Breaking News
Home / Amharic / የአማራ ባንክ ውክልናን በተመለከተ ማብራሪያ !

የአማራ ባንክ ውክልናን በተመለከተ ማብራሪያ !



1. ማን ነው የሚወከል ?
ከኮቪድ አንፃር እና የባንኩ ባለአክሲዮኖች ቁጥር ከ150,000 በላይ በመሆናቸው በባለ አክሲዮኖች እንዲወከሉ የሚፈለገው የባንኩ አደራጆች ናቸው ።
ነገር ግን ተመራጭ አማራጭ ባይሆኑም ባለአክሲዮኖች የሚከተሉት ሁለት መብቶች አሏቸው ። አንደኛ ከአደራጆች ውጭ ያለ ሌላ ማንኛውም ሰው የመወከል መብት አላቸው ። ሁለተኛ ማንንም ሰው አልወክልም እኔ በቀጥታ ነው ስብሰባ የምሳተፈው ካሉም መብታቸው ነው ።
ነገር ግን እነዚህን ሁለት አማራጮች በስፋት ጥቅም ላይ ከዋሉ በስብሰባው የሚገኘውን ሰው ቁጥር ያበዛብናል ። ይህ ሲሆን ደግሞ በኮቪድ እና ሎጂስቲክ ጉዳዮች ስብሰባው ማካሄድ ያስቸግረናል ። በዚህም የባንኩ ምስረታ ይጓተታል ። ስለዚህ ባለአክሲዮኖች ከላይ የተጠቀሱት ሁለት መብቶች ቢኖራቸውም የባንኩን ምስረታ ለማፍጠን ሲባል አደራጆችን እንድትወክሉና እና ምስረታውን እንድናፈጥነው ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን ።
ይህን ስንል ግን ባንኩ በአደራጆች ጉባኤ ብቻ ይመሰረታል ማለት አይደለም ። ሌላ ሰው በሚወክሉ ባለአክሲዮኖች ፤ በቀጥታ መገኘት በሚፈልጉ ባለአክሲዮኖች ፤ ከፍተኛ ድርሻ ባላቸው ባለአክሲኖች ፤ ብዙ ህዝብ በሚወክሉ ድርጅቶች ፤ ማህበራት ፤ እድሮች ወዘተ የሚካሄድ ይሆናል ። አደራጆችን ወክሉ ስንል የተሳታፊውን ቁጥር ለመቀነስ እንጂ አደራጆች ብቻ ስብሰባውን ያካሂዱታል ብላችሁ ያልተገባ ግንዛቤ እንዳትይዙ ለማሳሰብ እንወዳለን ።
የባንኩ አደራጆች በቁጥር 34 ናቸው ። የአደራጆቹ ኘሮፋይል ውልክና በምትሰጡበት ጣቢያ በፖስተር የሚተዋወቅ ይሆናል ። ከእነዚህ አደራጆች ውስጥ ይወክለኛል የምትሉትን አንዱን አደራጅ ወክሉት ።
የተጠናል ወይም የቡድን ውክልና መስጠት ይቻላል ። የተናጠል ውክልና ማለት አንድ ባለአክሲዮን አንድ አደራጅ ሲወክል ነው ። የቡድን ውክልና ማለት ደግሞ ለምሳሌ አንድ አስር ባለአክሲዮኖች ሰብሰብ ብለው በአንድ የውክልና ፎርም አንድ አደራጅ እንዲወክል ሲያደርጉ ነው ። ወጭ ከመቀነስ አንፃር እኛ የምንመርጠው የቡድን ውክልናን ነው ።
በውክልናው ለአደራጁ የምትሰጡት መብት ሁለት ነው ። አንደኛው በጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ነው ። ሁለተኛ የባንኩን መመስረቻ ፅሁፍና መተዳደሪያ ደንብ እንዲፈርም ናቸው ።
2. ውክልና የሚሰጠው መቸና የት ነው ?
ከህዳር 1-15 ፤ 2013
በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ እና ድሬዳዋ የምትገኙ ባለአክሲዮኖች የምትወክሉት በየአካባቢያችሁ የሚገኝ የፌደራሉ ውልና ማስረጃ ፅ/ቤት እየቀረባችሁ ነው ። አዲስ አበባ ላይ በየክፍለ ከተማው ባለ የፌደራሉ ውልና ማስረጃ ፅ/ቤት ለአማራ ባንክ ብቻ የተመደበ መስኮት ስላለ እየቀረባችሁ ውክልና መስጠት ትችላላችሁ ።
ከህዳር 16-30 ፤ 2013
በአማራ ክልል የዞን ከተሞች ያላችሁ ባለአክሲዮኖች የምትወክሉት በምናመቻቸው የፌደራሉ ውልና ማስረጃ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ይሆናል ። ይህንን ወደፊት የምነግራችሁ ይሆናል ።
ከህዳር 1-30 ፤ 2013
በአማራ ክልል የወረዳ ከተሞች እና በሌሎች ክልሎች ያላችሁ ባለአክሲዮኖች የምትወክሉት በየአካባቢያችሁ የሚገኙ የወረዳ የውልና ማስረጃ አገልግሎት የሚሰጡ የፍትህ ተቋማት ነው ። ውክልናውን ከሰጣችሁ በኋላ በተራ ቁጥር 3 ከታች ከተጠቀሱ ዶክመንቶች ጋር በአማራ ባንክ የአዲስ አበባ የፖስታ ሳጥን ቁጥር 149 አድራሻ መላክ አለባችሁ ።
በውጭ አገር የምትኖሩ ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የምትወክሉት ደግሞ በምትኖሩበት አገር ኤምባሲ በመቅረብ ይሆናል ። እናንተም ከላይ የተጠቀሱ ሙሉ ዶክመንቶችን በአማራ ባንክ ፖስታ ሳጥን መላክ አለባችሁ ።
3. ውክልናውን ለመስጠት የሚያስፈልግ ዶክመንት ፤
ለመወከል ስትመጡ የሚከተሉትን ዶክመንቶችን መያዝ አለባችሁ
የታደሰ መታወቂያ ፤ የቀበሌ ፤ መንጃ ፈቃድ ፤ ፓስፖርት ወዘተ እንደ መታወቂያነት ያገለግላል ።
አክሲዮን ስትገዙ የሞላችሁት የአማራ ባንክ ፎርም እና ገንዘቡን ገቢ ያደረጋችሁበት የባንክ ደረሰኝ ።
ለህፃናት አክሲዮን ከገዛችሁ የልደት ሰርተፊኬታቸው ያስፈልጋል።
አማራ ባንክ አ.ማ አደራጆች

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.