Breaking News
Home / Amharic / ወላጅ አባቴ ታደለ ፀጋዬ ከታሰረ ዛሬ 5ኛ ቀኑ ነው።

ወላጅ አባቴ ታደለ ፀጋዬ ከታሰረ ዛሬ 5ኛ ቀኑ ነው።

ብልግና አይቸግርም!

Christian Tadele Tsegaye (ገብርዬ)
*****
ወላጅ አባቴ ታደለ ፀጋዬ በቋሪት ወረዳ አመራሮች ታፍኖ ከታሰረ ዛሬ 5ኛ ቀኑ ነው። በወቅቱ ጉዳዩን ስሰማ ቀልድ መስሎኝ ነበር። ያው በስህተት ያሰሩትም መስሎኝ ነበር። በኋላ መረጃዎችን ሳጣራ ግን ቀልድም ስህተትም አልነበረም። ታስቦበት፤ ወርደው ሊያወርዱን ያጠመዱልን ወጥመድ መሆኑን ተረድቻለሁ። ለዚህም የወረዳው ም/አስተዳደሪና የአስዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆነው ግለሰብ (ስሙ ኤርሚያስ ባይነስ የሚባል) «እስኪ ልጅህ መጥቶ ሲያስፈታህ እናያለን» የሚል መዘባበቻ በ75 ዓመቱ አዛውንት አባቴ ላይ መሰንዘሩ፤ የወጥመዱን መነሻ ብቻ ሳይሆን የዚህ ሴራ ጎንጓኞች ግብንም ፍንትው አድርጎ አመላካች ነው።

ለመታሰሩ የቀረበው ሰበብ የመንግሥት መደበኛ ተግባር የሆነውን ሁከትን የማረጋጋት ሥራ በአገር ሽማግሌነቱ መስራቱ መሆኑ ደግሞ የበለጠ ገራሚ ነው። የብልግናችሁን ጥግ፤ ነውራችሁንም አዝማሪዎቻችሁ እንዲያውቁት ጭምር እንጂ ለእኔስ ወላጅ አባቴ ታደለ ፀጋዬ ላይ ያደረጋችሁት ሁሉ በሌላው አማራ ያደረጋችሁትና የምታደርጉትም ስለሆነ ድንቄም አይደለ! ፍትኅን ከጨቋኝ ሊያውም ከጃንደረባ መለመን ለነውራችሁ እውቅና መስጠት ነው። ብቻ ግን አንዳችስ እንኳ የሞራል ተጠያቂነት እንደሌለብኝ እንድታውቁት ይሁን።

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.