Breaking News
Home / Amharic / ዶ/ር አምባቸው አዳራሹን አነቃነቁት:: አማራ ከእንግዲህ አያለቅስም!

ዶ/ር አምባቸው አዳራሹን አነቃነቁት:: አማራ ከእንግዲህ አያለቅስም!

ከ ቬሮኒካ መላኩ

የተከበራችሁ አንባብያን
እነሆ በረከት
በአማራ ገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ጠቅላላ ለመሰብሰብ የታቀደው 1.5 ቢሊዮን ብር ነው። የቴሌቶኑ አዘጋጆች ከጠቅላላው 1.5 ቢሊዮን ብር ውስጥ በአንድ ምሽት በሸራተኑ ዝግጅት እንሰበስባለን ብለው ያቀዱት 5 መቶ ሚሊዮን ብር ውስጥ ከ150 ፐርሰንት በላይ አሳክተው በሰአታት ቀን ብቻ 800,000,000 የሚያክል ብር ሰብስበዋል። በዚህ ፔስ መቀጠል ከቻልን የጠቅላላ ግባችን ከ200% በላይ በአጭር ጊዜ ማሳካት ይቻላል።
.
የፖለቲካ የሀይል ሚዛን በዚህ ወቅት ጥርት ብሎ ወጥቷል። ዛሬ የአማራ መጠናከር ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ትልቅ ዋስትና መሆኑን የተረጋገጠ ጉዳይ ሆኗል።ላለፋት 10 ወራት” በኢትዮጵያ ሱሴ” ጭምብል ስር ተደብቆ የነበረው የፖለቲካ አወናባጅ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ጠንዝቷል። ዛሬ አማራነትን እኛ አማሮች ብቻ ሳንሆን የኢትዮጵያ ዉድ ልጆች የሆኑት ብሄር ብሄረሰቦች በፍቅር የሚመለከቱት ማንነት ሆኗል ። ለዚህም ማረጋገጫ በቴሌቶኑ የተሳተፉት የሶማሌ :አፋር : ቤኒሻንጉል : ጋምቤላ ህዝቦች አጋርነት ማረጋገጫ ነው ። በተለይ ሱማሌ ክልልን ለየት የሚያደርገው በቴሌቶኑ የሱማሌ ክልል መንግስት ብቻ ሳይሆን የሱማሌ የቢዝነስ ግሩፕ መሳተፉ ነው ። 
.
እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች በመልእክት መቀበያ ሳጥኔ ውስጥ በአስቀመጡልኝ መልእክት በቴሌቶኑ ስልክ እየደወሉ ብር ለመለገስ ስልኩ ተጨናንቆና ሞልቶ መግቢያ አጥተን ከክፍሉ ደጅ እየተቆራጠጥን ነው ብለውኛል ። ይሄ የአማራ ምጥቀት ድንቅ ነው። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የአማራን ጣዕም የበለጠ እየተረዳ የመጣዉ የአሁኖቹን ወሮበላ ባለ ተራ መሪዎች ሲመለከት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ኬክ ሲጠብቅ ሬት ሆነው መጡለት ።በመጨረሻ አማራ ሲተርት “ጋን በጠጠር ይደገፋል” እንድል ድጋፋችሁን ቀጥሉ።ብልህ ህዝብ ብልህ ዘመን ይሰራልና ዘመናችንን እንስራ ።
አመሰግናለሁ።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.