Breaking News
Home / Amharic / የዉጫሌ ዉል መፍረስና የአድዋ ጦርነት መነሻ ምክንያት !

የዉጫሌ ዉል መፍረስና የአድዋ ጦርነት መነሻ ምክንያት !

የዉጫሌ ዉል መፍረስና የአድዋ ጦርነት መነሻ ምክንያት ::

ራስ መኮንን ጣልያንን ለመጎብኘት በሔዱበት ጊዜ ጣልያንና ኢትዮጽያ የዉጫሌን ዉል እንደተፈራረሙና ኢትዮጽያ በጣልያን መንግስት ስር ልትኖር ስምምነት ተደረገ የሚል ወሬ በጣልያን ጋዜጣ ላይ ተፃፈ ።በወቅቱ እቴጌና ሚኒልክ ጥበብ ተማር ብለዉ ኢጣልያ ሀገር የሰደዱት አንድ አፈወርቅ የሚባል ትዉልዱ የዘጌ የሆነ የኢትዮጽያ ልጅ ከዚያዉ ነበረና ይሄን ቃል ከጋዜጣ ላይ አይቶ ለደጃች መኮንን ነገራቸዉ ።
* የኢጣልያ መንግስት መልክተኛ ኮንት ሳልምቤኒ እንጦጦ በሐምሌ ገባ ።
አጤ ሚኒልክ በክብር አሳምረዉ ተቀበሉት ከዚያ ወዲያ የዉጫሌ ዉል እንደገና ተነሳ ።አጤ ሚኒልክ ኢትዮጽያ ቀጥ ለጥ ብላ እራሷን ችላ በመንግስቷ አገዛዝ ትኖራለች እንጅ በማንም መንግስት ጥግ ትኖር ዘንድ ከዛሬ በፊትም በታሪክ አልተገኘም ለእንግዲሁም እንዲህ ያለዉ ነገር አይታለምም በማለት እቅጩን አስረግጠዉ ነገሩት ዉሉ የፍቅራችንን የንግዳችንን እንዲህ እንዲህ ያለዉን ነገር ይናገራል እንጅ ኢትዮጽያ በኢጣልያ ጥግ ትኖራለች የሚል ቃል ከአማርኛዉ ፅህፈት አይገኝበትም ። ኮንት አንቶሎኒ ችክ ብሎ የተዋዋልነዉ ለ 5 አመት ነዉ ከዛ ዉስጥ 2ቱን ጨርሰነዋል ስለዚህ ለዚች ለቀረችዉ ጊዜ ስለ ክፍል 17 አናንሳዉ ይቅር ዝም በሉ ብሎ ለጃንሆይ ተናገረ በዚህ ጊዜ መቸም ነገር ካስተርጓሚዉ ነዉና አስተርጓሚዉ ኮንት አንቶኔሊ እንዳለዉ አምስት አመቱ እስኪያልቅ ክፍል 17 አይነሳ ይቅር ይላል ብሎ ማስተርጐሙን ትቶ እንዲያዉ ባጭሩ 17 ክፍል ይቅር ይላል ብሎ ለጃንሆይ ተናገረ ጃንሆይም ይቅርን በሰሙ ጊዜ እኔስ እስከዛሬ የተናገርኩት በ17 ክፍል እንዲቀር አልነበረምን አሁንም ይቅር ይሰረዝ አሉ
ከዛ የስምምነት ሰነዱ ላይ በአማርኛ የተፃፈዉ ቃል ይቅር ተሰርዟል ይል ነበር ይሄዉ ቃል በሁለት ወረቀት ተቀድቶ አንዱ ለኮንት አንቶኔሊ አንዱ ከቤተ መንግስት ተቀመጠ ።
*ኮንት አንቶኔሊ እሱ እንደተመኘዉ ሁኖ የተፃፈ መስሎት ደስ ብሎት ተቀበለ ይሄ በሆነ በማግስቱ ግን ኮንት አንቶኔሊ ያን ወረቀት ለሌላ አስተርጐአሚ አስተርጉሞ ባየ ጊዜ የ17 ኛዉ ክፍል የነበረዉ ቃል ተሰርዞአል ማለት ለመቼዉም ተፍቋል የሚል መሆኑን አወቀዉ * ኮንት አንቶኔሊ በዚህ በጣም ተናዶ እና ደንግጦ ወደ ጃንሆይ በመመለስ እቴጌና ጃንሆይ የተቀመጡበት እልፍኝ በመግባት ለምን የ 17 ተኛዉ ክፍል ተሰርዞአል ተብሎ ተፃፈ በማለት ጃንሆን ይጠይቃል ጃንሆይም ሁለታችን አንተና እኔ ተነጋግረን አንተ ወደህና ፈቅደህ የተፃፈ ቃል ነዉ ሌላ አልታከለበትም ባስተርጐሚህ የተናገርከዉ ነዉ አሉት።
ከዛ ኮንት አንቶኔሊ እንዳልተሳካለት አዉቆ የዉሉን ወረቀት በጫጨቀዉና ጦርነቱ እንደማይቀር ተናግሮ ከልፍኝ እየወጣ እያለ “እቴጌ ጣይቱ ከት ብለዉ በመሳቅ የዛሬ ሳምንት አድርገዉ በዚህ የሚደነግጥ የለም ሂድ የፎከርክበትን አድርግ እኛም የመጣዉን እናነሳዋለን እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰዉ ከዚህ የሌ ለ አይምሰልህ የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነዉ እንጅ መት አይደለም አሁንም ሂድ አይምሽብህ የፎከርክበትን በፈቀደህ ጊዜ አድርገዉ እኛም ከዚሁ እንቆይሀለን አሉት” ዳግማዊ አጤ ሚንልክም እንግዲህ ከኢጣልያ ጋር መዋጋታቸዉ ቁርጥ መሆኑን አወቁና መሳርያ ማሰናዳት ጀመሩ ።

ምንጭ ጦቢያ ዳግማዊ አጤ ሚኒልክ

ክብር ለሚገባቸዉ ክብር መስጠት ባህላችን እናድርግ

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.