Breaking News
Home / Amharic / ከአማራ ወጣቶች የተሰጠ መግለጫ!

ከአማራ ወጣቶች የተሰጠ መግለጫ!

በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት እና በአምባገነኑ ህወሃት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ጦርነት አምርቶ ጦርነቱ ከሰባት ወራት በላይ እንደቆየ ይታወቃል። በጦርነቱ ያልታጠቁ ንፁኀን ህዝቦችን ጨምሮ በርካታ ወገኖች ለአካል ጉዳትና ለሞት ሰለባ ሁነዋል፤ የአገር ሀብትና ንብረትም ወድሟል።እንደ አማራ ሕዝብ በዚህ ጦርነት ያገኘነው ትርፍ በህወሃት በተፈፀመ መንግስታዊ ወረራ ተወስደው የነበሩ ርስቶቻችንን በአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ እና ሚሊሻ ከፍተኛ መስዕዋትነት ማስመለሳችን ነው።
በ21/10/2013 ዓ/ም ከሰዓት ጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ተጠየቀ እና የመከላከያ ሰራዊት ቦታውን ለቆ ወጣ ፤ ህወሃት መቀሌን ተቆጣጠረ የሚሉ ዜናዎች ተሰምተዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደ አማራ ነገ ምን ሊመጣ እንደሚችል አርቆ ማየት፣ ዙሪያ ገባውን በተጠንቀቅ መጠበቅ እና በሁሉም መስክ አፀፋ ለመስጠት መዘጋጀት ያስፈልጋል። የአማራ አንቂዎች የጦርነቱ አሸናፊዎች ነን ከአላስፈላጊ ትንተናዎች እንቆጠብ።ከዚህ በፊት ከነበረው የባሰ ችግር ሊመጣ ይችላል። ስለዚህ ህዝባችን በአንድነት ቁሞ አካባቢውን በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ በያለንበት መሬት ላይ ስራ እንስራ።
መታወቅ ያለበት የማዕከላዊ መንግስት ከህወሃት ጋር ቢደራደርም ባይደራደርም እኛ አማራዎች ግን ርስቶቻችንን በማስመለስ ጦርነቱን አሸንፈናል። ከጦርነቱም አትርፈናል።
በጦርነቱ ያስመለስናቸውን ግዛቶችን ለመንጠቅ የሚሞክር ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴ ከተፈጠረ ተፈጥሯዊ ራስን የመጠበቅ መብታችንን ተጠቅመን የሚመጣውን ሀይል ሁሉ መመከት እንዳለብን ለመላው የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ እና የአማራ ሚሊሻ ማሳሰብ እንወዳለን።
#አንድ አማራ!

Check Also

ሰሎሞን ካሳ ማነው? Who is Solomon Kassa?

አንከር ሚዲያ እንደዘገበው .. ለማታውቁት ሰለሞን ካሳ ይባላል ., ወንጀለኛው የሆነው ይህ ሰው የህዝብ ድምፅ …

የአድዋ በአል በለንደን ከተማ በደማቅ ተከበረ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.