Breaking News
Home / Amharic / ኢዜማ ከንቲባ ታከለ ኡማ ወንጀል ሰርተዋል ሲል በደሎችን በመዘርዘር መግለጫ አውጥቷል።

ኢዜማ ከንቲባ ታከለ ኡማ ወንጀል ሰርተዋል ሲል በደሎችን በመዘርዘር መግለጫ አውጥቷል።

ይቅርታ የጎደለው የኢዜማ ጥሩ አቋም !
********************************
ኢዜማ ከንቲባ ታከለ ኡማ ህግን ከለላ በማድረግ ወንጀል ሰርተዋል ሲል በህዝብ ላይ የፈፀሟቸውን በደሎች በመዘርዘር መግለጫ አውጥቷል።

ኢዜማ በመገለጫው ተዘርዝረው የቀረቡት ወንጀሎችም ሆኑ መግለጫው ያላከተታቸው የወንጀል ድርጊቶች በከንቲባው ሲፈፅሙ በወቅቱ የነበረውን የህዝብ ድምፅ በማጣጣል ለከንቲባው ገፅታ ግንባታ መስራትን እንደ ትክክለኛ የፖለቲካ አቋም ወስዶ በይፋ ለወንጀል ድርጊቱ በመሪው በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በኩል ከለላ ሲሰጥ እንደነበረ ይታወቃል።

ዶ/ር ብርሃኑ ከንቲባ ታከለ ሲሾም የህግ ጥሰት መፈፀሙን የተቃወምን ሰዎችን ሲያወግዙ፣ ለኦሮሞ ብልፅግና “የዴሞግራፊ ቅየራ” ፕሮጀክት መታወቂያ ሲታደልም ሆነ የኮንደሚንየም ዘረፋ ሲፈፀም በይፋ በሚዲያ ቀርበው ፓርቲያችን ባለው መዋቅር አጣርቷል ተራ አሉባልታነው ታከለ አሻጋሪ ነው በማለት እስክንድር ነጋን ሲኮንኑ እንደነበረ ይታወሳል።

የሆነው ሁሉ ሆኖ ዛሬ በኢዜማ በኩል ሁለት አመት ያረፈደው መግለጫ “ታከለ ኡማ ወንጀል ሰርተዋል” ብሎ ሲኮንን የፓርቲው መሪ ዶ/ር ብርሃኑ እራሳቸውን ከመግለጫውም ከአካባቢውም ዘወር አድርገዋል።

ፓርቲውም ዛሬ የታከለ ኡማን ወንጀል በመግለጫ ከመዘርዘር በቀር ፓርቲው ለወንጀል ሰሪው ከንቲባ ሽፋን ሲሰጥ መቆየቱንም ሆነ ይህ ወንጀል እንዳይፈፀም ሲከላከሉ የነበሩትን እንደ ጠላት ቆጥሮ ማብጠልጠሉን በመጥስ በአንድ መስመር ይቅርታ አልጠየቀም።

ለማንኛውም “ማርፈድ ከመቅረት ይሻላል” የፓርቲው መሪ ግን ከመደበቅ ይልቅ አሁንም የታከለን ድርጊት በይፋ ቢያወግዙ፣ ለወንጀሉ ሽፋን በመስጠት በአዲስ አበባ ህዝብ እና በባልደራስ ላይ ለፈፀሙት በደል ይቅርታ ቢጠይቁ መልካም ይመስለኛል። በደሉ ህዝብ ደም እንባ እያስለቀሰ ያለ የተረኞች የግፍ ግፍ ነው።

ኢዜማ በመግለጫው ያካተታቸው የታከለ ኡማ ወንጀሎች
**********************************************

1. ኢፍትሐዊ ሕጎችን እና መመሪያዎችን በማውጣት እና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሕጎችን እና ደንቦችን በማሻሻል ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢፍትሐዊ በሆነ መልኩ ፈጽሞ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤት የማስተላለፍ ተግባር እንደፈፀመና እየፈጸመ መሆኑን አረጋግጠናል።

2. ለ32,653 የ20/80 ተመዝጋቢ እድለኞች እና 18,576 የ40/60 ተመዝጋቢ ዕድለኞች ዕጣ የወጣላቸው እድለኞች በሕጉ መሠረት በፍጥነት እንደሚተላለፍ ሙሉ ቃል የተገባ ቢሆንም ። ውስጥ ለውስጥ ለራሳቸው አባላት፣ ለሹማምንቶች፣ ለማይታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች ታድለዋል።

3. ኢ/ር ታከለ በ13ኛው ዙር ዕጣ አወጣጥም ሥነ ሥርዓት
ከ15,000 በላይ የ40/60 ተመዝጋቢ ነዋሪዎች ውስጥ 90,000 ቤቶች ለቀሩት እና ከ32,000 የ20/80 እድለኞች በሙሉ የማስተላፍ ሥራ እንደተጠናቀቀ የተናገሩት እውነት አልነበረም፡፡

4. የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ከአሁን ቀደም በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ቦታ እና ኮንዶሚኒየም የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ድጋሚ በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየታደላቸው ነው ፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የድልደላ እጣ የወጣላቸው ሲሆን፣ የድልድል እጣ ለደረሳቸው ሰዎች ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ድልደል ተደርጎላቸዋል፡፡ በተሰጣቸው የቤት ቁጥር የነዋሪነት መታወቂያ ተዘጋጅቷል ።

5. የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንጻዎች ውስጥ የተሠሩ የንግድ ቤቶች በተመለከተ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ፣ ልጅ እና የልጅ ልጅ ተብለው በገፍ ስለመታደላቸው፤ በእግር ኳስ ደጋፊነት ስም ለተሰባሰቡ ማኅበራት ተከፋፍሏል ።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.