Breaking News
Home / Amharic / ከአማራ ህዝብዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ ! ይህን መልእክት ለአማራ ሕዝብ እንዲደርስ አድርጉ !

ከአማራ ህዝብዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ ! ይህን መልእክት ለአማራ ሕዝብ እንዲደርስ አድርጉ !

ከአማራ ህዝብዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

 

የአማራ የውርደት ዘመን የሚያበቃበት ጊዜ አሁን ነው!

 

በጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ እና በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ላይ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ጥሪ

 

ሚያዚያ 9, 2015
የተከበርከው የአማራ ሕዝብ:-
ባሳለፍነው ሳምንት የአማራ ሕዝብ በአብይ አህመድ፣ በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ እና በባህር ዳር በሚገኙ በኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ የአማራ ተላላኪዎች የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም የአማራ ክልል ልዩ ሃይልን ለመከላከል፣መዲናችን አዲስ አበባ እንዳንገባ የተደረገው እገዳ እንዲቆም፣የፖለቲካ እስረኞችን እና ጀግኖቻችንን እንዲፈቱ በሚሊዮኖች ተነስተን ድምፅ አሰምተናል። ቁጣህን ለአለም አሳይተሃል፥ ገዥው ቡድን ምን ያክል አንደተርበሸም አይተሃል።
የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ክልሉን ከትህነግ፣ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ) ሲጠብቅ ከርሟል። የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ለአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ወሳኝ ሆኖ ቆይቷል። አብይ አህመድ ፣ የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ እና በባህርዳር የሚገኙት አሻንጉሊቶቻቸው የህዝቡን የጸጥታ ምሰሶ ነቅለዋል።
የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በርካታ የአማራ አርበኞችን በሸዋ ሮቢት ከተማ ጨፍጭፈዋል።መከላከያ ሠራዊት እና አጋሮቻቸው በመንገድ ላይ የነበሩ በርካታ የአማራ ልዩ ሃይሎችን ገድለዋል።
የጀግኖቻችንን መስዋዕትነት እያከበርን ለቤተሰብ እና ወዳጆቻቸው ሀዘናችንን እንገልፃለን። ገዳዮቻቸው ፍትህ እስኪያገኙ ድረስ በፅናት አንታገላቸዋለን::
የአብይ መንግስት ይህንን የጸጥታ እጦት በመጠቀም የወልቃይት፣ የጠለምት እና የራያ ታሪካዊ መሬቶቻችንን ለትህነግ ሊሰጥ ዝግጅት ጨርሷል። በተጨማሪ የኦሮሙማ ገዥ ቡድን ታሪካዊ መሬቶቻችንን አጣዬ እና ሸዋ ሮቢት ለራሱ ሊወስድ እየሞከረ ነው። የኦሮሙማ ገዥ ቡድን እና አጋሮቹ ሁላችንንም ሊያስጨርሱን እና እንደ ህዝብ ሊያስወግዱን ቆርጠው ተነስተዋል::
የአማራ የውርደት ዘመን የሚያበቃበት ጊዜው አሁን ነው። ይህ ወቅት ለፋኖ አርበኞቻችን እና በመላው አለም ለሚገኙ አማራዎች ታሪካዊ እና ወሳኝ ጊዜ ነው። ፋኖ ትጥቅ አትፍታ! የአማራን ህዝብ ጠብቅ! ጨቋኞችን ሁሉ ያሸነፈ ኩሩ የተከበረ ታሪክ አለን። ታሪካዊ ባህላችንን በማደስ ህዝባችንን፣ መሬታችንን፣ ባህላችንን፣ ታሪካችንን እና ማንነታችንን ከወራሪዎች ለመጠበቅ በአንድ ላይ የምንነሳበት ጊዜ አሁን ነው።
በመሆኑም መላው የአማራ ሕዝብ ከዚህ በታች ያሉትን እርምጃዎች በአስቸኳይ እና በቋሚነት እንዲወስድ እንጠይቃለን።
1. ገንዘብህን በሙሉ ከመንግስት ባንኮች ወደ ግል ባንኮች አስገባ።
2. ለአብይ መንግስት እና ለተላላኪዎቹ ግብር መክፈልህን አቁም።
3. የብአዴን፣ የብልፅግና ካቢኔ አባላት፣ የብአዴን ኮሚቴ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በመደወል የአብይ እና የኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ አሻንጉሊት በመሆናቸው እራሳቸውን እና የአማራን ህዝብ ነግራችሁ ገስጿቸው። በአማራ ላይ የያዙትን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቀጥሉ መፍቀድ የለብንም። ከማንኛውም ማህበራዊ እንቅስቀሴዎችና ግንኙነቶች አግልሏቸው።
4. በመንግስት ከተያዙ ንግዶች እና መንግስትን ከሚደግፉ የንግድ ድርጅቶች ምንም አይነት አግልግሎት አትጠቀሙ::
5. በመንግስት ባለቤትነት የተያዙ ሚዲያዎችን፣ ባለስልጣናትንና ደጋፊዎቻቸውን በማህበራዊ አውታር መደቦች መከተል አቁሙ።
6. ከማንኛውም የመንግስት ሚዲያዎች እና ለመንግስት ሚዲያ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ዝግጅቶች ላይ ከመሳተፍና ቃለመጠይቅ ከመስጠት ተቆጠቡ።
7. በአማራ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የመንግስትን ፕሮፓጋንዳ የሚያራምዱ ፕሮግራሞችን እንዳያዘጋጁ የራሳቸውን ህዝብ በሚዲያ ከማዋረድ እንዲቆጠቡ ጥሪና ግፊት በማድረግ ገስጿቸው።
ዲያስፖራ አማራውዎች የአማራ ህዝብ ወዳጆች:-
8. በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ የአማራ ተላላኪዎች የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመቃዎም የአደባባይ ሰልፎችን በማድረግ ለህዝባችሁ ያለመታከት ድምፅ ሁኑ። በአብይ መንግስት ላይ ማእቀብ እንዲጥሉ ጠይቁ
9. ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ለመላክ የመንግስት ቻናል አይጠቀሙ። የአብይ መንግሥት ላይ ማእቀብ ጣሉ። ዶላታችሁ አብይ ከእናንተ አንድ የሚፈልገው ነገር ነወ።። በእርሱና በኦሮሙማ አገዛዙ አንድ ያለለችሁ ወሳኝ መሳሪያ ነው።
10. በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ማዕቀብ ጣሉ። በግልም ሆነ በመስሪያ ቤት ለሚደረጉ ጉዞውች የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከመጥቀም ታቀቡ።
አመራሩ ተጨማሪ የሚወሰዱ እርምጃዎችን የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በዓል ካከበሩ በኋላ ያሳውቃል::
የአብይ አህመድና ተላላኪዎቹ አገዛዝ መውደቁ የማይቀር ነው። በህብረታችንም ውድቅቱን በአጭር ጊዜ እውን እንዲሆን እንሰራለን።

የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ አመራር

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.