Breaking News
Home / News / የአማራ ወጣቶች ማህበር ወዴት መሸገ?

የአማራ ወጣቶች ማህበር ወዴት መሸገ?

አወማ-አማራው ከተደቀነበት ችግር አኳያ መመከት የሚችል የአደረጃጀት አድማስ እና ሀይል ያለው ነው፤ምክንያቱም አደረጃጀቱ በሁሉም የአማራ ግዛቶች አለ የያዘው ሀይልም ትኩስ በመባል የሚታወቀውን የወጣት ሀይል ነው፡፡ትኩስ ሀይል ደግሞ ዱካ ጠቋሚ ካገኜ እና፡ከልክ ያለፈ ግለት ሲሰማው ተው ብረድ ብሎ የሚመክረው አካል ካገኜ ሮጦ ይቀድማል ታግሎ ይጥላል፡፡

የዚን ሀይል ትኩስነት እና ጉልበት የተረዱ ጠላቶቺም ከብአዴን/አዴፓ ጀምሮ አምርረው ይጠሉታል፤የኮሸሽሌ እሾህም በእዬ መንገዱ ይዘሩበታል በሞቅታው ላይም ቤንዝን ያርከፈክፉበታል፤ስለሆነም ሀይሉ የሾህ መከላከያ ጫማ ሊጫማ የእሳት ማጥፊያ ዉሃ ሊይዝ ይገባል፡፡

ይሄ ችግሮቺን የደረጃ ድንጊያ አድርጎ፡በድንጋዬች ላይ እየተረማመደ የመጣው አወማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀዛቀዝ ታይቶበታል፤ምንአልባትም የመቀዝቀዙ ምንጪ በሀገራቺን ተጨባጪ ሁኔታ የፖለቲካ መስሪያ የሆነው የኮረና በሽታ እና በበሽታው ሰበብ የተዘጋጄለት ወጥመድ ይሆናል፡፡በኮረና በሽታ ምክንያት በታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዎጅ መሰረት ፖለቲከኞቹ በሚፈልጓቸው ግለሰቦቺ እና አደረጃጀቶች ላይ የወጥመድ መረቭ መዘርጋታቸው ሀቅ ነው፤ነገር ግን ወጥመድ ፈርቶ እጂን አጣጥፎ መቀመጥ ከመጠመድ ስለማያድን ከስብሰባ እና ከማናለብኝነት እንቅስቃሴ ተቆጥቦ በብልሀት ወቅቱን የሚመጥን የተቀመመ ስራ መስራት ያስፈልጋል፤ከዘመኑ ጋ ብረሩ የአዳራሽ ስብሰባን ወቅቱ ቢከለክል ፎን ኮንፈረንስ አልተከለከለም፡፡ና ራሂ ሹሃ-ያ በመቅለሲሱ ሃቅ፡፡ሰላም፡፡

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.