Breaking News
Home / Amharic / የአማርኛ ቋንቋ ግስጋሴ አሁንም እንደቀጠለ ነው ::

የአማርኛ ቋንቋ ግስጋሴ አሁንም እንደቀጠለ ነው ::

#Ethiopia|| አንብቡትም #የአማርኛ ቋንቋ ግስጋሴ አሁንም እንደቀጠለ ነው። በዚህ ፍጥነቱ የአለም ቋንቋ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ዛሬ ደግሞ ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነግሮናል። ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት እንደጀመረ ሰማን። ይኼ የሚያስገርም አይደለም
ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት አልፎታል።
 

አማርኛ፦

 
1. በ2007 ዓ.ም.የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል።
2.. በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል።
3. Dstv’ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።
4. አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋም ነው። እንዲያውም በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ “እንኳን ወደ #WESTEND በደህና መጣችሁ!” የሚል ጽሁፍ ማየትም የተለመደ ነው።
6. በኢትዮጵያ በስነ-ጽሑፍ ቅርስነት በዮኔስኮ ከተመዘገቡት መካከል፦
– ታሪከ ነገስት ዘዳግማዊ ምኒልክ፣
-ዐፄቴዎድሮስ ለእንግሊዝ ንግስት ቪክቶሪያ የፃፉት ደብዳቤ፣
-ዳግማዊ ምኒልክ ለመስኮብ ቄሳር ዳግማዊ ኒኮላስ የፃፉት ደብዳቤና ሌሎችም በአማርኛ የተጻፋ ናቸው።
7. አማርኛ ቋንቋ በአፍሪካ ምድር በስነ ጽሑፍ ሀብት የበለጸገ ብቸኛው እና ነባር ቋንቋ ሲሆን አማርኛ ቋንቋ በአንድ ድምፅ የኮምፒውተር መተግበሪያ ተሰርቶለት እንግሊዝኛ ቋንቋ በቀላሉ መጻፍም ተችሏል።
በጉንደት፣በጉራዕ፣በአድዋ እና በማይጨው በተደረጉ ጦርነቶች ወታደሩን ከየብሄሩ ያሰባሰበ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ነው።
መይሳው ካሳ (ዐፄ ቴዎድሮስ) ለእንግሊዝ ማስጠንቀቂያ የሰጠው በአማርኛ ነው።
ዐፄ ዮሐንስ አዋጅ ያስነገረው በአማርኛ ነው።
ዐፄ ምኒልክ አለምን ያስደነቀ አመራር የሰጠው በአማርኛ ነው።
ዐፄ ኃይለሥላሴ ጀኔቫ ላይ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ንግግር ያደረጉት በአማርኛ ነው።
መንግስቱ ኃይለማሪያም 17 አመታት ሀገሪቱን አንቀጥቅጦ የገዛው በአማርኛ ነው።
መለስ ዜናዊ እድሜ ልኩን አገር የመራው በአማርኛ ነው።

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.