Breaking News
Home / Amharic / አቶ መላኩ ፈንታ ማነው?

አቶ መላኩ ፈንታ ማነው?

ሃቀኛው መላኩ ፈንታ

መልከ ቀና ነው፤ ፀጉሩ እንደ መኸር ጤፍ ተኝቷል። ሲራመድ ይፈጥናል። ወደ ምኒሊክ ቤተመንግሥት እየገባ ነው። ገባ።
“አቶ መለስ ሦስት ምርጫዎች አሉኝ!” ቀጠለ።
አንድ ህግ ተክትዬ መሥራት፣ ሁለት እያስመሰልኩ መኖር፣ ሶስተኛ ሳልሰራ በሪፖርት መኖር!
አቶ መለስ በምርጫው ተደንቀው “በህግ ስራ፤ ማንም ከህግ በታች ነው” አሉት።
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ንግግር ከራሱ እሳቤ ጋር ተጣጣመ።
የሚኒስቴር የቤተሰብ መኪና አልቀበልም ብሎ ቤተሰቡ በአዲስ አበባ የታክሲ ሰልፍ መያዝ ለመዱ። ቁርስ እና ምሳውን ከመስሪያ ቤቱ ካፍቴሪያ በ15 ብር እየተመገበ ሥራውን አጧጧፈ።
አንድ የክልል ቢሮ ኃላፊ ቢያንስ ሁለት መኪና እና መኖሪያ ቤት ይሰጠዋል። ለዚህ ሰው ግን የለውም ።በጭቃ ቤት ይኖራል። ሰውየው የገቢዎች እና ጉምሩክ ኃላፊ ነው። ሚኒስትር ነው። የሃገሪቱ ገንዘብ በመዳፉ ቢያልፍም ወደ ኪሱ አያስገባም። ሰውየው መላኩ ፈንታ ነው።
አንድ ቀን የአቶ በረከት ስምኦን ዘመድ በ3 ሚሊየን ብር ያለቀረጥ ካሜራ አስገባ። መላኩ ሆዬ አስወረሰው። አቶ በረከት ቢደውልም ወይ ፍንክች መላኩ ሆዬ።
መላኩ ሒልተን እና ሸራተን ሆቴልን አያውቋቸውም። አላሙዲ ስለ መላኩ ኩሩነት ሁሌም ይደነቃሉ። ለአላሙዲ ሚኒስትሮች ይሄዱላቸዋል እንጂ ራሳቸው ወደ ሚኒስትር ቢሮ አይሄዱም። አላሙዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ብቻ ይገባሉ። ሌላ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት በገንዘባቸው እና በወኪላቸው ያስፈፅማሉ።ኩሩው አቶ መላኩ ግን ከአላሙዲ ጋር ሸራተን አልተገናኙም። ይልቁንም አቶ አላሙዲ በአቶ መላኩ ተደንቀው ወደ ቢሮአቸው አመሩ። አቶ መላኩ እና አላሙዲ እንደማንኛውም ደንበኛ ቢሮ ተገናኙ።ሲገናኙም መላኩ የተለየ መቅበጥበጥ አላሳየም። አቶ አላሙዲ በአቶ መላኩ ተደነቁ።
አቶ መላኩ ሲታሰር ከሚኖርበት የመንግሥት ቤት ቤተሰቦቹ እንዲወጡ መንግስት ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። የአቶ መላኩ ቤተሰቦች ወደ ጎዳና ሊወድቁ ሲል በክብሩ የማይደራደር በመሆኑ ቀድሞም አድንቀውት ነበርና አቶ አላሙዲ ለአቶ መላኩ ቤተሰቦች ቤት ሰጧቸው። እስከዛሬም የሚኖሩት አቶ አላሙዲ በፈቀዱት ቤት ነው። አቶ አላሙዲ ጉዳይ ለማስፈፀም በብቸኝነት ሂደው የነበሩት ወደ አቶ መላኩ ቢሮ እንደሆነ ይነገራል።
2005 ዓም ከ3 ሺ በላይ አማራዎች ከቤሻንጉል ተፈናቅለው ፍኖተሰላም ላይ ከተሙ።
አቶ መላኩ “አማራው ሁነኛ ተወካይ የለውም። ሀገሪቱም አግላዋለች” ሲል በኢህአዴግ ጉባዔ ተናገረ። በብአዴን ውስጥ ትምክህት ቤቷን ገነባች ተብሎ ተወገዘ።
አቶ መላኩ በ 2000ዎቹ አካባቢ የአማራ ልማት ማኅበር ቴሌቶንን አቀናጅተው በቀን ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ አሰብስበዋል። አማራው በኢኮኖሚ እንዲራመድ አማራ ባንክ እንዲከፈት አድርጓል። ይህ ባንክ በወቅቱ አማራው አማራ ሲሉት ብዙ ላይሞቀው ይችላል ተብሎ አባይ ባንክ ተብሏል። የደጀን ሲሚንቶ ፋብሪካ እና በደብረብርሃን ያሉ ውስን ፋብሪካዎች የአቶ መላኩ የጥረት ውጤቶች ናቸው።
ጎንደር ፒያሳ የዳግማዊ ቴዎድሮስን ሃውልት እንዲቆሞ አድርጓል። አቶ በረከት እና አቶ መላኩ ጎንደር ቀበሌ አንድ አብረው አድገዋል። የዳግማዊ ቴዎድሮስ ሃውልት ሲገነባ አቶ በረከት አሻራ ብዙ ባይኖራቸውም የኔ ስም ከአሰሪ ኮሚቴው ካልገባ ብለው ስማቸውን አሰፍረዋል።
የወገኑ ወደኋላ መቅረት የሚያንገበግበው አቶ መላኩ በ 2005 ዓም የብሄሮች በዓል በባህርዳር ሲከበር ከተማሪዎች ካፌ ሻይ በ50 ሳንቲም አብረን ተቋድሰናል። አቶ መላኩ ክብራቸው እውነት እንጂ ስልጣናቸው አልነበረም።
ግንቦት 5 ቀን 2005 ዓም ሙሰኛ ተብሎ ወደ ቃሊቲ ገባ። ከተከሰሰበት ገራሚ ነገር ውስጥ የወይዘሮ መቅደስ ለማ ጉዳይ ነው።
አቶ መላኩ ከወይዘሮ መቅደስ ሁለት ልጆችን ወልዷል። ቴዎድሮስ እና ፋሲል መላኩን። ነገር ግን የሰማንያ ሚስቱን በስልጣኑ ከሌላ ወንድ የነጠቃት ነው ተብሎ ተከሰሰ። የሁለት ልጆቹን እናት ባለቤትህ አይደለችም ተባለ።
ሌላው ሆቴል ሄደህ ሳሙና እና ሻወር ስልጣንህን ተጠቅመህ በነፃ ተጠቅመሃል የሚል ክስ ነበር።
እንዲሁም ባለቤትህን ደብረሊባኖስ ገዳም በመንግስት መኪና ወስደሃል ተብሎም ተከሶ ነበር።
መላኩ 5 ዓመት ሙሉ ያለ ብይን በእስር ቆየ። በአምስት ዓመቱ እስሩ ተቋረጠ። አቶ መላኩ እንደ እስክንድር ነጋ፣ እንደ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከውጭ ወደ ሃገራቸው ገብተው ለሃገራቸው ሲሉ ዋጋ ከከፈሉ ብሩሃን መካከል ናቸው።
ምንጭ፤ ጋዜጠኛ እና ደራሲ የሺሀሳብ አበራ ከሶስት አመት በፊት እንደጻፈው

እነሆ ዛሬ የአማራ ባንክን እውን አደረገ

Check Also

ሰሎሞን ካሳ ማነው? Who is Solomon Kassa?

አንከር ሚዲያ እንደዘገበው .. ለማታውቁት ሰለሞን ካሳ ይባላል ., ወንጀለኛው የሆነው ይህ ሰው የህዝብ ድምፅ …

የአድዋ በአል በለንደን ከተማ በደማቅ ተከበረ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.