Breaking News
Home / Amharic / ኦሮሚያ ዉስጥ የሚካሄደዉ ጀኖሳይድ ሊቆም አይችልም!

ኦሮሚያ ዉስጥ የሚካሄደዉ ጀኖሳይድ ሊቆም አይችልም!

written by: Miky Amhara
 
ኦሮሚያ ዉስጥ የሚካሄደዉ ጀኖሳይድ ሊቆም አይችልም ምክንያቱም፤
 
1. በተለይም ጨለማን ተገን አድርጎ የኦሮሚያ መንግስት የሚያካሂደዉ ጭፍጨፋ በመሆኑ መቼዉንም አይቆምም፡፡
2. የኦሮሞ ኢሊቶች፤ አክቲቪስቶች እና ፖለቲከኞች እስከዛሬዋ ድረስ ህዝባቸዉን ሞቢላይዝ እያደረጉት ያሉት በየአካባቢዉ አማራዉን ጠላት አድርገዉ እንዲያዩት በመሆኑ ጭፍጨፋዉ አይቆምም፡፡
3. አይደንቲቲ ሁሌም ቢሆን የሚሰጥህ እና ዲፋይን የሚያደርግልህ የሚገድልህ ጠላትህ ነዉ፡፡ አማራ አይደለሁም ብትለዉም ገዳይህ ዲፋይ አድርጎሃል፡፡ ከአካባቢዉ ባህል ጋር አሲሚሌት ማድረግም ሆነ ወይም በፖለቲካዉ ፓሲቭ መሆን ለጀርመን ጀዉሾች፤ ለሩዋንዳ ቱትሲዎች፤ ለአዘር ባጃኖች አልሰራም፡፡ በ50 እና በ100 ግድያዎች ተነስቶ ቀስ በቀስ እስከ ስድስት ሚሊየን የጅምላ ግድያ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ ኦሮሚያ ዉስጥ ያለዉ አማራ በፖለቲካዉ ፓሲቭ ቢሆንም ማንነቱንም ለመቀየር ቢሞክርም ከመታረድ አልዳነም፡፡
ከዚህም በመነሳት የህዝብ እልቂትን ለመታደግ ከፍተኛ ችግር ያለባቸዉን እና ሪሞት የሚባሉትን እንዲሁም ለተደጋጋሚ ጥቃት ተጋላጭ አካባቢዎች የሚኖረዉን ህዝባችን ማንቀሳቀስ እና ማስፈር (population transfer) አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ህይወትንም መታደግ ነዉ፡፡
Population transfer በተለያዩ ሀገራት ጥቅም ላይ የዋለ እና የህዝቦችን ህይወት የታደገ ነዉ፡፡ ለምሳሌ
1. ኦሮሚያ ክልል ትልቁ ድክመቱ የነበረዉን እስከ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጋ ኦሮሞወች ከሶማሌ ክልል የተወሰኑ ቦታዎች ላይ በማስወጣት ዛሬ ላይ የተሻለ ሰላም አላቸዉ፡፡ ቢያንስ የሚገደል ህዝብ የለም፡፡
2. የሶማሌ ክልልም ከ 50 ሽህ በላይ የሚሆኑ ከኦሮሚያ ሁለት እና ሶስት አካባቢዎች በማስወጣቱ ከጭፍጨፋ አድኗቸዋል፡፡
3. በሰሜን ናይጀሪያ ኢቦዎች ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በተደጋጋሚ ሲካሄድ የሀገሪቱ መንግስት ከ 1ሚሊየን በላይ የሚሆኑትን በሰሜኑ ክፍል ይኖሩ የነበሩትን ወደ ሌላ አካባቢ አንቀሳቅሷል፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ለጄኖሳይድ የቀረበ ጭፍጨፋ አላጋጠማቸዉም፡፡
4. የታሚል ዘር የሆኑ በሲሪላንካ ከተማ ኮሎምቦ አካባቢ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በየጊዜዉ ሲያጋጥማቸዉ በመቶሽዎች የሚቆጠሩት ወደ ሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተዛዉረዋል፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ለጄኖሳይድ የቀረበ ፍጅት አላጋጠማቸዉም፡፡
5. በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሰርቦች ከስሎቬኒያ እና ክሮሽያ ክፍለግዛቶች በመዉጣት ህይወታቸዉን አትርፈዋል፡፡
6. እስከ ሁለት ሚሊየን የሚደርሱ ጀርመኖች ከኢስተርን ኢሮፕ ሀገሮች በመዉጣት ከጭፍጨፋ ድነዋል፡፡
7. ከ 2 ሚሊየን በላይ ራሽያዎች በ1990ዎቹ ከተገነጣጠሉት ሀገራት ወደ ራሽያ ግዛቶች ገብቶ በማስፈር ከጭፍጨፋ ተርፈዋል፡፡
8. 200 ሽህ ሃንጋሪዎች ከሰርቢያ አንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በመስፈር ከጅምላ ግድያ ተርፈዋል፡፡
9. ቡልጋሪያ፤ ግሪክ፤ ቱርክ ዉስጥ በየጊዜዉ የሚረጉ ዘርን መሰረት ያደረጉ ጭፍጨፋዎች አንዱን ወደ አንዱ በማስፈር ዘር ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋን አስወግደዋል፡፡
በመሆኑም በተደጋጋሚ እና ከፍተኛ ችግር የሚያጋጥምበትን አካባቢ በመለየት በተለየም በምእራብ ወለጋ ህዝባችን ከአካባቢዉ የማስወጣት ስራ መስራት አስፈላጊ ነዉ፡፡ ከእነዚህ አካባቢዎች የሚወጡትን ለከተሞች ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች ማስፈር፡፡ ለአዲስ አበባ ቅርብ በሆኑ እንደ ሰሜን ሽዋ አካባቢ ባሉት ዙሪያዎች ማስፈር፡፡ ወንዝ ያለበት አከባቢ ማስፈር፡፡ በተለይም መጠነኛ ግድቦች የሚሰሩባቸዉ እና በትንንሽ መሬት በአመት ሶስት እና አራት ጊዜ የሚያመርቱብት አካባቢ ማስፈር፡፡ ሰፋፊ ቦታዎች እና ከፍት የእርሻ መሬቶች ያሉበት አካባቢ ማስፈር ለምሳሌ ቋራ አካባቢ፤ ጃዊ፤ ምእራብ ጎንደር፤ ማእከላዊ ጎንደር (ዳንሻ ወልቃይት)፤ ወልደያ አካባቢ እና የመሳሰሉት፡፡
ባለሃብቱ ተባብሮ በ10 ሽህ የሚቆጠሩ ቤቶችን በመስራት እንዲያግዝ ማድረግ አስፈላጊም ከሆነ ለአመት እና ለሁለት አመት ብቻ የሚቆይ ልዩ የገቢ ግብር በመጣል ለዚሁ ተግባር ማዋል፡፡
እኛም ባናጓጉዛቸዉ አሁን ላይ በዱር በገደል እያሉ ግማሹ እየሞተ፤ ግማሹ እየቆሰለ፤ ንብረቱ ተበትኖ እየወጡ ነዉ ያሉት፡፡ ይሄን ለ 40 አመት ማስቆም ካልቻልን እነዚህ ለተደጋጋሚ ጭፍጨፋ ተጋላጭ የሆኑትን በመምረጥ በስርአቱ ከእነ ሃብት ንብረታቸዉ ማጓጓዝ ዉጭ ሌላ መፍትሄ የለዉም፡፡ ከዚህ ዉጭ ጨፍጫፊ መንግስት ላይ የቱም ያህል ጫና ብታደረግ ሊያቆም አይችልም፡፡
ለህዝባችን ሀገር እናወርሳለን ብለን ሞትን ልናወርስ አይገባም!

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.