Breaking News
Home / Amharic / ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ።

ጠ/ሚ/ሩ አገር መምራት ስላልቻሉ ስልጣን መልቀቅ አለባቸው!
*****
👉በዶክተር ደሳለኝ ጫኔ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳዩት ከፍተኛ የሆነ የአመራር ድክመት፣ብቃት ማነስ፣
የአገሪቱን ውስብስብ ችግሮች አቅልሎ ማየትና በበቂ ሁኔታ ተተድቶ መፍትሄ
መፈለግ ስላልቻሉ ስልጣን እንዲለቁ መጠየቅ መጀመር አለብን።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ማግስት ጀምሮ፦
1) ከ2000 በላይ አማሮች በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በደቡብና በኦሮሞ ክልል
በማንነታቸው ተለይተው በጅምላ ሲጨፈጨፉና እንደቅጠል ሲረግፉ፣ ዛሬ ብቻ
በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ ከ250 በላይ አማራ/አገው/ሺናሻ በቆዳ
ቀለማቸው ተለይተው ሲታረዱ የወሰዱት ርምጃ ካለመኖሩም በላይ ለአማራ
ዘር ማጥፋት እያሳዩት ያለው ስሜት አልባነት፣ ቸልተኝነትና እንዝህላልነት
ለተቀመጡበት ወንበር የማይመጥን በመሆኑ፣
2) ፋሽስቱ ትህነግ 2 አመት ሙሉ ዝግጅት ሲያደርግና በአገር መከላከያ
ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሶ ወታደሮችን እስከመግደልና መሳሪያዎችን
እስከመዝረፍ የደረስ ጥቃት እስኪያደርስ ድረስ ችግሩን በማቃለል፣ በማናናቅና
በማድበስበስ ላሳዩት ድክመትና ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ያለመቻል
ከስልጣን እንዲለቁ መጠየቅ አለብን።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆይ፦ ኢትዮጵያን በአግባቡ መምራት ስላልቻሉ፣
አገራችን በሩዋንዳ እንደተፈፀመው አይነት የዘር ፍጅት ቀስ በቀስ እያመራች
በመሆኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ስልጣንዎትን በገዛ ፈቃድዎ
መልቀቅ እንዳለብዎ እንደአንድ ዜጋ እጠይቃለሁ።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.