Breaking News
Home / Amharic / መኖሪያ ቤታቸው በኦሮሚያ ክልል መንግስት ያፈረሰባቸው የአማራ ተወላጆች ራሳቸውን አጠፉ!

መኖሪያ ቤታቸው በኦሮሚያ ክልል መንግስት ያፈረሰባቸው የአማራ ተወላጆች ራሳቸውን አጠፉ!

ሰበር ዜና!
 
 
 
 
መኖሪያ ቤታቸው በኦሮሚያ ክልል መንግስት የፈረሰባቸው ሰዎች እራሳቸውን አጠፉ!
 
የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ አከባቢዎች መኖሪያ ቤታቸው በኦሮሚያ ክልል መንግስት የፈረሰባቸው ሰዎች እራሳቸውን ማጥፋታቸውን የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።
በቅርቡ በተመሰረተው እና ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው በተባለው ሸገር ከተማ ስር በተካተቱ ስድስት ክፍላተ ከተሞች ህገ ወጥ ናቸው በሚል ማንነትን በለየ መልኩ የአማራ ተወላጆች መኖሪያ ቤት እየፈረሰ ይገኛል።
በሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ሱሉልታ እና ገላን የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ መኖሪያ ቤታቸው ፈርሶባቸው ጎዳና ላይ ወድቀዋል።
የክልሉ ልዩ ኃይል በሚያጅበው ግብረ ኃይል መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው እና መውደቂያ ያጡ ሰዎች ባደረባቸው የአዕምሮ ጭንቀት እራሳቸውን ማጥፋታቸውን ነው የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ያየረጋገጡት።
ተበድረው እና ያላቸውን ጥሪት አሟጠው የሰሩት መኖሪያ ቤት ሲፈርስ ተስፋ በመቁረጥ በገመድ በመታነቅ እና መርዝ በመጠጣት በሱሉልታ አከባቢ እስከ አሁን የታወቁ ሁለት ሰዎች እራሳቸውን ማጥፋታቸውን ነው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለአማራ ድምፅ የገለፁት።
ቤተሰቦቻቸውን የሚያስጠጉበት እና የሚያስጠልሉበት ያጡ በርካታ ሰዎች በእዕምሮ ጭንቀት እራሳቸውን ስተው ሆስፒታል መወሰዳቸውም ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ መኖሪያ ቤታቸው በመፍረሱ እና የሚጠለሉበት በማጣታቸው በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ቀርተዋል የተባለ ሲሆን በሴተኛ አዳሪነት የተሰማሩ ልጃገረዶችም መኖራቸው ተጠቁሟል።
የአማራ ድምፅ ያየነጋገራቸው በለገጣፎ ለገዳዲ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሌላኛው ተጎጂ፣ “አዲስ ያሰራሁት መኖሪያ ቤቴ ፈርሷል፣ ከባለቤቴ ጋር ለአመታት ጥረን ግረን ያፈራነው ሀብት ንብረት በአፍራሽ ግብረ ኃይሉ ወድሟል ስለዚህ ብቸኛ አማራጫችን እራስን ማጥፋት ሁኗል” ብለዋል።
ትናንት የተሻለ ህይወት እኖር ነበር ዛሬ ግን ከነቤተሰቦቼ መጠለያ አጥቼ እየተንከራተኩ ነው ያሉ ሲሆን በልመና ህይወት መሰማራታቸውን ጨምረው ገልፀዋል።
እየተካሄደ የሚገኘው የቤት ማፍረስ ዘመቻ አሁንም መቀጠሉ የተገለፀ ሲሆን ከኦሮሞ ተወላጆች ውጭ የሌሎች ብሔር ተወላጆች መኖሪያ ቤት እንዲፈርስ ምልክት እንደተደረገበት ነዋሪዎቹ ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት፣ እናቶች እና አዛውንቶች የሚጠለሉበት አጥተው ጎዳና ላይ የወደቁ ሲሆን አንድ አከባቢ ተሰባስበው እንዳይገኙ በፀጥታ ኃይሎች እንዲበተኑ እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል።
በግሬደር ማሽን በመታገዝ መኖሪያ ቤቶችን እያፈረሰ የሚገኘውን ግብረ ኃይል የሚያጅቡት የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች ቤታችንን አናስፈርስም ባሉ የአከባቢው ነዋሪዎች ላይ በከፈቱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአማራ ድምፅ መዘገቡ አይዘነጋም።
አማራ ድምፅ እንደዘገበው

Check Also

በአሜሪካን ሀገር የምትኖሩ የአማራ ማህበራትና የአማራ ልጆች የት ነው ያላችሁት?? Share!

ድሮን ሲያስተኩስ የነበረው ባንዳ በፋኖ ተያዘ ! እኔን ያየህ ተቀጣ !

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.