Breaking News
Home / Amharic / መሬት ላይ ያለውን ሀቅ በመደበቅ እና በማደባበስ መፍትሄ ማምጣት አይቻልም ።

መሬት ላይ ያለውን ሀቅ በመደበቅ እና በማደባበስ መፍትሄ ማምጣት አይቻልም ።

ትግራይ መገንጠሏን እያወጀች ኦሮሚያም በመንግስት ታግዛ አልፎም ኦነግ እና ኦፌኮ የሽግግር መንግስት እያወጁ መሐል ላይ አንድነት ባለ ጨፍላቂ ነህ እየተባለ ሰለባ የሆነው ያልነቃው አማራ አንተ ትበታተናለህ እንጂ ኢትዮጵያ አትበትንም የሚለው ሒሳብ መክሸፍን ተረድተናል ።
ይህ መሬት ላይ ያለውን ሀቅ በመደበቅ እና በማደባበስ መፍትሄ ማምጣት አይቻልም ።
የኢትዮጵያ የዘመናት ችግር ከሻቢያ ጀምሮ ህወሃት እና ኦነግ ጭምር ሀገር የመመስረት እና አማራን በመጥላት ላይ የተመሠረተ እንደሆነ እና ለዚህም እንዲመቻቸው የኢትዮጵያ ባለውለታ ጀግኖች መሪዎችን (ምንሊክ) የመሳሰሉት ላይ አዲስ ትርክት ለትውልዱ በመመገብ ነው ።
ይሄም ፍሬ አፍርቶ ከኤርትራ በመቀጠል ትግራይ አልፎም ኦሮሚያ ሀገር የመሆን ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል ።
ይህ ሁሉ ሲሆን አንድነታችን ልዩነታችን እያሉ በማመኘት የአስተዳደር ወሰን ናቸው እያለ ዝምታ ባበዛው የአማራ አፅመ እርስት በመውሰድ የራሳቸው ካርታ ይፋ አድርገው ጨርሰዋል ።
ይህ ሁሉ ሲሆን በስነ ልቦና የተጎዳው ብአዴንን ጨምሮ የአማራ ሙህራን አብዛኛው ከጣት ከማያልፉ ጥቂቶች በስተቀር የጠነከረ ጥረት አላደረጉም ።
አሁን አይኔን ጆሮዬን ጋረጃለሁ ያላለ ወይንም ከየዋህነት በታች የሆነ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም በግልፅ እያለቀ ነው ።
ይህ ታርጌት( ሰለባ )የሆነው የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን እያለ ያጣቸው ነገሮች እንዳሉ ሆነው ከዚህ በኋላ የራሱን ህብረተሰብ አልፎም ሰለ ኢትዮጵያ የሚከራከርበት የራሱ መሬት ያስፈልገዋል ። በደቡብ አማራ በሴራ ያጣናቸው ለወደፊት ብዙ ትግል የሚጠይቁ መሬቶች ከአዲስ አበባ አንስቶ እስከ ሻሸመኔ ናዝሬት እና ደብረዘይት ሞጆ አብላጫ የሸዋ መሬት አማራ እንደ ሀገር ከወዲሁ ተጠናክሮ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ጭምር ማስመለስ እንደሚችል ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ቢሆንም ዝም ከማለት በያቅጣጫቸው የሁሉንም ጥረት ይጠይቃሉ ።
ታዲያ አማራ ከሀቅ ጋር ስለሆነ የሌላውን የማይፈልግ የራሱንም ስንዝር እንደማይሰጥ እና በአሸናፊነት መወጣቱ የማይቀር ቢሆንም ከፊቱ የተደቀኑ ብዙ ፈተናዋች የአሉበት በሴራ ከበባ ውስጥ እንደመኖሩ በዚህ ታሪካዊ ጊዜ ወቅቱን የዋጀ ዝግጅት ማድረግ እና መስፈርታችንም አማራ እና አማራነት ሆኖ ጥቃቅን ልዩነቶቻችንን ታገስ ብለን ለትልቁ ለህልውና አደጋችን ቅድሚያ በመስጠት የሁላችንም አስተዋፆ ለማድረግ ወሳኝ ጊዜ ነው ሁሉም በእውቀቱ እና በድርሻው ተሳትፎውን በማጠናከር በተጠንቀቅ ተዘጋጅቶ መቆም አለበት።

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.