Breaking News
Home / Amharic / አቢይ የሚናገረው ስለ ኢትዮጵያዊነት ነው። የሚከተለው ግን የጎሳ ፖለቲካ ነው።

አቢይ የሚናገረው ስለ ኢትዮጵያዊነት ነው። የሚከተለው ግን የጎሳ ፖለቲካ ነው።

አቢይ :- የሚናገረዉ ነገር ስለ ኢትዮጲያዊነት ነዉ። የሚከተለዉ ግን የጎሳ ፖለቲካ ነዉ።
——————————
የሚከተለዉ ህገመንግስት ኢትዮጲያን ቀዳዶ የሚጥለዉን የጎሳ ህገመንግስት ነዉ።
—————
አቢይ በምላሱ ግን እንዲህ ብሎ ይነግረናል። የሚከተለዉ ንግግሩ የአቢይ የፓርላማ ንግግሩ መሆኑ ነዉ።

“ትግራይ ነህ፤ አማራ ነህ፤ ኦሮሞ ነህ ተባብለን መባላት ከማባላት ባሻገር የጨመረልን እከክ ነው። የሚጠቅመን በምላሳችን የምንዘራው ስድብና ጥላቻ ሳይሆን፣ በእጃችን የምንነካው አፈር ነው።”
—————-
በአለፉት ሁለት አመታት በኢትዮጵያዉያን ላይ በዘረኝነት ስንት ኢ-ፍትሃዊ ነገር እንደተሰታ ባላስተዉል ኖሮ ከላይ አቢይ የተናገረዉን ንግግር ብቻ በመስማት ይሄማ ምርጥ መሪ ነዉ። ይሄማ ሊደገፍ ይገባዋል ብዬ እደመድም ነበር።

————

ግን ይሄን የመሰለ ንግግር በተግባር ሳይተገበር ለመድረክ ማሳመሪያ መሆኑ የሚታወቀዉ አሁንም የአቢይ የፖለቲካ ያዉ የጎሳ ፖለቲካ መሆኑ : ህገመንግስቱም የጎሳ ፖለቲካ መሳሪያ: ክልል አከላለሉም የጎሳ ፖለቲካን ለማራመድ እንዲበጅ ሆኖ የተሰራ መሆኑ ነዉ።

አቢይ ኢትዮጲያዊነት ይቅደም ኦሮሞ አማራ ትግሬ መባባል ይቅር ካለ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍናዉን መቀየር ነዉ ያለበት።

ህገመንግስቱን በመለወጥ አሁን ያለዉን ክልል ማፍረስ ነዉ ያለበት።

ይሄ ሳይሆን ግን እንዲህ አይነት ንግግር ማድረግ ድራማ ነዉ። የጎሳ ፖለቲካ መጥፋት ሲችል ብቻ ኢትዮጲያዊነት ከፍ ይላል።

የጎሳ ፖለቲካና ኢትዮጲያዊነት አጥፊና ጠፊ ናቸዉ። ሀገር እየመሩ የጎሳ ፖለቲካ ፍልስፍናን ተሸክሞ ኢትዮጵያን በጎሳ ክልላዊ ከረጢት ሸንሽኖ : የጎሰኝነት ፖለቲካን የሚያጀግን ህገመንግስት አዝሎ ኢትዮጲያዊነትን መስበክ ዝም ብሎ ተረት ተረት ለህጻናት ወይም ድራማ መስራት ነዉ።

ኢትዮጲያዊነትን አስቀድሞ የጎሳ ስርዓትን አጥፍቶ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ እንደ ሰዉ የሚኖርበት ሀገር የሚሰራ መሪ እና ፓርቲ ብቻ ነዉ ስለ ዲሞክራሲ እኩልነት ሰበአዊነት እና የህዝቦች የጋራ ብልጽግና ቢናገርም ቢሰራም ተዓማኒነት ያለዉ።

እንዲህ አይነቱን ኢትዮጲያዊ የመጣ እንደሆነ ብዙሃን ኢትዮጲያዉያን ይደግፉታል።

አቢይ የአፍ አክሮባቱን ትቶ ኢትዮጲያዊነትን በተግባር ያስቀደመ እንደሆነ የኢትዮጲያዉያን መሪ ይሆናል።

ከዚያ ዉጭ ግን ምንም አይነት የኢትዮጲያዊነት ንግግር አሁን ያለዉን የዘረኛ ስርዓት ግፍ እና እዉነታ ለመሸፈን አቅም አይኖረዉም።

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.