Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ክልል ምክር ቤት የአፈና ውሎ ቀጥሏል !

የአማራ ክልል ምክር ቤት የአፈና ውሎ ቀጥሏል !

 
(ፀጋ አራጌ ትኩዬ)
የሚያሣዝነኝ ነገር ቢኖር ቢያንስ ቢያንስ መናገርና ሃሣብህን መግለፅ ከምትችልበት ሁኔታ እንዴት የማትችልበት እጣ ፈንታ ይቀየራል። እኔ በኢህአዴግ ጊዜ በማንኛውም አጋጣሚ ሃሣቤን ከመግለፅ ተገድቤም ታፍኘም አላውቅም። ለውጥ ብዬ ለለውጥ ታግዬ መጣ በተባለው የለውጥ ዘመን ግን የህግ ጥሠት አለ፣ ሰነ ስረአት ይከበር ብዬ በመከራከሬ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አዳራሽ በፖሊስ ተይዠ እንድወጣ ትእዛዝ ከተሠጠ በኋላ በምክር ቤቱ አባላት በተፈጠረ ጫጫት ፖሊስ ገብቶ ሣያወጣኝ ቢቀርም ነገሩ ግን እንዳልተፈፀመ አድርጌ አልወስደውም።
በመሠረቱ እኔ ሁሉንም ነገር ለመሆን የወሠንኩኝ ሠው መሆኔን ያላውቁ ሠዎች ጉዳዩን የተለያዬ ሠበብ አስባብ እየፈጠሩ ለማደናገር ቢሞክሩም አይሣካላቸውም። እኔ የአማራ ህዝብ ሞት እስከሚቆምና ጥያቄዎቹ እስከሚመለሱ ትግሉ የጠዬቀውን ዋጋ ሁሉ እከፍላለሁ። ይህንን ትግል ያለ ማቋረጥ በማንኛውም ያልተመቸ ሁኔታ ሣደርግ ስራ አጥቸ ፆም አዳሪ እንደምሆን፣ ታስሬ እንደምሠቃይ፣ ቀጥሎም የመጨረሻውን የሞት ፅዋ እንደምቀምስ በመዘንጋት አይደለም። መኪናና እጀባ ተጓድልብናል ብለው የአማራን ህዝብ በግዞት አስይዘው እንደሚቀልዱት ግን ለመቀለድ አልወሠንኩም። እኔ በምክር ቤቱ ውሎ ሃሣቤን ለመግለፅ እጀን ሣወጣ ብውልም እድል የሠጠኝ አካል የለም። ሠው በህጋዊ መድረክ ከተከለከለ የሚጠቀመው የትግል መድረክ ያገኘውንና በእጁ ያለውን እድል ይሆናል።
በምክር ቤቱ አባላት የስነ ምግባርና የአሠራር ስረአት ደንብ ቁጥር 12/2003 አንቀፅ 15 ን/አንቀፅ 1፣2፣3 የምክር ቤቱ ስብሠባ እንዴት በግልፅና በዝግ እንደሚካሄድ በግልፅ አስቀምጧል። እኔ የምጠይቀው የአማራ ክልልን ፍትህ ቢሮን ህግ በአደባባይ በማን አለብኝነት ሲሻር፣ በተሻር ህግ ስብሠባ ሲመራ ለምን ዝም እንደሚል ማብራሪያ እንድሠጥበት የሚመሩበትን ህግ የሻሩ ባለስልጣን ለምን እንደማይጠየቁ አሁንም ስለ ህግ አቤት እላለሁ።
በመጨረሻም የታፈንኩት እኔ ብቻ ነኝ ብዬ አላምንም። የታፈነው የአማራ ህዝብም ነው።
እኔ የማቀርበው ሃሣብ የዚህን ያህል ሚዛን ተሠጥቶት የሚፈራ መሆኑን እስካሁን ብዙ አልገመትኩም ነበር። ከዛሬ ስብሰባ የገባኝ ነገር ተካራክረው እኔን ማሸነፍ አይችሉም። ወደፊትም በሃሣብ አሸናፊ መሆኔን አረጋግጫለሁ። ዝርዝር የምክር ቤቱን ሂዴት ከቀናት በኋላ እፅፋለሁ።
ሃሣብና እውነት ያሸንፋል፣ ጉልበትና አፈና ይሸነፋል።

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.