Breaking News
Home / Amharic / ውሸት የተጠናወተውና ከሕዝብ የተጣላ መንግስት !

ውሸት የተጠናወተውና ከሕዝብ የተጣላ መንግስት !

#ግርማካሳ
ሕወሃቶች አስር ሺህ ገደልን ፣ ማረክን ወዘተ እያሉ ነው፡፡ ያው ሕወሃት ዜናዎች በመቶ እጥፍ ማጋነን የለመዱ በመሆናቸው ብዙ አያስደንቅም፡፡ 95% ያሉት ዉሸት ነው የሚል ግምት ነው ያለኝ፡፡ ነገር ግን ቢያጋንኑም 5% የሚሉትን ትንሽ እውነት እንዳለበት ግን የሚታወቅ ነው፡፡ አፍነው ወስደው የማረኳቸው ወታደሮች ይኖራሉ፡፡ አንድ ቪዲዮ አይቻለሁ “ከቦንጋ ነው የመጣሁት ፣ ስድስት ወር ነው የሰለጠንኩት” ያለች ወታደር ልብስ የለበሰች ወጣት ስትናገር፤፡
በኔ እይታ የአብይ መንግስት ትግራይ ስላለው ነገር ሕዝቡን እየዋሸ ያለ ነው የሚመስለኝ፡፡ አንደኛ በዚያ ጦርነት ካለ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከተማረኩ፣ አልተማረኩም ብሎ መዋሸት ለምን አስፈለገ፡፡ ጦርነት እኮ ነው፣ መሞትና መማረክ ያለ ነገር ነው፡፡ ይልቅ እውነታውን ተናግረው፣ ለአለም አቀፍ ማሀረሰብ ሕወሃት በአካባቢው ትልቅ ችግር እየፈጠረ፣ የመከላከያ አባላትን አሁንም እያፈነ መሆኑን ተናግረው ፣ ይሄን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ መነሳት ነው የነበረባቸው፡፡
በወላጋም እንደዚሁ ነው፣ ሸኔን ደመሰስን ብለው ይበጠረቃሉ፣ ግን ደግሞ ኦነግ በየጊዜው ችግር መፍጠሩ አላቆመም፡፡
የአብይ መንግስት ትልቁ ችግር ውሸት የተጠናወተው መንግስት መሆኑ ነው፡፡ እውነቱን ለሕዝብ ገልጾ፣ የሕዝብን ድጋፍ ከጎን አሰልፎ እነዚህን የአገር ነቀርሳ የሆኑትን ለመደምሰስ እርምጃዎች ካልተወሰዱ፣ አገር ሰላም አታገኝም፡፡ ሕወሃት በትግራይ ሕዝብ ላይ፣ ኦነግ በወለጋ ሕዝብ ላይ የመከራና የስቃ ናዳ እንዲወርድባቸው ነው እያደረጉ ያሉት፡፡ እነዚህ ቡድኖች የሕዝብ ጠላቶች ናቸው፡፡ መደምሰስ ያለባቸው፡፡
ሕዝብን ከጎን ለማሰለፍ ደግሞ፣ የሕዝብ መሰረታዊ የፍትህ የእኩልነት ጥያቄዎች ማክበር መጀመር አለበት፡፡ በምርጫው ትንሽ ወደዚያ ይኬዳል የሚል ግመት ነበር፡፡ ግን የአብይ መንግስት እንደውም የበለጠ ከሕዝብ የሚያጣላዉን አካሄድ ነው በምርጫው እያደረገ ያለው፡፡ ፒፒዎች በብዙ ቦታ ምርጫውን አጨማልቀዉታል፡፡
በኔ እይታ የአብይ መንግስት አካሄዱን ካልቀየረ፣ ግትርነቱና ጭፍንነቱን ወደ ጎን ካላደረገ ፣ ከሕወሃት የ100% ምርጫ ካልተማረ፣ እንኳን በትግራይና በወለጋ ያለው ችግር ሊፈቱ ቀርቶ፣ በሌሎች አካባቢዎች የተከያየ ችግሮች መፈጠራቸው አይቀርም፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ሁሉ ሳይቀር፡፡
በአንጻሩ ያሉ ችግሮችን ጠረቤዛ ላይ በማስቀመጥ፣ ብሄራዊ መግባባት እንዲኖር ከተሰራ፣ የአንድነት መንግስት ተመስርቶ በአገር አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ከተደረገ ሕወሃትን ሆነ ኦነግ በአንድ ጀንበር መደምሰስ በጣም ቀላል ነው የሚሆነው፡፡፡ ኦነጎችም ሕወሃቶች እንደዚህ ልብ ልብ የተሰማቸው አራት ኪሎ ያለው መንግስት በሕዝብ የማይደገፍና የተጠላ መሆኑን ስላወቁ ነው፡፡
በኮሎኔል መንግስቱ ጊዜ ሕወሃት በቀላሉ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና አዲስ አበባ የገባችሁ ሕዝቡ በደርግ በመማረሩ መሆኑ፣ ደርግ የህዝህብ ድጋፍ በማጣቱ መሆኑ ሊረሳ አይገባም፡፡

Check Also

ሰሎሞን ካሳ ማነው? Who is Solomon Kassa?

አንከር ሚዲያ እንደዘገበው .. ለማታውቁት ሰለሞን ካሳ ይባላል ., ወንጀለኛው የሆነው ይህ ሰው የህዝብ ድምፅ …

የአድዋ በአል በለንደን ከተማ በደማቅ ተከበረ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.