Breaking News
Home / Amharic / የምርጫ ዉጤት ! ባልደራስን አስሮ ብልጥግና 98% አሸንፍኩ አለ::

የምርጫ ዉጤት ! ባልደራስን አስሮ ብልጥግና 98% አሸንፍኩ አለ::

ቦርዱ እንዳመለከተው ብልፅግና ፓርቲ ከ436 መቀመጫዎች ውስጥ 410 ያሸነፈ ሲሆን ለቀጣዩ አምስት አመታትም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ወንበር አግኝቷል።

የተቃዋሚ ፖርቲዎች ያሸነፏቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት 11 ሲሆን የግል ተወዳዳሪዎች ደግሞ አራት አሸንፈዋል።

በአማራ ክልል አብን 5 የፓርላማ መቀመጫዎችን ሲያገኝ፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ኢዜማ 4 መቀመጫዎችን እንዲሁም የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 2 የፓርላማ መቀመጫዎችን አግኝቷል።

የግል ተወዳዳሪዎችን በተመለከተ በአዲስ አበባ አንድ የግል ተወዳዳሪ ያሸነፉ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ሶስት አሸንፈዋል።

በቀሪዎቹ አስር ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንባቸው መሆኑ ተገልጿል።

ለተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች እና የመቀመጫ ብዛት፣ የመራጮች ቁጥርና የመሳሰሉት መረጃዎችን እነሆ

1.አዲስ አበባ

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦1,819,343 መራጮች
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 99
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦ 23
  • ብልፅግና- 22
  • የግል ተወዳዳሪ አንድ

2.አፋር ክልል

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦1,696,016
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 97
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦8
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 6
  • ብልፅግና፦ 6

3.አማራ ክልል

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦7,122,516
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 94
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦138
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 125
  • ብልፅግና፦ 114
  • አብን፦ 5

በአንድ የምርጫ ክልል ድጋሚ ቆጠራ የሚካሄድ ሲሆን በአምስቱ ደግሞ እንደገና ምርጫ እንዲካሄድ ተወስኗል።

4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦162,609
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 55
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦9
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 3
  • ብልፅግና፦3

5. ድሬዳዋ

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦208,213
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 95
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦2
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 2
  • ብልፅግና፦ 1

በአንድ የምርጫ ክልል ድጋሚ ቆጠራ ይካሄዳል።

6. ጋምቤላ ክልል

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦415,899
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 89
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦3
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 3
  • ብልፅግና፦ 3

7. ኦሮሚያ ክልል

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦15,330,596
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 96
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦178
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 170
  • ብልፅግና፦ 167
  • የግል ተወዳዳሪዎች፡3

8. ሲዳማ ክልል

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦1,886,248
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 100
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦19
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 19
  • ብልፅግና፦ 19

9. ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል

  • የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር፦5,321,990
  • ድምፅ የሰጡ በመቶኛ 91
  • የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት፦104
  • ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው፦ 85
  • ብልፅግና፦ 75
  • ኢዜማ-4
  • የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፦2

የክልል ምክር ቤቶችን በምንመለከትበት ወቅት

  • ብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባን ምክር ቤት ሁሉንም 138 መቀመጫዎችን አሸንፏል።
  • በአፋር ከ96 ምርጫ መቀመጫዎች 51 መቀመጫዎች ብልጽግና ሲያሸንፍ፣ የአርጎባ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት 3 መቀመጫዎችን አሸንፏል። በአንድ የምርጫ ክልል ድጋሚ ምርጫ ይከናወናል።
  • በአማራ ክልል ከ294 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና 128 መቀመጫዎችን፣ አብን 13 መቀመጫዎችን አሸንፈዋል። በአምስት ምርጫ ክልሎች ድጋሚ ምርጫ ይከናወናል።
  • በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከ99 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ሰኔ 14 ምርጫ በተካሄደበት ብልፅግና 22 መቀመጫዎችን አሸንፏል።በአንድ የምርጫ ክልል ድጋሚ ምርጫ ይከናወናል።
  • በድሬዳዋ ከ189 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ብልፅግና ፓርቲ 189ቱን መቀመጫዎችን አሸንፏል።
  • በጋምቤላ ከ156 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ 149 መቀመጫዎች አሸንፏል። የጋምቤላ ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ጋህነን) 7 መቀመጫዎች አሸንፏል።
  • በኦሮሚያ ከ537 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ሰኔ 14 ምርጫ በተካሄደባቸው ብልጽግና ፓርቲ 513 መቀመጫዎች አሸንፏል።
  • በሲዳማ ከ190 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎ ብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም 190 መቀመጫዎችን አሸንፏል።
  • በደቡብ ክልል 291 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች በሰኔ 14 ምርጫ የተከናወነው በ89 ምርጫ ክልሎች ነው። ብልጽግና ፓርቲ 245 መቀመጫዎችን፣ ኢዜማ 10 መቀመጫዎች የጌዲኦ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት 6 መቀመጫዎችን አሸንፈዋል።

የቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በፓርላማ የአዲስ አበባ ተወካዮች

ምርጫ ክልል 1 -ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ
ምርጫ ክልል 2- ብርሃነ መስቀል ጠና
ምርጫ ክልል 3 – ዶክተር ሊያ ታደሰ
ምርጫ ክልል 4 – ሙሉ ይርጋ
ምርጫ ክልል 5 – ያስሚ ወህቢ
ምርጫ ክልል 6 – ዶክተር ወንድሙ ተክሌ
ምርጫ ክልል 7 – መሐመድ ከማል አሊ አል-አሩሲ
ምርጫ ክልል 8 – ዳግማዊት ሞገስ
ምርጫ ክልል 10 – ዶክተር ቤተልሄም ላቀው
ምርጫ ክልል 11 – ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም፣
ምርጫ ክልል 12 እና 13 – ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል
ምርጫ ክልል 15 – ህይወት ሞሲሳ
ምርጫ ክልል 16 – ሰሃርላ አብዱላሂ
ምርጫ ክልል 17 – ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር)
ምርጫ ክልል 18 – ዛዲግ አብርሀ
ምርጫ ክልል 19 – ዶክተር ትዕግስት ውሂብ
ምርጫ ክልል 20 – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ምርጫ ክልል 21 እና 22 – ዶክተር ይናገር ደሴ
ምርጫ ክልል 23 – ዲላሞ ኦቶሬ
ምርጫ ክልል 24 – ዶክተር ከይረዲን ተዘራ
ምርጫ ክልል 25 – ዶክተር ቶፊቅ አብዱላሂ
ምርጫ ክልል 26 – እንዳልካቸው ሌሊሳ
ሁሉም ከብልጥግና ሲሆኑ ፤
ምርጫ ክልል 28 – በግል ተወዳዳሪነት የቀረቡት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ናቸው።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.