Breaking News
Home / Amharic / እንታረቅ ብለው ጠርተው አሰሩት ! ይሄ መንግስት እንዴት ይታመናል?

እንታረቅ ብለው ጠርተው አሰሩት ! ይሄ መንግስት እንዴት ይታመናል?

መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን በተመለከተ ከክልሉ መንግስት እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ለሳምንታት በተደረገ ውይይት ግለሰቡ በሰኔ 15 ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንደሌለው ተረጋግጦ እና ስምምነት ላይ ተደርሶ ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ባህር ዳር መጥቶ ነበር።
ጉዳዩን በጉጉት ሲጠብቀው ለነበረው የአማራ ህዝብ ለማሳወቅ ተዘጋጅተን ሳለን ቃሉን ሰጥቶ ይመለሳል በሚል ሰበብ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰደ በኋላ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርቦ ግዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት በእስር ላይ ይገኛል።

በዚህ የሽምግልና ሂደት ቤተ-ክርስቲያን ተሳትፋለች። የሀገር ሽማግሌወችም ደክመዋል። ለግዜው ዝርዝር ጉዳዩን ከመግለፅ ተቆጥበናል። መንግስታዊ ክህደት የሚያስከትለው ውርደትን ብቻ ነው። የከፋ ችግር ከመከሰቱና ወደ አለመረጋጋት ከመሄዱ በፊት መንግስት በአስቸኳይ መፍትሔ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን።

ቃል ይከበር!!

SUPPORT FANO

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

One comment

  1. የአማራን ህዝብ ካለበት ፈታኝ ሁኔታ አውጥቶ ለሁለተናዊ ስኬት ለማብቃት ከእውነት ጋር እንቁም!!

    https://amharic.borkena.com/2020/05/25/የአማራን-ህዝብ-ካለበት-ፈታኝ-ሁኔታ-አውጥ/

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.