Breaking News
Home / Amharic / አብን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ!

አብን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ!

አብን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ
*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የፖለቲካ ፕሮግራሙን፣ አማራጭ ፖሊሲዎቹን እንዲሁም በወቅታዊና ስትራቴጂካዊ አካባቢያዊ፣ አገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ከ125 በላይ ስኬታማ ሕዝባዊ መድረኮችን ማዘጋጀቱ ይታወሳል። በመዲናችን አዲስ አበባም በሚሊንየም አዳራሽ ከሕዝባችን ጋር ውይይት ለማድረግ በተደጋጋሚ ጊዜ ጥያቄ አቅርበን ከ6 ወራት በኋላ የአዲስ ፓርክና ዲቨሎፕመንት የሚሊንየም አዳራሽን የካቲት 24/2011 ዓ/ም መጠቀም የምንችል መሆኑን ጠቅሶ አስፈላጊውን ቅድመሁኔታ አሟልተን ክፍያ እንድንፈፅም ደብዳቤ ጽፎልን ነበር።

በአዲስ ፓርክና ዴቨሎፕመንት ደብዳቤ መሰረት ውል ለመያዝ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ክፍል ፈቃድ ጠይቀን ከሳምንት በላይ ካጉላሉን በኋላ በቀጠሯችን መሰረት በቀኑ ስንገኝ አዳራሹ ለኦኤምኤን ገቢ ማሰባሰቢያ ከእኛ ተነጥቆ መሰጠቱ ተገልፆልናል። ይህም በፓርኩ ማኔጅመንትና በከተማ አስተዳደሩ ኃላፊዎች የጓዳ ስምምነት የተደረገ መሆኑን ተገንዝበናል።

ሕዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ ከኅትመትና ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ በሚሊዮን የሚቆጠር ኃብት ወጪ ያደረግን በመሆኑ ስብሰባ እንዳናካሂድ ስልታዊ በሆነ መንገድ መከልከላችን የሚደርስብን የኢኮኖሚ ኪሳራ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አብን ይህን አይን ያወጣ አፓርታይዳዊ አካሄድና ለባለጊዜ አፋሽ አጎንባሽነት በንቅናቄው ላይ እንደተሰነዘረ ንቀት ብቻ ሳይሆን አማራነት ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ይቆጥረዋል።

ስለሆነም አብን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የምትኖሩ አማራዎች እንዲሁም ለፍትኅና እኩልነት ውግንና ያላችሁ ኢትዮጵያውያን የተፈፀመብንን አፓርታይዳዊ አሰራር በማውገዝ አብራችሁን እንድትቆሙ እንጠይቃለን። የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ይኽን መሰል አፓርታይዳዊ አሰራር አጣርተው አስፈላጊውን የሕግና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰዱ በአጽንዖት እንጠይቃለን። አብን የአዳራሽ ውስጥ ስብሰባ በመከልከሉ ምክንያት ፕሮግራሙን ወደ አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የተገደደ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀኑን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

Check Also

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Peace Prize of Abiy Ahmed has been Revoked in Germany.

Date: 08/03/2023Author: Martin Plaut3 Comments Ethiopia’s Prime Minister has been quietly stripped of an international peace prize that …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.