Breaking News
Home / Amharic / አማራንና አፄ ምኒልክን የተሳደበው ሃጫሉ ሁንዴሳ አምቦ ዩንቨርስቲ በስሙ ተሰየመለት::

አማራንና አፄ ምኒልክን የተሳደበው ሃጫሉ ሁንዴሳ አምቦ ዩንቨርስቲ በስሙ ተሰየመለት::

አማራንና አፄ ምኒልክን የተሳደበው ሃጫሉ ሁንዴሳ አምቦ ዩንቨርስቲ በስሙ ተሰየመለት::
በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከንቲባ ታከለ ኡማ ውሳኔ ለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ት/ቤት በስሙ እንደተሰየመለትና በመቀጠልም በሃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘውን አደባባይ በሃጫሉ ስም ለመሰየም መርሃ ግብር መያዙ ሰማን። ለአርቲስቱ የሚመጥነዉ ማስታወሻ ማስቀመጥ ተገቢ እንደሆ ስላመንኩ እሰየው ብለናል።
 
በተጨማሪም ሐውልት ሊያቆምለት መሆኑን ሰማን።
ነገር ግን
በነ አለምፀሃይ ወዳጆ አማካኝነት አዲስ አበባን የቆረቆረቻት የእቴጌ ጠሃይቱ መታሰብያ ሃውልት ለመስራት የተቀመጠን የመስራት ድንጋይ በቄሮ መንጋ ሲፈርስ ታከለ ኡማ መጀመሪያ የተፈቀደውን ፕሮጀክት ከኔ እውቅና ውጭ የተሰራ ስራ ነው በማለትና ሸምጥጦ በመካድ ፕሮጀክቱ እንዲቆም ማድረጉን አስታውሶኝ ሁኔታው አግራሞትን ፈጥሮብኛል።
ሌላው ከዚህ ጋር በተያያዘ
ሃገሩን በኢኮኖሚና በልማት ለማሳደግ የሙቀት መጠኑ ከ38-40 ዲግሪ ሳልሲየስ በሚደርስ ሃሩር በርሃ ላይ ለ7 አመታት እየተቃጠለ ሲሰራ የነበረው የልማት አርበኛ ኢንጂነር ስመኘው የግፍ ግድያና በመንግስታቸን የተሰጠው ምላሽ ትዝ አለኝና አንዳች ነገር ውስጤን ሰንጎ ያዘኝ።
የ53 ዓመት ጎልማሳ የኢንጂነር ስመኘው ስም በህዝብ እውቅና እያገኘ የመጣው የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ማኔጀር ሆኖ ሲሾም ይሁን እንጂ ስመኘው የግልግል ጊቤ አንድንና ሁለትን ግንባታዎችን በመገንባት በሃላፊነት የተወጣ መሪ መሃዲስ ነበር።
ኢንጂነሩ የጀመረውን ግድብ እውን ለማድረግ ትጋቱ ይገርመኝ ነበር። በግድቡላይ የነበረው መሻት የህዝብ ግንኙነት እስኪመስል ድረስ ሊጎበኙ ለሄዱ ሰዎች ስሜት ውስጥ ገብቶ ንግግር ሲያደርግ ምኞቱ ከፊቱ ይታይ ነበር።
እንዲህ አይነቱ ከራሱና ከቤተሰቡ ሂዎት የሃገሩን ያስቀደመው ስመ ጥር መሪ መሃዲስ በአክራሪ ኦነጋዊያን በጭካኔ ሲገድል እንኳንስ አደባባይና ት/ቤት ሊሰየምለት ለረጅም ጊዜ ከምቃብሩ ላይ ድንጋይ የሚስቀምጥለት አልነበረም። ጭካኔ ከተሞላበት አገዳደሉም በላይ የጠ/ሚንስትራችን “አንድ ኢንጂነር ስመኘው የሚባል ሰው ሞቶ ተገኝቷል” ብለው የተናገሩትን መስማት ቅስም ስባሪ ነበር።
ሃገራችን መቼ ይሆን በመርህ የምትመራው❓
 

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.