Breaking News
Home / Amharic / ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ!

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ!

ቅዳሜ ዕለት ባህር ዳር ውስጥ ተሞክሯል የተባለውን “መፈንቅለ መንግሥት” መርተዋል ተብለው ሰማቸው የተጠቀሰው የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋድየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ መገደላቸው ተዘገበ።

ብሔራዊው ቴሌቪዥን እንደገለጸው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባህር ዳር ዙሪያ በሚገኝ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን አሳውቋል።

• የሥራ ኃላፊነታቸውን “ከባድና የሚያስጨንቅ… ነው” ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ?

የኢቲቪ ዘገባ ጄነራሉ በምን ሁኔታ በጸጥታ ኃይሎች እንደተመቱ የገለጸው ነገር የለም። ዜናው እንዲሁ በጥቅል መታታቸውንና ህይወታቸው ማለፉን ብቻ ነው የገለጸው።

ስለብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ በጥቂቱ

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ተወለደው ያደጉት ወሎ ላስታ ውስጥ ነው። አሳምነው ወደ ትግል በመግባት የወቅቱን ኢህዴን በኋላ ብአዴን የተባለውን የአማራ ድርጅትን ከመቀላቀላቸው በፊት በደሴ ከተማ በሚገኘው የመምህራን ኮሌጅ ውስጥ መምህር ሆነው አገልግለዋል።

ወታደራዊው መንግሥት በአማጺያኑ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በትውልድ አካባቢያቸው አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ነበር።

• ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው

በማስከተልም ወደ መከላከያ ሠራዊቱ ገብተው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ነበር። ወደ አሜሪካ በመሄድ ወታደራዊ ትምህርት የተከታተሉት አሳምነው ከጦርነቱ በኋላ የጄኔራልነት ማዕረግ አግኝተው በሠራዊነቱ ውስጥ በኃላፊነት ሲያገለግሎ ቆይተዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የመከላከያ ሠራዊቱን ኮሌጅ በበላይነት በመምራትና በማስተማር እንዳገለገሉ ይነገርላቸዋል። ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው በ2001 ዓ.ም ከሌሎች ወታደራዊ መኮንኖች ጋር መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ በማሴር ታስረው ነበር።

ጄኔራሉ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ስለተባሉ ማዕረጋቸው ተገፎ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ለዘጠኝ ዓመታት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከእስር ተፈትተው ለአገራቸው የከፈሉት መስዋዕትነትን እውቅና በመስጠ ትማዕረጋቸው እንዲመለስና የሚያገኙት ጥቅም እንዲከበርላቸው አድርገዋል።

የአማራ ክልልም ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለአጭር ጊዜ በቆዩበት የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ሰጥቷቸው ነበር።

• በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደ አረፉ

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተሞከረውና የክልሉን ፕሬዝዳንትና የአገሪቱን ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹምንና የሌሎች ሁለት ከፍትኛ ባለስልጣናትን ህይወት ከቀጠፈው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጀርባ እንዳሉ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስታውቋል።

የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ኃላፊነቱን የተረከቡት አቶ ላቀ አያሌው ለክልሉ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ጄኔራሉንና ሌሎች የድርጊቱ ተሳታፊዎችን ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎች እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.