Breaking News
Home / News / አማራ ክልል ምክር ቤት አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ሰየመ፡፡

አማራ ክልል ምክር ቤት አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ሰየመ፡፡

አማራ ክልል ምክር ቤት አዲስ ርዕሰ መስተዳድር ሰየመ፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለፓርቲያቸው መልቀቂያ ማቅረባቸውንና አዴፓ መልቀቂያውን መቀበሉን ተከትሎ ለምክር ቤቱ የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡
የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ እንዲደረግ የቀረበለትን ጥያቄ የተቀበለው የአማራ ክልል ምክር ቤት በአዴፓ በዕጩነት የቀረቡለትን ዶክተር አምባቸው መኮንን ሲሳይን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሰይሟል፡፡
ዶክተር አምባቸው አምባቸው መኮንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሠረተ ልማት አማካሪ ሚኒስር ናቸው፡፡
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ‹‹ታላቁን የአማራ ሕዝብ ለመምራት ዕድል የሰጠኝን ፓርቲዬን አመሠግናለሁ፤ በስልጣን ዘመኔ በሰጠኋቸው ውሳኔዎች ያስከፋኋችሁ ካላችሁ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ወኔና ጉልበት ሆኖኝ የኖረውን የአማራ ሕዝብ አመሠግናለሁ፤ ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድርም መልካም የሥራ ዘመን እመኛለሁ›› ብለዋል በመሰናበቻ ንግግራቸው፡፡
ምንጭ፡- 29/06/2011(አብመድ)

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.