Breaking News
Home / ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል (FANO) የተሰጠ መግለጫ!!

ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል (FANO) የተሰጠ መግለጫ!!

ቢዘገይም ፍላጎታችንና መሆን ያለበት እየሆነ ነው እናመሰግናለን ጀግኖቻችን💪💪💪❤
ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል የተሰጠ መግለጫ!!
×××××××××××××××××××××××××××
የአማራ ህዝብ ከፊትለፊቱ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ በመግስታዊ መዋቅሩ አማካኝነት ማስቆም የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ መንግስት ተደጋጋሚ የክተት ጥሪዎችን ማስተላለፉ ይታወቃል። ሆኖም ህዝቡ በተደረገለት ጥሪ የህዝቡን አቅም የሚመጥን ምላሽ ባለመስጠቱ የችግሩ ስፋት እና የወራሪወች እንቅስቃሴ በየዕለቱ እየሰፋ መጥቷል።
በዚህም ምክንያት ህዝቡን በተለይም የአማራን ወጣት በገፍ የሚያንቀሳቅስ ወታደራዊ ብቃት እና ፖለቲካዊ ንቃት ለህዝቡ ማስታጠቅ እና ማታገል የሚችል አዲስ አደረጃጀት መፍጠር ለነገ የማንለው የቤት ስራ ሆኗል።
በመሆኑም ዛሬ ነሃሴ 06 ቀን 2013 ዓ.ም በፍኖተ ሰላም ከተማ በተካሄደ ጉባኤ ከላይ የተጠቀሰውን ዓላማ ከግብ ያደርሳል ያልነውን ህዝባዊ ኃይል መስራች ጉባኤ አካሂደናል። በእኛ እምነት በስፋትም ሆነ በጥልቀት ወቅቱን ይመጥናል ያልነውን አደረጃጀት ፈጥረናል።
በዚህ መሰረት፡-
በአርበኛ ዘመነ ካሴ ሰብሳቢነት እና በካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ምክትል ሰብሳቢነት የሚመራ ሰባት ቋሚ እና አራት ተጠባባቂ የስራ አስፈጻሚ አባላት ያሉበት የአማራ ህዝባዊ ኃይል አደረጃጀትን በታላቅ ወኔ እና ተነሳሽነት አዋቅረናል።
መዋቅሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች የሚመሰረት መሆኑን አውቃችሁ በየወረዳው የተሻሉ እና የበቁ ልጆችን እያዘጋጃችሁ እንድትጠብቁን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በመስራች ጉባኤው የተገኙ የየወረዳ ተወካዮች በሁሉም ወረዳዎች የሚፈጠረውን አደረጃጀት እንዲመሩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል። ወጣቶች የየወረዳ አደራጆችን በቅንነት እንድትተባበሩ እና ራሳችንን ለማስከበር ህዝባችንን ከጥቃት ለመከላከል ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ተጋድሎ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁን እና ጥሪ ስናደርግላችሁ እንድትከቱ ፥ ይፋ በምናደርጋቸው ቦታወች ያለምንም ማመንታት እንድትገኙ በታላቅ አደራ ጥሪ እናስተላልፋለን።
ኮሚቴዉ በሚያስተባብረው መሰረት እድሜውና ጤናው የሚፈቅድለት አማራ በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ በየወረዳ ማእከሉ እየተመዘገበ ህዝባዊ ሃይሉን በመቀላቀል ቀጣይ ጥሪዎችን ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪያችን እያስተላለፍን በቀጣይ ቀናት ዘርዘር ያለ መግለጫ ከስራ አስፈጻሚው እንደሚሰጥ በአክብሮት እንገልጻለን።
የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን በተግባር እናሳያለን!
ድላችን በህብረታችንና በክንዳችን!!
Betelhem Dagnachew Zewde

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.