Breaking News
Home / Amharic / አዲስ አበባ ዉስጥ ከኦሮሞ በስተቀር ማንም ሥራ እንዳይቀጠር የሚሰራዉን ተንኮል ተመልከቱ።

አዲስ አበባ ዉስጥ ከኦሮሞ በስተቀር ማንም ሥራ እንዳይቀጠር የሚሰራዉን ተንኮል ተመልከቱ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ለሥራ ቅጥር ማሟላት ያለብንን መስፈርት አሟልተን ፈተናውን ብናለፍም ተጨማሪ ቋንቋ አትችሉም በሚል ቅጥር ሳይፈፀምልን አራት ወር ሞላን ሲሉ በባልደራስ ፅ/ቤት ተገኝተው ቅሬታቸውን ያቀረቡ አመልካቾች ገለፁ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ህዳር 2 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሙሉ ክፍት ቦታዎችን በቅጥር ለሙላት በሚል በ 2010 አና 11 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎችን በዜሮ አመት ለመቅጠር ባወጣው መስፈርት መሰረት የአዲስ አበባ መታወቂያ ያላቸውን ማወዳደሩ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚሉት ከሆነ መስፋርቱን አሟልተን ፍተናውን ተፈትነን ከማለፊያ ውጤት በላይ አስመዝግበን የነበረ ቢሆንም ተጨማሪ ቋንቋ አትችሉም በማለት ከኛ ውጤት በታች ያመጡ አካላትን ቀጥረው አኛን ሳያካትቱን ቀርተዋል።

ይህ ጉዳይ ትክክል እንዳልሆነ ለከተማው የሰው ሃብት ልማት ገልፀን ከማለፊያ ወጤት በላይ አምጥተን ለምን እንዳልተቀጠርን ስንጠይቅ በስህተት መሆኑን ገልፀው አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ በሁለተኛው ዙር እንደሚቀጥሩን ቢገልፁም እስካሁን ድረስ ምንም የተተገበረ ነገር የለም ብለዋል።

ለምን አራት ወር ሞላው በሚል ቅጥር እንዲፈፅሙልን በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ የስው ሃብት ልማት ቢሮ በተደጋጋሚ አቤቱታ ብናቀርብም ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የግል ስብዕናችንን በሚነካ መልኩ ይዘልፉናል ብለዋል።

የሥራ ቅጥር አስፈጻሚዎቹ በመስሪያ ቤቱ የሚሰሩ አካላት የሚያናግሩን በማንችለው ቋንቋ ነው። በዚህም ልንግባባ አልቻልንም። የኛን ስም ዝርዝር እና የቅጥር ማስታወቂያ ተገን በማድረግ የራሳቸውን ሰዎች እየቀጠሩ ነው በማለት ቅሬታቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም እኛ የአዲስ አበባ ተወላጆች ተገፍተን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መመሪያ መታወቂያ በህገወጥ መንገድ እየተሰራላቸው ከክፈለ ሃገር የሚመጡ አማርኛ ቋንቋ መግባባት የማይችሉ አካላት ቅድሚያ እየተቀጠሩ ይገኛል ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ይህንን ጉዳይ ኢቲቪን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ላይ ባካል ቀርበን ብናሳውቅም ድምፃችንን አፍነውታል።
በመሆኑም በአዲስ አበባ ህዝብ ሆን ተብሎ የሚደርሰዉን በደል እንድታሳውቁልን በማለት ጠይቀዋል።

ስንታየሁ ቸኮል

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.