Breaking News
Home / Amharic / በእነ በለጠ ካሳ ላይ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ፤

በእነ በለጠ ካሳ ላይ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ፤

★★★
ፓሊስ ከሰኔ 15ቱ የአማራ ሕዝብ መሪዎች እና የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮነኖች ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል ለሁለት ጊዜ የ28 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው በእስር ላይ የሚገኙት፦

1. አቶ በለጠ ካሳ የአብን የፅህፈት ቤት ኃላፊ፣
2. አቶ አንተነህ ስለሺ የአብን የአዲስ አበባ የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ፣
3. አቶ ንጉሴ ይልቃል የአብን የየካ ክፋለ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ፣
4. ፍስኃ ገነቱ የአብን አባል
መስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር።

ፓሊስ የምርመራ ስራየን ስላልጨረስኩ ለ3ኛ ጊዜ ተጨማሪ 28 ቀን ይሰጠኝ ብሎ የጠየቀ ሲሆን የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ፓሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የሚጠይቅባቸው ምክንያቶች ተመሳሳይነት ያላቸውና ከአሁን ቀደም በተሰጠው ሁለት የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ውስጥ ከደንበኞቻቸው ጋር የሚያያዝ ተጨባጭ ማስረጃ አለማቅረቡንና ፓሊስ በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ እየጠየቀ ደንበኞቻቸውን የተፋጠነ ፍትህ እንዳያገኙ ማድረጉን በመጥቀስ የጠየቀው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሊፈቀድለት አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የፓሊስ የምርመራ መዝገብ ከቀጠሮው ቀን ቀድሞ እንዲቀርብ በማዘዝ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ የሚለው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለመስከረም 19 ቀን 2012 ዓ.ም 4:00 ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

Check Also

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

ከጎጃም አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ – ዘመነ ካሴ – Amhara FANO Gojjam

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.