Breaking News
Home / Amharic / በደንብ ይነበብ – አብንን መርዳት የህልውናና ፣ የመዳኛ ጉዳይ ነው!

በደንብ ይነበብ – አብንን መርዳት የህልውናና ፣ የመዳኛ ጉዳይ ነው!

በደንብ ይነበብ

መሪያችን ወደ ቁምነገር የምንቀይርበት ሰዓት ላይ እንገኛለን ።ክርስቲያን ታደለ እርዳታ ያስፈልገናል ብሏል ። ይህን መስማት እጅጉን ያማል ። አብንን መርዳት የህልውና ፣ የመዳኛ ጉዳይ ነው ። 
******************************************
የሚያበሳጭ ነገር ነው። እንዴት ነው ነገሩ ጎበዝ????
በዚህ ጊዜ እንዲህ ያለ ነገር መስማት ያሳፍራል። ያሸማቅቃል።👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Christian Tadele Tsegaye
አማራ የጋራችን እንጂ የግላችን ሕዝብ ስላልሆነ፤ የኅልውና ትግሉም የጋራችን ሊሆን ይገባል! 
(ገብርዬ)
*****
በብዙ ምክንያት በአደባባይ የማንገልፃቸው ብዙ ነገሮች አሉ። የግድ ስለሆነ የኅልውናም ጉዳይ ነውና ለመላው አማራ እና የአማራ ወዳጆች የማቀርበው ጥሪ አለ። ትግላችንን በገንዘብ እና ቁሳቁስ አግዙን። ሕይወታችንን ለመስጠት ከዝግጁም በላይ ነን። እናንተ ደግሞ በእውቀት፣ በገንዘብና በቁሳቁስ አግዙን።

ከ130 በላይ ሕዝባዊ መድረኮች፣ ከ120 በላይ ቢሮዎች፣ የጥናት ሲምፖዚየም፣ የአማራጭ ፖለሲዎችና የአቋም ሰነዶች ዝግጅት፣ መደበኛ የስራ አስፈፃሚና ምክርቤት ስብሰባዎችና የታቀዱ ሥራዎች ማስፈፀሚያ፣…እነዚህን ሁሉ በአማራዊ ወኔ እንጂ በየትኛው አቅማችን ፈፀምናቸው? ለዚህ ሁሉ ምን ያህል የሰው ኃይል፣ ፋይናንስና ቁሳቁስ ኃብት ተጠቀምን? እውነቱን ለመናገር ፈጣሪ ብርታቱን ሰጥቶን፣ የሕዝባችን ሰቆቃ የእልህ ኃይል ሞልቶን፣ የደጋፊዎቻችን አለኝታነት አቅም ሆኖን፣ የሕይወት መስዕዋትነት ጭምር እየከፈሉ ለሕዝባችን ሌት ተቀን የሚታትሩ አባላቶቻችን ምሰሶ ሆነውን ቆመን እንጂ እስካሁን የመጣንበት መንገድ ለወግም አይመችም።

የኅልውና ትግላችን ወደ ጨነቀ‘ለታው ተሸጋግሯል። ቢያንስ ከፍተኛ አመራሮችን የሙሉ ጊዜ ታጋይ ማድረግ የግድ ይለናል። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰን የምንሰራበት፣ ሕዝባችንን የምናደራጅበት የራሳችን አንድም ተሽከርካሪ የለንም ብንል ማን ያምነናል?! አመራሮችና አባላት ለሕዝባችን ገንዘባችንን ብቻ ሳይሆን መላ እኛነታችንን ሰጥተናል። በእስካሁኑ ጉዞ የምንችለውን ብቻ ሳይሆን የማንችለውንም ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው። የአማራ ባለሀብቶች ከመሽኮርመም ወጥታችሁ የሕዝባችንን የኅልውና ትግል ማገዣ ጊዜያችሁ ነው። የመንግሥት ሰራተኞች፣ በግል ተቋማት የምትሰሩ ተቀጣሪዎችና በጉልበት ሥራም የተሰማራችሁ ወገኖች ያቅማችሁን ለኅልውና ትግሉ ማበርከት ይጠበቅባችኋል። አርሶአደሮቻችን በዓይነትም ቢሆን ትግሉን መደገፍ አለባቸው። በውጭ የምትኖሩ ወገኖች በቋሚነት ገንዘብ እያሰባሰባችሁ አብን የሚያደርገውን የኅልውና ትግል በባለቤትነት መያዝ ይጠበቅባችኋል። እያንዳንዱ አማራ አማራነቱን የመታደግ የታሪክና የትውልድ አደራም፥ግዴታም አለበት! ለቢሮ ኪራይ፣ ለአደረጃጀትና ፖለቲካ ሥራዎች፣ ለመጓጓዣ፣ መኪና፣ ወዘተ ወጪዎች ገንዘብ አስፈልጎናል። እርዱን! መኪና፣ ዴስክቶፖች፣ ፕሪንተሮች፣ ፎቶ ኮፒየሮች፣ ላፕቶፖች፣ ስቴሽነሪ፣ ፈርኒቸር፣ ካሜራዎች፣ ወዘተ በዓይነትም ቢሆን የሚለግሰን ከተገኘ እጅጉን ደስተኞች ነን።

የታላቁን የአማራ ሕዝብ ጉዳይ እየመራን የትም እንዳልሆነ ብንሆን የሚገመተው ሕዝባችን ነው። በዚህ ጉዳይ ከዚህ በላይ ባልናገር ደስ ይለኛል። የአማራ አክቲቪስቶችም ይህንን ጥሪያችንን በአካልም ሆነ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እንድታዳርሱ ይሁን። ለአብን የምታደርጉት ድጋፍ ሁሉ ለአማራ ሕዝብ ኅልውና የሚደረግ ኢንቨስትመንት ነው!

 

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.