Breaking News
Home / Amharic / የልዩ ኃይሎችን ትጥቅ መፍታት ውሳኔን በሚመለከት!

የልዩ ኃይሎችን ትጥቅ መፍታት ውሳኔን በሚመለከት!

ጉዳዩን ከሚደግፉ ወገኖች ውስጥ ነበርኩ! ነበርኩ ማለት አሁን አይደለሁም ማለት ነው፡፡ ለምንʔ
 
1ኛ ብልጽግና እንደ ስብስብ ሕዝብን በእኩል የማያይ፣ በብሔርና በሃይማኖትም በተለይ የኦርቶዶክስና የአማራን ጥፋት የሚሻ መሆኑን በግልጽ እያሳየ በመምጣቱ ነው፡፡
ይሄንንም ባለፉት አምስት አመታት አንድም እልቂታቸውን ባለማስቆም፣ እራሱም ደግሞ የሚገድልና የሚረሽን ሆኖ አሁን ደርሷል፡፡
2ኛ ኢትዮጵያውያንን በሃይኖትና በዘር ለይተው የሚጨፈጭፉ የሚያፈናቅሉ ኃይሎች ትጥቅ አልፈቱም፣ የበለጠ እየተጠናከሩ ነው፡፡
3ኛ እራሱ መንግሥት ከየአካባቢው፣ በተለይም በአዲስ አበባ ዙርያ የዘር ማጥፊያ ከተማ መሥርቶ የኢትዮጵያን ብዝኃነት እያጠፋ /በሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም ጉዳዩ ዘርን መሠረት ያደረገ መሆኑ መረጋገጠኑን ልብ ይልዋል/፣
መቶ ሺህዎችን እያፈናቀለ የዘር ማጥፋት ፕሮጀክቱን በይፋ እየተገበረ ነው፡፡
4ኛ አማራ የተባለውን ክልል በተለየ መልኩ ለማጥፋት እንደሚፈልጉ የብልጽግና ፖለቲካ ልሂቃን፣ በተለያየ ፓርቲ ስም ያሉ ግለሰቦች፣ በኦሮሞ ስም የሚነግዱ በዘር ማጥፋት ፍላጎት የተሳከሩ አክቲቪስቶች ወዘተ. እየዛቱና ያንኑ በተግባር እያሳዩ በመሆኑ፣
5ኛ መከላከያውን በጄኔራል ኢታማዦር ሹምነት የሚመሩት ሰውዬ ተtረኝነትን የሚደግፉ፣ ዘረኛ መሆናቸውን በይፋ በሚዲያና በስብሰባዎች ላይ የተናገሩ መሆናቸው መከላከያውና የፀጥታ መዋቅሮች ገለልተኛና አመራሩም ሕዝባዊ አለመሆኑ፤
6ኛ ውሳኔው በሁሉም ቦታ በተመሳሳይ ሰዓት የማይፈጸም መሆኑ፤ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ላይ ብቻ እየተፈጸመ መሆኑ የአማራውን ሕዝብ ለማጥፋት ሲዝቱ የኖሩትን ተግባራዊ ለማድረግ መጀመርያ መከታ ሊሆን የሚችል ኃይል የማሳጣት ግልጽ ተግባር በመሆኑ እና በዚህ ዘመን ዓይናችንን እያየ የሕዝባችን አካልየሆነን ሕዝብ ለማጥፋት የሚደረግን ድርጊት መደገፍ ስለማንችል / የልዩ ኃይሎች ደመወዝ መቋረጥ ካለበት በሁሉም ቦታ በተመሳሳይ መቋረጥ ሲኖርበት ተለይቶ አማራው ልዩ ኃይል ደመወዝ እንዲቋረጥ መደረጉ ይሄን ያጠናክራል/
7ኛ የሶማሌ ክልል አልሸባብ ያሰጋኛል እያለ፣ የአማራውም ክልል በተመሳሳይ በሕውሓት በኩል ስጋት አለብኝ እያለ፣ የትግራይ ክልልም የኤርትራ ኃይሎች አሁንም ሕዝባችንን የጎዱ ነው እያለ፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ እና የጋምቤላም ክልሎች ከደቡብ ሱዳን የተለያዩ ጥቶች አሉብን እያሉ በመንግሥት በኩል ለነዚህ ሁሉ ስጋቶች ጆሮ ዳባ ልበስ መባሉ
8ኛ ውሳኔውን ከሕብረተሰቡ ጋር በመወያየት ሁሉም አምኖበት ሳይሆን የብልጽግና ፓርቲ ባለሥልጣናት ብቻ ጉዳዩን ስለፈለጉት ብቻ ሊተገብሩት በመሆኑ፣
9ኛ ይሄንን ምክንያ አድርጎ መከላከያውን በየቦታው በመማገድ ከሕዝብ ጋር ሊያዋጉት፣ የሕዝብ ልጆች ሕዝብ ላይ እንዲተኩሱ ለማድረግ በመሆኑና
10ኛ ኢትዮጵያ ከነበረችበት አክሳሪ ጦርት ወደ ሌላ የማትወጣው የተራዘመ አክሳሪ እርስ በርስ ጦርነት እንድትገባ የሚያደርግ፣ ሥልጣንን ብቻ በማፍቀር የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑና በሌሎችም ምክንያቶች
ውሳኔውን በፍጹም አልደግፍም!!!
መከላከያ ሠራዊቱ እንደተቋም የእዝ ሰንሰለቱ በብልጽግና የተያዘ መሆኑን እናያለን አባላቱ ግን ሕዝባቸው ላይ ከመተኮስ ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው!
የፓርቲው ውሳኔ ሀገሪቱን የሚያፍርስ ነው!
ሀገሪቱ ከፈረሰች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚባልም አይኖርምና ሠራዊቱ ለራሱም ሲል የፖለቲካ ኤሊቱ የቤት ሥራውን በአግባቡ ያለመሥራቱ ዳፋ ሒሳብ ማወራረጃ እንዳይሆን ትእዛዝ ወደ አለመቀበል መሸጋገር መቻል አለበት!
የአምባገነኖች መጫወቻ መሆን የለበትም!

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.