Breaking News
Home / News / በአማራ ክልል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን 4.7 ሚሊዮን ብር አልቀበልም አለ።

በአማራ ክልል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን 4.7 ሚሊዮን ብር አልቀበልም አለ።

በአማራ ክልል ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠውን 4.7 ሚሊዮን ብር አልቀበልም አለ። በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያሰባስበው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ በሰጡት መግለጫ “ለአማራ ሕዝብ የገባው ቃል ከባንኩ ከምንጠብቀው አንፃር እና በአማራ ክልል ሕዝብ ካለው ስም አንፃር የሰጠው ድጋፍ አነስተኛ በመሆኑ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃል የገባውን ገንዘብ አይቀበልም” ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 100 ሚሊዮን ብር መለገሱን በትናንትናው ዕለት አስታውቆ ነበር። 90 ሺሕ ተፈናቃዮች የሚገኙበት የአማራ ክልል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጋፍ 4.7 ሚሊዮን ብር ደርሶታል። ባንኩ ለሶማሌ ክልል 35 ሚሊዮን ብር ፤ለኦሮሚያ ክልል 33.6 ሚሊዮን ብር ለደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል 18.3 ሚሊዮን ብር ሰጥቷል። (ቪዲዮ፦ አለምነው መኮንን::

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.