Breaking News
Home / News / አቶ ክርስቲያን ታደለ ላይ የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ተጨማሪ 10 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ፤

አቶ ክርስቲያን ታደለ ላይ የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ተጨማሪ 10 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ፤

★★★

ከሰኔ 15ቱ የአማራ ሕዝብ መሪዎች እና የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮነኖች ግድያ ጋር በተያያዘ ጠርጥሬቻዋለሁ በሚል ለ2 ጊዜ 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የድርጅታችን አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ጳጉሜ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ለ5ኛ ጊዜ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ፖሊስ ከአሁን ቀደም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸውን ምክንያቶች በመጥቀስ ለ3ኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጠን ይገባል ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ጠበቆቻቸው በበኩላቸው ለፖሊስ በተሰጠው 56 ቀናት ውስጥ በደንበኛቸው ላይ ምንም አይነት ተጨባጭ ነገር አለማቅረቡንና መቅድሙ ላይ አቃቢ ህግ ደንበኛቸውን በተመለከተ ያከናወነውን ዝርዝር ተግባራት ለይቶ አለማስቀመጡን በመጥቀስ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቀድለት አይገባም፤ ከተጠረጠሩበት ሽብር ወንጀል ጋር የሚገናኝ ማስረጃ ፖሊስ ባለማቅረቡ ተጠርጣሪው በነፃ ሊለቀቅ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ የምርመራ መዝገብንና የግራ ቀኙን ክርክር በማየት ተጨማሪ የምርመራ ቀን ለፓሊስ ሊሰጥ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሰረትም ዛሬ ፓሊስ የምርመራ መዝገቡን ይዞ ቀርቦ ክርክር የተደረገበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ከጠየቀው 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ 10 ቀን ብቻ በመፍቀድና ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ እንዲያቀርብ በማዘዝ ለመስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.