Breaking News
Home / Amharic / የብልጽግና ፓርቲ ሰንካላ አቋሞች!

የብልጽግና ፓርቲ ሰንካላ አቋሞች!

የብልጽግና ፓርቲ አባል ለመሆን “ዋልታ ረገጥ አመለካከትና ተግባሮችን በጽናት የሚታገል ” መሆን ቅድመ ሁኔታ ሆኖ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ምዕራፍ 2 አንቀጽ 9 ተራ ፊደል ሐ ላይ በግልፅ ተቀምጧል ። አልፎ አልፎ አንዳንድ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ይህን ደንብ ሲተላለፉ ማየት ለፓርቲው ህልውናም ሆነ ለሃገር ሰላም ጥሩ አይደለም ። ከህወሓት ጋር አብሮ ሊቀበሩ የሚገባቸው ብዙ ብዠታዎች አሉ ።
ሀገር እየመራ ያለው ብልጽግና ፓርቲ ግልጽ አቋም መያዝ እና ለሕዝቡ ማሳወቅ የሚገባው ጉዳዮች መሐከል የሚከተሉት ወሳኝ ይመስሉኛል ::
1️⃣
የአስተዳደር ክልል ወሰኖች በምንም መልኩ ድንበሮች አለመሆናቸውን እና ባስፈለገ ጊዜ ሊለዋወጡ የሚችሉ መሆኑን በግልፅ ማሳወቅ አለበት ። በቋንቋ መስፈርት የተከለሉት የህወሓት ክልሎች የተደራጁት ለአስተዳደር ምቹነት ሳይሆን ለመገንጠል እና ሌላ ሀገር ለመመስረት በሚመች መልኩ ታስበው የተዘጋጁ አስቂኝ ክልሎች ናቸው።
2️⃣
ህገመንግስቱ በርካታ አጨቃጫቂ የሆኑ ጥያቄዎች ያሉበት መሆኑን ማመን እና ተፈላጊው ማሻሻያ እንዲደረግበት የሚያስችል የሕዝብ ሃሳብ ማሰባሰብ ሥራ የሚሰራ መሆኑን ከወዲሁ መግለጽ አለበት ። ህገመንግስቱ ሕወሓት እና ኦነግ የኢትዮጵያውያንን አብሮነት በሚያጠናክር ሳይሆን ለነፃ አውጪ ድርጅትነት የመገንጠል ሕልማቸው እንዲመች አድርገው ያዘጋጁት የጋብቻ ፍቺ ረቂቅ ሰነድ ነው ።
3️⃣
መጤ ብሔር እና ነዋሪ ብሔር በሚል በጽንፈኞች ሲነዛ የነበረው አካሄድ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና በሕግ የሚያስቀጣ መሆኑን በይፋ መግለጽ በዚህ ድርጊት የተሳተፉ ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ ቅጣት በመጣል ለሕዝብ ይፋ መደረግ አለበት ። ወደ ኋላ እየቆጠርን እንተሳሰብ ከተባለ አዳም(አደመ) እና ሔዋንም(ሃዋ) ለዚህች ምድር መጤ መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም ።
4️⃣
በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ሁሉም መሬት የሁሉም ዜጋ መሆኑን እና ተመሳሳይ አይነት ቋንቋ መናገር ብቻውን የዚያ አካባቢ ብቸኛ ባለቤት የሚያደርግ ማረጋገጫ አለመሆኑን መግለጽ አለበት ። ቋንቋ የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ የሆነበት የህወሓት የከፋፍለህ ግዛው አሰራር መቀበር አለበት። አንድ ሲዳማ በኦሮሞ ክልል ኢንሸስት ሲያደርግ እንደውጭ ሀገር ባለሃብት የሚቆጠርበት እና እሱም ሌላ ሀገር ሄዶ ሃብቱን እንዳፈሰሰ እንዲያስብ ያደረጉ የህወሓት ከፋፋይ ፖሊሲዎች መወገድ አለባቸው ።
የብልጽግና ፓርቲ አመራር አባላት በዚህ ረገድ ተመሳሳይ አቋም ማራመድ ይገባቸዋል ። እየዘላበዱ ኢትዮጵያን ማሳዘን ማቆም አለባቸው ።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.