Breaking News
Home / News / አስተያየት ከደብሩ ነጋሽ  (ሃኪም) 

አስተያየት ከደብሩ ነጋሽ  (ሃኪም) 

አስተያየት ከደብሩ ነጋሽ  (ሃኪም)

ምረር እንጂ አማራ ምረር እንድቅል፣ አልመር ብሎ አደል ዱባ እሚቀቀል!

በረዥም ታሪኩ አማራ አያሌ የህልውና ተግዳሮቶች ቢያጋጥመውም፣ አንዴም ስላልተጠነቀቀ በወያኔው የ 27 አመታት የወረራ ዘመን፣ ከ ስድስት ሚሊዎን የበለጠ ህዝበ ተፈጅቶበታል። ባለፉት ግማሽ ምዕት አመታት፣ በኦቶማን ቱርክ ድጋፍ ፣ግራኝ አህመድ አማራውን፣ ክርስትያን ፣እስላም፣ ሳይለይ ፈጅቷል።  የኦሮሞም ወረራ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ደም አጉርፏል።
እንግሊዝ  በቴወድሮስ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያን ስትወጋ፣ የትግሬው ንጉስ ዮሃንስ ስለአገዘ፣ ለአገልጋይነቱ ባገኘው መሳሪያ አማራን አምሷል። ደጁ ድረስ የመጡን ወራሪ ጣልያንና ደርቡሽን ትቶ ፣ ምንም ባልበደለው ያልታጠቀ አማራ ዘመተ።  ዮሃንስ ሸዋን ቢያፍርም፣ በወሎ ፣ በጎንደርና ጎጃም 80’000 የታጠቀና የተራበ ትግሬ፣  አፍሷል። የሶስቱንም ነባር ዕምነት ተከታዮች አማሮች፣ ክርስትያኑን፣እስላሙንና አይሁዳውያን ቅማንትን ፣ በተደጋጋሚ ፍጅቷል፣ ዘርፏል፣ ቤተክርቲአናትና ገዳማትምና እህል ሳይቀር አጋይቷል፣ ሴቶችን አስደፍሯል ።
እስላሙንና  ቅማንቱን በሰይፍ ሃይማኖት አስቅይሯል፣ በአዋጅ መሬታቸውን ወርሷል። ዮሃንስ ባአማርነቱ የፈጀውን ቅማንት ፣ ዛሬ ወያኔ በፊናው ከወገኖቻቸው ያፋጃቸዋል።
‘አዎ ማለት መረታት፣ ያለመመከት መመታት’
ባለፉት 150 አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ በእንግሊዝ፣ በጣልያን፣ ህለተዜ ስትወረር ፣ ትግሬ  ለጠላት ያልተገዛበት  ወቅት አልነበረም። በሶማልያውም፣ ወያኔም አብሮ ኢትዮጵያን ወግቷል።
አማራ፣ ኢትዮጵያን መስርቶ፣ ከተሞችዋንም ቆርቁሮ፣ ዳር ድንበሯን ሲያስከብር የኖረ፣ ስልጡን ህዝብ ነው። ጣልያን አማራን ነጥሎ የፈጀውም ግዙፍ ማንነቱን፣ በአድዋም ሚናውን ጠንቅቆ ሰለተረዳ ነው።  በጣልያን ወረራ በ 1931 ዐመተ ምህረት (1938 ኤአ) ፣ በግምት ከ 25’000 ባገሪቷ ዱር~ቤቴ ካሉ አርበኞች፣ ውስጥ ከ 23’500 በላይ አማሮች እንደነበሩ፣ የጣልያን መረጃ ያማለክታል።  በዚሁ  የጣልያን ወረራ ከ 800’000 እስከ አንድ ሚሊዎን  ኢትዮጵያውያን ሲፈጁ፣ በትንሹ  ካስሩ፣ ዘጠኙ ዐማሮች እንደነበሩ፣ የጣልያን ሰነዶች ይመሰክራሉ። ግራዚያኒ ከፈጀው 34’000 አዲስ አበቤዎችም ፣ በነቂስ የተጨፍጨፈው አማራው ነበር።
‘እስቲ ጨምርበት በበደል ላይ በደል፣ ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል’
ከ 1966 ዐም ጀምሮ ፣ ለአርባ አምስት ዐመታት በስውርም ሆነ በገሃድ ያልጠረጠረው አማራ ሲመነጠር ቆየ። ደርግ አይነተኛ ጠላት ብሎ ፈርጆት፣ በገጠርና በከተማው ያልተፈጸመበት ግፍ የለም።  ለአማራ የህልውና ዋስትና የነበረ ትጥቁ ነበር። ያንን የፈታው በደርግ ‘በምሁራን’ ጃስ ባይነት ነበር። ስውር አላማ የነበራቸው አማራ-ጠል አልባሌዎች ፣ በምንሽርና  በመውዜር፣ ታንክና መድፍ ይማርኩ የነበሩን ጀግኞች፣ ነፍጠኛ ብለው አስፈጇቸው።  ወደር ያልነበራቸው ምሁራንን ፣ አዋቂዎች፣ የጦር መኮንኖች፣ መንግስቱ ሃይለ ማሪያምን በመሰለ መናኛ፣ በግፍ ተረሸኑ። አማራው። ከእርስቱ ተነቀለ፣ የከተማ ቤቱ ተወረሰ። ደህየ ። በሌሎችም የደርሰ ቢሆን፣ ከተሜው አብዛኛው አማራ ስለነበር፣  ሰለባነቱም በዚያው ልክ ነበር።
ቀይ ሽብር ፣ ነጭ ሽብር በማለት፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ወጣት አማሮች በከተማና ገጠር ታደኑ። ከደርግ ጥይት የተረፈው ፣ ከወላጅ ጉያ እየተወሰደ ለትግሬና ኤርትራ ተገንጣዮች የሳት እራት ሆነ። ለ 17 አመታት ከደርግ ሰቆቃ እንባውን ሳያብስ፣ ኢትዮጵያን ሊቀራምቱና ሊያቀራምቱ የመጡ የውስጥ ወራሪዎች በግላጭ አገኙት። ይህ ሁሉ ሲሆን የአማራው ምሁር፣ ቀፎው የተነካበት ንብ አልሆነም ። በዚያው በፈረደበት ኢትዮጵያዊነት ስም እጅግ ተጎዳ።
አዲስ አበባ ያማራ ዐጽመ~ርስት ስትሆን ፣ የድፍን ኢትዮጵያውያንም ከተማ ናት
አማራ ‘በፍርድ ከተወሰደች በቅሎው፣ የተቀማው ጭብጦ’ የሚያቃጥለው ህዝብ ነው። ዛሬ በወያኔ ጃስ ባይነት፣ የኦሮሞ ‘ልሂቃን’፣ አዲሳባን ‘የግላችን ነች’ ከማለት አልፈዋል። ኦሮሞው አቢይ፣ በነውር ስማቸው የጎደፉ ወገኖቹን በሹመት አንበሽብሿል። የወያኔ ምርኮኛ የነበረን ለጦር አበጋዝነት፣ ለአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዥነትም፣ ብልግናው የሚወራለትን፣ ሾመ። ከንቲባም። እሱማ ስራ ለመቀጠር፣ ኦሮምኛ ቋንቁን ማወቅ፣ መስፈርት ያደረገ ጎበዝ ነው። በነካ እጁ፣ አዲስ አበባ ውስጥ በግፍና በገፍ የሚያስፈርሳቸው ቤቶች እንዳጋጣሚ ያማራ ናቸው። እንዳጋጣሚም፣ ብዙህ ሽህ ገጠሬ ኦሮሞዎችን የአዲስ አበባ ከተማው ነዋሪነት መታውቅያ ያለአግባብ ይታደላቸዋል!!
አዲስ አበባ፣ አማራ ከ 1500 አመታት በፊት፣ ከውቅር ድንጋይ ዋሻ ሚኪያኤልን ቤትክርስቲአን ያነጸባት ከተማ ናት ። ዛሬ በዙሪያዋ ለብዙ ትውልድ የኖሩን አማራ ገበሬዎች፣ በልማት ስም የኦሮሞው መስተዳደር ከርስታቸው ሲነቅል አማርነታቸው ግን ሳይጠቀስ ነው።
ከ 1380 ጀምሮም በረራ በመባል ትታውቅ የነበርችው አዲስ አበባ፣ ያማራ አጽመርስቱ ናት። ምንሊክ አዲስ አበባን የቆረቆሩት፣ ግራኝ በደመሰሳት ከተማ፣ በበረራ ቅሪት ላይ ነው። ግራዚያኒም ካስፈጃቸው 34’000 አዲስ አበቤዎችም ብዙዎቹ አማሮች ነበሩ።ኦሮሞ ዝር ያለባት ትላንት ነው።
ወራሪዎቹ፣ ወያኔና ኦንግ ፣ ያማራን ጉዳይ አስፍጻሚ ሎሌዎች ፈጥረው አማራን ከማእዱ ከአዲስ አበባ ለማራቅ፣ ባህር ዳር ያሽቀነጥሯቸዋል። ‘ርስት በሺህ ዐመቱ ለባለቤቱ’ ይላል ያገሬ ሰው። አዲስ አበባም እንደገና፣ የሸዋም፣ ያማራም፣ የድፍን ኢትዮጵያዊም ከተማ መሆኗ አይቀሬ ነው።  አማራ ከማንም በበለጠ እንደሻማ እየቀለጠ፣ ለእናት ሃገሩ ሲባዝን፣ ባንዳና መሰል ባላንጣ፣ አጽመርስቱን፣ ሸዋን፣ቤተአማራን፣ ላኮመንዝን፣ጎጃምን፣ ጎንደርን መቀራመታቸው፣ ‘አደባብሰው ቢያርሱ፣ ባረም ይመለሱ’ ነው ነገሩ።
‘ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዳው አይቀበለውም’
በአማራውም ሆነ በኢትዮጵያ ለተደቀነው የህልውና ፈተና፣ዋንው ምክንያት፣ አማራው፣ ባገሩ ጉዳይ ታዛቢ በመሆኑ ነው። ፍትህን በኢትዮጵያ ለማስፈን ፣ ያማራው ተጋድሎ አቻ የለውም።  ‘’ መሬት ላራሹ’‘ ብሎ ከማንም በላይ ተዋድቆ፣ ደርግ ያጨናገፈውን ለውጥ፣ በማምጣት የአማራው ድርሻ ግዙፍ ነው። ባለመታደል፣ በግራ~ዘመም እና አማራ~ጠል ደርግ ውስጥ የነበሩ  ኦነግ ፣ የወያኔና ሻብያ  የባንዳ ዝርያ፣ እንዲሁም የነቀዙ አማሮች ፣ አማራን በ‘የብሄር ጭቆና’ ወንጅለው ዘመቱበት። ‘ አማርኛ መማሩ፣እንጀራና ወጥ፣ ዱለት፣ ምንቸት፣ጠጅ መውደዱ፣ ገመናውን የሚሸፍንበት ጨርቅ መልበሱ’  የባህል ተጽዕኖ ተባለ።
ይህን በመሰለ ፍሬ ክርስኪ ክስ፣ ያርበኛው ዝርያ፣ ያማራው ልጅ እውነት መሰሎት አፈገፈገ። ‘‘እስቲ ወቃሾቻችን እንዳሻቸው ይሁኑ ፣ይሞክሩት’’ አለ። ያባቶቹን ግዙፍ ማንነት ሸሸው፣ ተጠየፈም።
ያማራው ታዛቢ መምሰል የልብልብ ያበቃቸው ወያኔና ኦንግ፣ከደርግ ግፍ ያላገገመውን አማራ፣ በሃሰት ‘’አማራ የኦሮሞን ጡት ቆርጧል’’ ፣ብለው ሃውልት አቆሙበት ።ብልት መስለብ፣ ሲሆን የኦሮም ባህል እንጂ፣ የአማራ እንዳልሆነ ያውቁታል ። አብይና ለማ በዚህ ሊጸጸቱ ቀርቶ ፣ ህግ ቢያከብሩ ኖሮ፣  ያንን ነገ  አማራው እንደሚፋረዳቸው አወቅው ሃውልታቸውን ፣ ባፈረሱ ነበር። አሁንም ተገትሯል።
አማራው ባይደፈር፣  ምርኮኛው የጦር አበጋዝ ፣ብርሃኑ ጁላ 29 ንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞች በገምድር አስጨፍጭፎ ባልካደ!  በዚያው ሰሞን፣ ስምሪት ላይ የነበረን የኢትዮጵያ ሰራዊት ያገቱን ትግሬዎችስ በነጻ ይለቅ ነበር? የቀድሞ የወያኔ ምርኮኛና ፣ ለ 28 ዐመት ሎሌያቸው የነበረን፣  የተናቀን ከሃዲ፣ ያገሪቱ የጦር አበጋዝ ከማድረግ፣ የባሰ ላገር ህልወና አደጋ አለ?
አማራ ‘ኢትዮጵያ እንዳትበታተንብን፣ በሚል ስሜት ተጠፍንጎ ፣ ራሱን ጥሎ፣ የገጠመውን ተገንዝቧል።  ‘የማ ቤት ለምቶ የማን ሊበጅ ፣ ያውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጅ’ አለማለቱን እንጃ እንጂ።
ለውደፊት አማራው ምንነቱንና ማንነቱን ለማስከበር፣ ጠላት ተመሳሳይን ጥቃት ለመሰንዘር እንዳይዳዳ፣ ያማራን ቁመና የሚመጥን፣ ትጥቁን የማይስደፍር ድርጅት ያስፈልገዋል። በቅርቡ ብሶት የወለዳቸው ያማራ ምሁራን ያቋቋሙት፣ ዐማራ ብሀራዊ ንቅናቄን (አብን)  መደገፍ የሚገባው ዐማራ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ህለውና የሚያሳሳው ዜጋ ሁሉ ነው።
‘ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባ’
ከ 50’000 አመታት በላይ  ኢትዮጵያ ውስጥ  ለመኖሩ የማያወላዳ የደም የምርምር መረጃ ያረጋገጠለትን አማራ፣ ‘መጤ’ አሉት ።  ያዛሬ 1’400 አመታት ግድም፣ ከየመን በአገልጋይነት አክሱም የተጋዙ የወያኔ ምንጅላቶችና፣ ከ450 አመታት ወዲህ ዮጵያን የወረሩ የኦነግ ኦሮሞዎች እንኳን መጤ አልተባሉም። መባልም የለበት። አማራና ኦሮሞ፣ ከማንም የበለጠ በደምም የተዋሃደ ህዝብ ነው።
የዚህ ጽሁፍ ደራሲ ፣ሁለት ቅድም አያቶች ከወሎ ሃረር ወርደው የግብጹን ምስለኔ አሚር አብዱላሂን፣ ድል ነስተው፣ እንደገና አድዋ ጣልያንን ድባቅ የመቱ ነፍጠኞችና ፣ኩሩ ቦረኖች እንደነበሩ ሁሉ፣ ኩሩም አማሮች ነበሩ።
ለወያኔና፣ ለመናጆው ኦንግ፣ አንድ ያበው ተረት ይጠቀስ። “ አጣራለሁ ብላ በቅሎ ሸንታ ሽንቷን ፣ ገልጣ ታሳያልች የውስጥ አካላቷን“። ማንነታቸውን ማስገንዘብ ይገባል። ይሉንኝታን ለሚያውቅ ነው። ያማራው  ወደር የልሽ ሰማዕትነቱ፣ ጀግንነቱን ፣ አጋር ስብእናው፣ አሌ የማይባል ፍትሃዊነቱ፣  ያገርና ወገን አልኝታነቱን ፣ ቅንነቱ፣ ባህሉ፣ ትውፊቱ፣ ስነልቦናው፣ ወ፣ዘ፣ተ፣ የበርካታ ሽህ ዘመናት ስልጣኔው ውጤት ነው።
ወያኔና መሰሎቻቸው ያማራው  ልዕልና፣ የሴትና ወንድ አቻነት፣  የእነርሱን አልባሌነት ማጋለጡ፣ ያበሳጫቸዋል። ለአብነት፣ የሚከተሉት ብሂሎቹ ትልቅነቱን ይገልጻሉ። ‘’ሴት ታውቅ፣ በወንድ ያልቅ’’ (የሴትን ከወንድ፣ ብዕውቀት ትልቃለች) ፣ ‘’የትም ተወለድ አንኮበር እድግ’’ ( ከማ መወልድ ሳይሆን፣ ሆኖ መገኘት መብለጡን) ‘’፣ ‘’እስላም ካበለ ፣ ዘላን ከፈተለ/ሚዛን ዘነበለ’’( ሙስሊም ሊዋሽ፣ አይቻለውም)።   እርግጥ ነው አማርነት አይገድም።  ዕውቁ የታሪክ ሊቀ ሊቃውንቱ፣ ሃይሌ ላረቦ እንዳለው ፣ ‘ስልጡን ኢትዮጵያዊ ሁሉ አማራ ነው።
‘እስቲ ጨምረበት በበደል ላይ በደል፣ ወተት ይሸፍታል እንክዋን ሰው ሲበደል’
ከ 1983 ጀምሮ  ‘ኦሮምያ’  በሚሉት የቅዥት ክልል የነባር እትዮጵያውያን ርስት፣ የወያኔና ኦነግ ጣምራ መንግስት፣ በሚሊዎኖች የሚቆጠሩን ዜጎች ፈጅተውና አባረው ዘር አጽድተዋል። አርሲ ራሱ በሞጋሳ (በግዳጅ) ኦሮሞ የሆነ ሃዲያ ነው። ሸዋም እንዳለ አማራ፣ ጉራጌና ጋፋት እንደነበር ዕውቅ ነው። ኦሮምያ የሚለው ቃል  አንድ በ 1850 አካባቢ ወለጋ የኖረ ጀርማን ሚሲዎናዊ የፈጠራት ናት ። ወያኔ በመናጆነት ከየስርቻው የሰበሰባቸው  የኦሮሞ ምሁራን ተብዬዎች፣ የተቀራመቱትን ክልል  በፈርንጁ የዳቦ ስም ኦሮምያ  አሉት ። ነባሩን ደግሞ ‘’ መጤ’’ ትብሎ ዜግነቱን ለ 27 አመት ትገፈፈ። ‘ባላዋቂ ቤት እንግዳ ናኘበት’  እንዲሉ።
ኦሮሞውን ፣ አማርኛ የመማር መብቱን ነፍገው አደነቆሩት ፣ ክፉኛ በደሉት። ኦሮሚፋን ለመጻፍ፣ ግዕዝ እጅግ መሻሉን ያውቃሉ። ግን ኦሮሚፋን የማይመጥነውን፣ አቅመቢስ ላቲን መረጡ። ሌላው ኢትዮጵያዊ፣ ኦሮሚፋን እንዳይማር  አደረጉ። ገዕዝ አቻ የሌለው ፊደል በመሆኑ፣ አርመኖች ከላቲን፣ከግሪክ፣ከእብራይጥ፣ ከአርብኛ የበለጠ ሆኖ ስላገኙት ነው፣ ክ 1500 አመት በፊት፣ ፊደላቸው ያደረጉት።
ከዚያ አልፎ፣ አማሮች በገዛ በአጽመርስታቸው በሸዋ ሳይቀር፣ በአማርኛ እንዳይማሩና እንዳይዳኙ ተደርጓል። ያማራን መሬት ከመቀራመታቸውና ለሌሎች ከመለገስም በላይ፣በህዝቡ ህልውና ዘምተዋል። ኦነጎች የነ ጎበናን፣ የነባልቻን፣ የነሃብቴ አባ መላን፣ የነገበየሁን፣ የነገረሱን፣ የነጃገማን፣ የነአብዲሳን ወዘተ ዕጹብ ድንቅ ጀኝንነትና፣ ልዕልና፣ ሊኮሩበት የሚያስችል አቅምም ሆነ ስብዕና የሌላቸው ናቸውና ።   የቀን ጉዳይ ነው እንጂ አዲስ አበባ፣ እንደገና የኢትዮጵያም ፣ የሸዋና፣ ያማራም ከተማነቷ አይቀሬ ነው።
አማራን ባያገለለ ፣የወራሪዎችና በንጹሃን ደም የተጨማለቁ ፣ ቡከን የወያኔና ኦነግን፣ ህግ~አራዊት፣ አማራው የመገሰስ ግዴታ አለበት። ስለዚህ የኢትዮጵያን ህልውና የሚምኝ ወገን ሁሉ፣ የአማራን መደራጀት ሊደግፍ ይገባል።ያማራው ብሀራዊ ንቅናቄ (ዐብን)፣  የቁርጥ ቀን ልጅ ነውና አደራ ።
ያአማራው ቁጣ ቢዘገይም ጎምርቷል። ያባትና የናቶቹን ቆራጥ ማንነት፣ መላበስ እንዳለበት ተረድቷል። የሚያዋጣው አማርነነት ብቻ ነውና። “ እስቲ ጨምርበት በበደል ላይ በደል፣ ወተት ይሸፍታል እንክዋን ሰው ሲበደል“ እንዲሉ። ያማራው ትግል እንደ ጭድ እሳት ቡግ ብሎ አይከስምም። ሊዳፈን የማይችል የግንድ እሳት እንጂ። የተገፋን አማራ ምንም ሃይል አይበግረው። አማራ ይህን ሆንኩ ብሎ ማላዘንን ይጸየፋል። ይሁን እንጂ ፣ ‘ጠላቴ ጧት ሙቶ እኔ ልሙት ማታ፣ የሺህ ቀን እድሜ ነው ያንድ ቀን ደስታ’ የሚያሰኝ ብርቱ የፍትህ ስነልቦና ያለው ህዝብ ነው። ዋዛ አደለም።

Check Also

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

የትግራይ ምሁር የወያኔና የአቢይ አህመድን ሴራ አጋለጠ።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.