Breaking News
Home / Amharic / አቶ ብናልፍ አንዷለም (የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ሀላፊ) ፋኖን አትደግፉ አሉ !

አቶ ብናልፍ አንዷለም (የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ሀላፊ) ፋኖን አትደግፉ አሉ !

ዘማቾችን በተመለከተ – ከብናልፍ አንዷለም 

አሸባሪው ህወሓት አማራ እና አፋር ክልሎችን በመውረር ያለ የሌለውን የህዝብ እና የመንግሥት ሀብት እየዘረፈ፣ ዜጎችን እየገደለ፣ ሴቶቻችንን እየደፈረ ነው። ይሄን አሸባሪ ኃይል ወደ መጣበት ለመመለስ ሁሉም የመንግሥት የጸጥታ አካላት ርብርብ እያደረጉ ሲሆን ህዝባችንም በተለይ ወጣቱ በቡድን በቡድን እየሆነ ግንባር በመግባት እየተፋለመ ነው። የአፋር ህዝብ ወጣት አዛውንት ሳይል በክልሉ ልዩ ኃይል ስር በአንድ ተንቀሳቅሶ ጠላቱን እየመከተ ነው። በአማራ ክልል በኩልም ገበሬው እና ወጣቱ በተመሳሳይ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተናበው እየሰሩ ነው። ሆኖም በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ጥቂት ግለሰቦች ለግል ጥቅማቸው ሀብት ለማሰባሰብ ይሁን በሌላ ምክንያት ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ የሆነ ታጣቂ ኃይል እያደራጀን ነው በማለት ውዥንብር እየፈጠሩ መሆኑ ታውቋል። በዚህ የህልውና ዘመቻ ምክንያት በየሰፈሩ የጎበዝ አለቃ ለመሆን የሚደረግን ሙከራ መንግሥት አይታገስም። በመንግሥት ቁጥጥር ስር ሆኖ በመከላከያ ሰራዊት የእዝ ተልዕኮ ስር የማይሆን የትኛውም ታጣቂ ከየትም ይምጣ ከየት ወደ ግንባር እንዲገባ አልተፈቀደም። ወደፊትም ቢሆን የመንግስትን ሚና ለመተካት የሚደረግ ሙከራ ህገወጥ ተብሎ ብቻ የሚታለፍ ሳይሆን እንደ ከፍተኛ የሽብር ወንጀል የሚቆጠር ስለሆነ ወጣቶች ያለመንግስት አካል ፈቃድ እና እውቅና በየሰፈሩ ወታደራዊ ስልጠና እንስጥ እና በእኛ ስር ተደራጁ ከሚሉ አካላት በመራቅ ለራሳችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። በየአካባቢው ያላችሁ የመንግሥት አካላት ከእናንተ እውቅና ውጪ የሆነ የጸጥታ አደረጃጀት ለመስራት የሚደረግን ማናቸውም ሙከራ በማስቆም ኃላፊነታችሁን በአግባቡ እንዲትወጡ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
 
  • ፈቃዱ ምሥራቅ

    አንተ ከዳሚ ተላላኪ!! አንተና ቢጤዎችህ ሕዝቡን የምትፈልጉል ለመዛት ብቻ ነው። ከእንግዲህ በእናንተ በሆዳም ተላላኪ ምስለኔዎች የሚወከል የአማራ ሕዝብ የለም። መርገምት!! በዘመነ ሕወሓትም “መንግሥት አይታገሥም” እያልክ ነበር ልጋግህን ስታራግፍ የነበረው። እንደዚያ የማይደፈር መስሎህ ሕዝብ ለማሸማቀቅ ስትጋጋጥበት የነበረው አገዛዝ በሕዝብ አፈር ግጦ የት እንዳለ ታውቀዋለህ። ዛሬም ተገልብጠህ ተ… 

    See more
     

    Mekash Teshome

    ደግሞ ጀምራችሁ ! አስገራሚ ብአደናዊ ፍጥረቶች
     

    አዳ ሚንዳዳ

    ወላሂ ምን ብየ ንደምሳደብ ግራ ገባኝ ሁሉም ስድቦች አነሱብኝ መርዛም
     

    ጌታመሆን አሰፋ

    አንተ ደዌ ህውሃት የጡት አባትህ ሲነካብህ እንደሚነዝርህ እናውቃለን አንተና መሰሎችህ ብአዴናውያን 30 አመት ሙሉ ህዝባችን ዋጋ አስከፍላችሁታልና ዋጋችሁን የምታገኙበት ቀን እሩቅ አይሆንም
     

    አዳ ሚንዳዳ

    ሲጀመር አልተመረጥክም ኮሮጆ ገልብጠህ እንጅ የጎጃም አማር ይመቸው እንደ አር ነው የተጠየፋችሁ ያዋረዳችሁ
    even ማንበብ እራሱ አትችልም ፁሁፍን ብታነበው ራሱ ትደነግጥ ነበር አብይ ፅፎ የሰጠህን ነው የለጠፍከው
    ብናልፍ አራም ነው ብሎ ቢፅፍልህና ለጥፍ ቢልህ ማንበብ ስለማትችል ትለጥፈው ነበር ብትችልም ሰጋጅ ስለሆንክ በግድህ ያስለጥፍህ ነበር
    እረ አባቴ ይሙት ካንተ ኑሮ ሞት በስንት ጣዕሙ
     

    Wudase Ferede

    አታፍሩም አሁንም መንግስት ይፍቀድ አይፍቀድ እያላችሁ ህዝቡን ልታስጨርሱ ፕሮግራም ስታወጡ?! ኧረ እንደው ምን ጉድ ናችሁ እናንተስ? እድሜ ልክ ለስልጣን ሽሚያ እንጅ አንድም ቀን ለህዝብ ጥቅም ሳትኖሩ እዚህ ደረሳችሁ!! ድሮ የህወሃት አሽከር ዘንድሮ የብልፅግናው… በእናንተ እንዝህላልነት ነው እስካሁን ህዝባችን እያለቀ እተፈናቀለ እየሞተ ያለው ዋጋ እያስከፈላችሁት ያላችሁት እናንተ ናችሁ!! እናንተን ነበር መረሸንማ!!! ምድረ አድር ባይ ሁላ
     
     
  • ያኀዌ ይርኢ

    በየትኛው የሞራል ልዕልና ነው ወጣቱን የምትወቅሱት???
    የአማራ ክልል መንግስት እንኳን የአማራን አደረጃጀት ሊወቅስ ይቅርና ፊቱ የመቆም ድፍረት የለውም

    መሪ ያጣ ትውልድ በመሆኑ ነው ለውጣ መጣ ከተባለ ጀምሮ በማንነቱ ምክንያት በግፍ በየ ጉድጓዱ ለሚታረደው አማራ መንግስት ምኑ ነው? ይሄን ግፍ የአማራን ሞት ሊያስቆም በሚችል በየትኛውም አደረጃጀት ውስጥ ገብተን እንታገለዋለን ።… 

    See more
  •  

    Mekete Abera

    ስራህ ስላልሰራህ ለወያኔ አሳልፈህ የሰጠኸውን ህዝብ ከፈለገ በዕድር ወይም በጎበዝ አለቃ ተደራጅቶ ራሱን ነፃ ለመውጣት መታገል አለበት ከ6ሚሊዮን ህዝብ በላይ በባርነት ስር መውደቁን የሰማህ አይመስልም።
     
  • Eth Love

    ከናተ ውጭ አማራ ጠላት የለውም ዛሬም ያው ናችሁ
     

    Teshome Worke Z Habesha

    እናንተን ይዘን የምንሻገረው ጊዜ የለም ሀገሪቱን ወደ ተወሳሰበ ኹኔታ እየከተታችሁ አፋችሁን ባትከፍቱ መልካም ነበር።
    ከብት!!!!
     
     

    Winta Nahom

    አማራ እንደዚህ ጊዜ በራሱ አመራሮች ተላላኪነት ተዋርዶ አያውቅም። የአማራ ጠላቱ ሆዳም አማራው ነው የተባለው እውነት ነው።
     
  • ከመሸነፍ ይሻላል አፈር መልበስ

    ዶክተር ጠ/ሚ አብይ አህመድ ና ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን እባካቹህ ይኽን ሰውየ ማለትም የጌታቸው ረዳ ተላላኪ ና ጭብላሙን ብናልፍ አንዷለም አሁንኑ አስወግዱልን ምክንያቱም በመከላከያችን ና በጀግኖቻችን ደም እየቀለደ ነው
     
     

    Bezawork Tilahun

    ተው ባክህ!
    አተላ! ቃብር ጠባቂ!

    ያልታገስክ እንደሆነማ ምናባክ ታመጣ! የመንግስትህ አቅምማ ታየልህኮ!… 

     

    Fisseha Alemayehu

    እናንተ ካልጠፋችሁ አማራ ሰላም አያገኝም አርፋችሁ ተቀመጡ የናንተን አማራነት ማጣራት ነው ቀጣዩ ስራ ምክንያቱም ከጠላቶቻችን ብትብሱ እንጂ አትሻሉም።
     
     
     የኦሮሙማ ብልፅግና ዳይፐር ቀያሪ አሽከር….

    ዮቶር አምሐራ

    ቆሻሻ ኦነግ የላከህ አዴፓ
     

    አሳቷ የጁ ወሎ

    ገራችንን አስወርረህ ወያኔን አስቀረንብህ መሠል ተናደድክ ዉዳቂ ነህ ። ተላላኪ ሞክር ።።።።።
     
    •  

    Dawit Serawit

    አንተ የጠነባህ ተላላኪ ባንዳ
    ይህ ጦርነት ሲያበቃ ብዐዴንን ከክልሉ ጠራርገን ነው የምናስወጣው
    በል እንግዲህ ሞጋሳ አድርገህ ኦሮሞነትህን ተቀበል፡ ካለበለዝያ እርምጃ የሚወድብህ መሆኑን እወቀው
     

    Etege Hiwot Mekonenn

    ምድረ ዳይፐር

    Shemlis Genanew

    ለጦርነት አንተን የማማከር እና ያንተን ፍቃድ የመጠየቅ ግዴታ የለብንም።
    ድስት ላሽ ባንዳ።
    አንተ የአብይን እና ሽመልስ አብዲሳን ትዕዛዝ ለመፈጸም የምትርበተበተዉን ያክል፣እኛ ደግሞ በጠላት እጅ የወደቁ ወገኖቻችንን የመታደግ አማራዊ ግዴታ አለብን።
    ማፈሪያ ነህ።
     
     

    Tebkew Terefe

    የእሬሳው ብአዴን ሰዎች ልክ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ናቸው። ሁሌም የሚያሳስባቸው ህዝባቸው ሳይሆን ሆዳቸውና ወንበራቸው ነው። አቶ ብናልፍ የአብይ አህመድ ምጣፍ ጎታችና ካሃዲ መንደሬ ሰው ነው። ሌሎችም ያው ናቸው። ብአዴን እንዳይለወጥ ሆኖ የተቋቋመ የከንቱዎች ስብስብ ነው። ብአዴንን መለወጥ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም። አነዚህ ሰዎች ይሁዳዎች ናቸው። ምህረት ብትሰጣቸውም መልሰው የነበሩበት ወንጀል ላይ ተዘፍቀው ታገኛቸዋለህ።
     

    Mihretie Emiru

    አቶ #ብናልፍ_አንዷለም ይህ ሀሳብዎት የግልዎት እንደሚሆን አልጠራጠርም። ነገር ግን ይህ የእርስዎ ሀሳብ እንጅ #የህዝብ እና የመንግስት አቋም አይሆንም ሊሆንም አይችልም‼ ምክንያቱም ሀገር አጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት ለወንበራቸው መደላደል የሚያስቡ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሽፋን ሰጪ ህዝብ ሊኖር አይችልም። ምናልባትም ሀገርና ህዝብ አጣብቂኝ ውስጥ በገቡበት በዚህ ወቅት ስልጣኑ እና ወንበሩ ያሳሰበው ሰው ቢኖር እርስዎ የመጀመሪያው እንደሚሆኑ አልጠራጠርም‼ የአማራ ፋኖ የሚሰለጥነው አማራንና ኢትዮጵያን ከአሸባሪው #ህወሃት እና ከውጪ ፀረ-ኢትዮጵያ አካላት ነፃ ለማውጣት እንጅ ሀገር ለማፍረስና ወንበር ለመነቅነቅ እንዳልሆነ መረዳት ይኖርብዎታል‼

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.