Breaking News
Home / News / ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ ሥራ ጀመረ ::

ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ ሥራ ጀመረ ::

ተቋርጦ የነበረው ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ መጀመሩን የትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተቋርጦ የነበረው የሀገር አቋራጭ፤ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ዛሬ መጀመሩን የትራንስፖርት ባለስልጣን ገለፀ።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመግታት ሲባል የሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ያስታወሰው ባለስልጣኑ፥ ከዛሬ ጀምሮ ግን የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ ስድስቱም መናኸሪያዎች አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን ገልጿል።

ስለሆነም የሀገር አቋራጭ፣ የአነስተኛና መለስተኛ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ትራንስፖርተሮች ተሸከርካሪዎቻቸው አገልግሎት ለሚሰጡት ህብረተሰብ አስፈላጊና ንጽህናውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበውቅባቸው ማሳሰቡን ከትራስንፖርት ሚኒቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደንብ መሰረትም የሀገር አቋራጭ፤ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከተሳፋሪ የመጫን አቅማቸው በ50 በመቶ ቀንሰው የሚጭኑ ይሆናል።

በተጨማሪም ማህበራት ሰራተኞች፣ ለአሽከርካሪዎች ፣ ለገንዘብ ተቀባዬች እና ለረዳቶች ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ ማስክ፣ እንዲሁም ሳኒታይዘር (አልኮል) ማቅረብ እንደሚገባም አስታውቋል።

የጫኝና አዉራጅ ማህበራት እና የስነስርዓት አስከባሪ አደረጃጀቶች ለጫኝና አውራጅ እና ለስነ-ሥርዓት አስከባሪዎች ጓንት፤ የአፍና አፍንጫ ማስክ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸውም ነው ባለስልጣኑ የገለፀው።

አሽከርካሪዎችም ተሸከርካሪዎቻቸውን ሥምሪት ከመውሰዳቸው በፊት ከመናሀሪያዉ አስተዳደር ጋር በመሆን የኬሚካል ርጭት ማካሄድ እንደሚገባም አብራርቷል።

በአጠቃላይ የኮረና ወረርሽን ለመከላከል ንጽህናውን የጠበቀ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት ትውልድን እና ሀገርን የማዳን ጥሪ መሆኑን በመግለፅ፤ ይህንን ያላሟላ ትራንስፖርተር ስምሪት ለመውሰድ የሚቸገር መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.