Breaking News
Home / News / ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

*****
ዛሬ ሰኔ 15/2011 ዓ/ም ምሽት በባሕር ዳር ከተማ የተከሰተውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ፣ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል። እስከዚህ ሰዓት ድረስ የተረጋገጠ መረጃ ማግኝት ባንችልም፣ ከባሕር ዳር የሚወጡ መረጃዎች አሳዛኝ እና መንፈስን የሚያውኩ ሁነው አግኝተናቸዋል። አብን ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን፣ ሕዝባችን በተለመደው አስተዋይነቱ እና ጨዋነቱ ያጋጠመንን ፈተና እንደሚወጣው ያለንን ሙሉ እምነት እየገለጽን፣ አጋጣሚውን ተጠቅመው የሕዝባችንን አንድነት ከሚፈታተኑ ኃይሎች የጥፋት ተልዕኮ እራሱን እንዲጠብቅ፤ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና አክቲቪስቶችም ሕዝብን የማረጋጋት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን በአግባቡ እንድትወጡ፤ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እጣ ፈንታችንን በራሳችን እጆች እንጽፋለን!

ተጨማሪ፦ በብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተመራ ክልላዊ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ መደረጉን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስታወቀ። የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራው መክሸፉን የክልሉ ገዢ ፓርቲ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአማራ ቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

Ethio 360 Media
ሰበር ዜና
በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ግቢ ውስጥ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተነገረ::
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አምባቸው መኮንን እና የአዴፓ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ምግባሩ ከበደ ክፉኛ ቆስለዋል ተብሏል::
ጥቃቱን ያደረሱት በጄኔራል አሳምነው ፅጌ የሚመሩ ልዩ ሀይሎች ናቸው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልፀዋል::
የክልሉ ምክር ቤት በታጣቂዎች እንደተያዘ መሆኑ ቢነገርም የፌዴራል መንግስት ሀይሎች አካባቢውን መክበባቸው ተነግሯል::
የጠቅላይ ሚንስትር የፕሬስ ሴክረታሪ ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለመንግስት መገናኛ ብዙሀን በአማራ ክልል የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተካሂዶ ከሽፏል ብለዋል:: ስለደረሰው ጉዳት ግን ያሉት ነገር የለም::

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.