Breaking News
Home / Amharic / የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከስቶ የነበረው ችግር እንደተፈታ አስታወቀች::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከስቶ የነበረው ችግር እንደተፈታ አስታወቀች::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ተከስቶ የነበረው ችግር በቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና እና ሥርዓት መሠረት እንደተፈታ አስታወቀች።

በዚህም መሠረት የቤተክርስቲያኗን ሥርዓት እና ሕግ ጥሰዋል ተብለው በቅዱስ ሲኖዶሱ ተወግዘው ተለይተው የነበሩት አባቶችም ወደ ቤተክርስቲያኗ መመለሳቸው ተገልጿል።

ሶስቱ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስና አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ ሃገረ ስብከታቸውና ማዕረጋቸው እንዲመለሱና ተሿሚዎቹ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመታቸው የጵጵስና ሹመታቸው
ተሽሮ ወደነበሩበት የክህነት ማዕረግ እንዲመለሱ ተወስኗል።

ከተሾሙት መካከል በቤተ ክርስቲያን ስርዓት ተመዝነው የሚያሟሉት በቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲሾሙ ይደረጋል ተብሏል።

ቤተ ክርስቲያኗ ሕገወጥ ነው ካለችው ጵጵስና ሹመት ጋር ተያይዞ ባለፉት ሳምንታት በአገሪቱ ስጋት ፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና እና ሥርዓት መሠረት መፈታቱን ቅዱስ ሲኖዶስ ረቡዕ የካቲት 08/2015 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል።

ችግሩ መፍትሔ ማግኘቱን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ጊዜ የቤተክርስቲያኗ ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብረሃም “ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች” ብለዋል።

ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ችግሩን በፖለቲካዊ መንገድ ከመፍታት ባሻገር በቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና ሥርዓት መሠረት እንዲፈታ ታላቅ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።

“አሁን ችግሩ ተፈትቷል፣ ወደፊትም የቤተ ክርስቲያኗ ሉዓላዊነት እና አንድነት ተጠብቆ ክርስቶስ እስከሚመጣ በአንድነቷ እና በሉዓላዊነቷ ትኖራለች” ማለታቸው በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።

ችግሩም እልባት እንዲያገኝ በቤተ ክርስቲያኗ በኩል አቡነ ናትናኤል፣ አቡነ ኤርምያስ፣ አቡነ ሩፋኤል እና የአገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ስለመደረጉ እና ችግሩንም ለመፍታት መቻሉ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበትም ቤተ ክርስቲያኗን የወከሉ አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ባሉበት ውይይት ተደርጎ የተደረሰበትን ስምምነት ሲኖዶሱ ተቀብሎታል ብሏል።

ከሦስት ሳምንታት በፊት በቤተክርስቲያኗ አካታችነት እና የቋንቋ አጠቃቀም ላይ ያነሳናቸው ጥያቄዎች ምላሽ አላገኙም በማለት 26 ኤጲስ ቆጶሳትን በመሾም ውዝግቡ መጀመሩ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከሃይማኖታዊ ቀኖና እና ሥርዓት ውጪ ነው በማለት የጵጵስና ሹመቱን የሰጡት እና ተሿሚዎችን የቤተክርስቲያኗን ሕግ እንዲሁም ሥርዓት ጥሰዋል በማለት አውግዞ እንዲለዩ መወሰኑ ይታወሳል።

ነገር ግን አባቶቹ ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ የሚጠይቁ ከሆነ ቤተክርስቲያኗ መልሳ እንደምትቀበላቸው ገልጻ ነበር።

በአባቶቹ መካከል የተደረሰው ስምምነት

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ለመስጠት የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች የካቲት 8/2015 ዓ.ም. ያደረጉት ውይይት አስር ነጥቦችን በማሳለፍ ተጠናቋል። በዚህም

  • 1. ቤተ ክርስቲያኗ ሥልጣናቸውን ሽራ ያወገዘቻቸው ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ አገረ ስብከታቸው እና ማዕረጋቸው እንዲመለሱ፤ እንዲሁም ተሿሚዎቹ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመታቸው ተሽሮ ወደነበሩበት የክህነት ማዕረግ እንዲመለሱ ተወስኗል። ከተሾሙት መካከል በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት መመዘኛውን የሚያሟሉት በቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲሾሙ ይደረጋል ተብሏል።
  • 2. በኦሮሚያ ክልል በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት፣ ቅዳሴ እና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሰጡ የተጀመረው ሥራ የሕዝቡን ጥያቄ ባማከለ መልኩ እንዲጠናከር
  • 3. በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች የተዳከሙ አብያተ ክርስቲያናትን ቋንቋውን በሚያውቁ አገልጋዮች እና በአገልግሎት ማጠናከር
  • 4. በእነዚህ አካባቢዎች ቋንቋውን እንዲያውቁ የሚያሰለጥኑ ተጨማሪ ኮሌጆች እና ማሠልጠኛዎች እንዲከፈቱ
  • 5. ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት ቋንቋውን የሚያውቁ እና የሚያገለግሉ ኤጲስ ቆጶሳት በቀጣይ የግንቦት የካህናት ጉባኤ ላይ ተወስኖ እንዲሾሙ
  • 6. በአስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ በፋይናንስ፣ በምደባ፣ በቅጥር የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት ማሻሻል እና ማጠናከር
  • 7. የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከር እና ለትውልድ አርዓያ የሚሆን ቤተ ክህነት እንዲኖር ለማድረግ አሰራሯን በጥናት አሻሽሎ ቤተ ክርስቲያኗን ለትውልድ ማሻገር
  • 8. ጥላቻን የሚያባብሱ ነገሮችን ከማድረግ ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራን እና አባቶች እንዲቆጠቡ እንዲሁም ይሄንን ተግባር ሆን ብለው የሚያደርጉም ተወግዘዋል
  • 9. ቤተ ክርስቲያኗ የገጠማትን ፈተና ውስጧን ለመፈተሽ፣ አንድነቷን ለማጠናከር እና የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን ለማስፋፋፋት ለበጎ መጠቀም የሚሉት ተጠቅሰዋል።

ችግሩ መፍትሔ ማግኘቱን በተመለከተ መግለጫ በተሰጠበት ጊዜ የቤተክርስቲያኗ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብረሃም “ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች” ብለዋል።

ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ችግሩን በፖለቲካዊ መንገድ ከመፍታት ባሻገር በቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና እና ሥርዓት መሠረት እንዲፈታ ታላቅ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.