዴራሉንና በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ከፍተኛ የሥልጣን ቦታዎችን ያለገደብ እና ያለበቂ ዕውቀትና የትምህርት ዝግጅት (አለ ተብሎ የተመዘገበውም በግዢ ከዲግሪ ወፍጮቤቶች የተመረተ ነው) በግፍ ሲገዛ የነበረው የተገንጣይ ወንበዴዎች ቡድን ከምኒልክ ቤተመንግሥት ከተወገደ በኋላ የትግራይን ሕዝብ አግቶ በአፈና እየገዛ ይገኛል። ሰሞኑን የተነሳበት ሕዝባዊ ተቃውሞም የትግራይ ሕዝብ ይህንን የጥቂቶች ቡድን ከላዩ ለመጣል ፈር የሚቀድ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ተሰጥቶታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ፈትለወርቅን በሦስት መሥመር ደብዳቤ ካባረሯት በኋላ በምትኳ የቀድሞው የንግድ ሚ/ር የነበሩትን መላኩ አለበልን በሚኒስትርነት ሾመዋል። ህወሓትን አልፈልግም ብለው የወጡትና አገርበቀል መፍትሔዎችን በማመንጨት የ3.5 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ የሆኑት አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ ጌታሁን መኩሪያን (ዶ/ር) በመተካት የኢኖቬሽን እና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ጌታሁን የትምህርት ሚ/ር ሆነዋል።

በፈትለወርቅ መነሳት ከፍተኛ ክስረት የደረሰባት ትህነግ/ህወሓት ጉዳዩን ከሕዝብ ጋር ጠብ የመጫሪያ ስልት አድርጋ ለመጠቀም የሞከረችው የተሳካ ባይሆንም ከምርጫው በኋላ ብልጽግና እንደ ፓርቲ የመንግሥትን ሥልጣን የሚይዝ ከሆነ የህወሓት ኅልውና ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከፌዴራል መንግሥት ተወግዶ እንደ ፈጣሪዋ መለስ የሙት ዓመቷን ራሷ እየዘከረች የምትኖር ትሆናለች በማለት በፌስቡክ ገጻችን ለጎልጉል አስተያየታቸውን የላኩ ተሳልቀዋል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

 

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.