Breaking News
Home / News / አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ

****************************************

ዛሬ የደስታና የድል ቀን ነው። የአማራን ህዝብ የገደሉና ያስገደሉ ፣ የዘረፉ ፣ የትህነግ ቅጥረኛና ተላላኪ ሆነው በህዝባችን ላይ ብዙ ግፍ የፈጸሙ ሰዎች ተይዘው ፍትህ ፊት ሊቀርቡ ነው። የደስታችን ምክንያት ብዙ ቢሆንም የስነ አዕምሮ ባለሙያና ሃኪም የሆነው ነፍጠኛው ወንድማችን ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ በተደጋጋሚ የሚገልጸው ሃቅ አለ።

“በሰው ልጆች ላይ ሰቆቃና ግፍ የፈፀሙ ግለሰቦች ተይዘው ህግ ፊት መቅረባቸው ፣ የሰሩት ጥፋት በአደባባይ ተገልፆና ሃቁ ፍርጥ ተደርጎ ፣ የሚገባቸውን ቅጣት ማግኘታቸው ለተበዳይ ወገኖቻችን ከሚሰጣቸው ማንኛውም ህክምና በላይ ህክምናና ፈውስ ነው”።

ህዝባችንን ለአመታት ያቆረቆዙ ፣ እንደ መዥገር ደሙን የመጠጡ ሁሉም ወንጀለኞች ለፍርድ ሲቀርቡ ያኔ ታላቁ ደስታ ይሆናል። የዋነኞቹ ጠላቶታችን በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሳ መያዝ የአምባገነኖችና የዘራፊዎች ጀምበር በርግጥም እያዘቀዘቀች መሆኑ ማሳያ ነው። በክልሉ ውስጥ ሙሰኞችን በደንብ የመመንጠር ስራውን ካከናወነ አዴፓ የሚገባውን ምስጋናና ክብር በይፋ የምንገልጽ መሆኑንም እናሳውቃለን።

እንኳን ደስ አለን ወገኔ ፣ ዛሬ ጥሩ ህክምና ነው!

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ በጥረት ኮርፖሬት ሙስና ፈጽመዋል ተብሎ በተጠረጠሩበት የሀብት ብክነት ወንጀል አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

አቶ ታደሰ ካሳ ጥረት ኮርፖሬትን በዋና ስራ አስፈፃሚነት ለበርካታ ዓመታት የመሩ ሲሆን አቶ በረከት ስምኦን ደግሞ ከበርካታ የመንግስት የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ባሻገር የጥረት ኮርፖሬት የቦርድ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፡፡

ጥረት ኮርፖሬት በተደረገ የኦዲት ግኝት መሰረትም ለኪሰራና ምዝበራ መዳረጉን ሲገለፅ ቆይቷል ፡፡

-Dr. Dessalegn Dagne (NAMA)

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.