Breaking News
Home / Amharic / የአብይ መንግስት የተሳሳተ፣ የሕዝብን ጥቅም ለአደጋ ያጋለጠ፣ የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ!

የአብይ መንግስት የተሳሳተ፣ የሕዝብን ጥቅም ለአደጋ ያጋለጠ፣ የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ!

በቀይ ያለው ትግራይ ነው። ሕወሃቶች ከሞላ ጎደል ከቆላ ተምቤን ዋሻዎች ከገደል ወደ ገደል እየሸሹ ነበር የሚኖሩት። የአብይ መንግስት የተሳሳተ፣ የሕዝብን ጥቅም ለአደጋ ያጋለጠ፣ የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወስድኩ ብሎ ትግራይን ለሕወሃት አሳልፎ ሰጥቶ መከላከያ እንዲወጣ አደረገ።
ከትግራይ ብቻ አይደለም በራያ ግንባር መከላከያ እንዲወጣ ተደርጎ ራያ በወያኔ እጅ ልትወድቅ ችላለች። ወያኔ በዚህ አልተወሰነችም በወልቃይት ጠገዴ በርካታ ጊዜ፣ በሱዳን የመውጫ ኮሪዶር ለማግኘት ዉጊያዎችን ክፍታ ነበር። በዚያ ያለውን የነ ኮሎኔል ደመቀ ኃይልን መቋቋም ስላልቻለች አልተሳካላትም።
በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ውስጥ ውጊያ እየተደረገ አይደለም። ከትግራይ አልፎ ህወሃት ሙሉ ለሙሉ በተቆጣጠረቻቸው በዋገመራ ዞን አርበገሌ ወረዳ፣ በራያና በአፋር ክልል ዞን 4 ካልል አምስት ወረዳዎች 3ቱ ላይ ብዙ ጦርነት የለም።
የዋገመራ ሌሎች ወረዳዎች፣ ጠለምት፣ ጠለምትን የሚያዋስኑ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች፣ የሰሜን ወሎ ዞን የራያ አካባቢ፣ የተቀሩት ሁለት የአፋር ዞን 4 ወረዳዎች የጦርነት ቀጠናዎች ሆነዋል።
ከአፋር አንድ ዞን (ዞን 4) ፣ ሶስት ወረዳዎች፣ ከአማራ ክልል ሶስት ዞኖች (ሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ፣ ዋገመራ) 3 ወረዳዎች የዉጊያ ቀጠና ሆነዋል ማለት ነው።
በቅርቡ በአፋር ክልል፣ በሰሜን ወሎ ዞብል ተራራ አካባቢ እንዲሁም ጠለምትና ሰሜን ጎንደር ዞን በሚገናኙባቸው አካባቢዎች በተደረጉ ጦርነቶች ሕወሃት ከፍተኛ ሽንፈት እንዳጋጠማት በስፋት ተዘግቧል።
የአማራ ክልል ሰራዊት ብቃት ባላቸው የወታደራዊ ባለሞያዎችና ስትራቲጂስቶች እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎም በመጪው ቀናትና ሳምንታት ከሰሜን ወሎ፣ ከዋገመራ፣ ከራያ፣ ከስሜን ጎንደርና ከጠለምት ወያኔዎች የመወገድ እድላቸው በጣም የሰፋ ነው የሚሆነው። ከጅምሩ ገስግሰው እዚህ ደረጃ የደረሱት በዋናነት በዚያኛው ሳይድ በነበረው አሻጥርና የወታደራዊ አመራር ክፍተት እንደነበረ የሚታወቅ ነው። እድሜ ለብልጽግና የፖለኢትካ አመራሮች ይበሉ።
ትግራይ ውስጥ ጦርነት ባይኖርም፣ በጣም ከፍተኛ ቀውስ እየተፈጠረ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። በትግራይ መረጃ ማግኘት በጣም ከባድ ነው። ከእርዳታ ድርጅት ሰጭዎች በቀር መውጣትና መግባት የሚችል የለም። ከትግራይ ማግኘት የሚቻለው፣ እውነት ይሁን ውሸት እነ ጌታቸው ረዳ የሚለቁትን መረጃ ብቻ ነው።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.