Breaking News
Home / Amharic / መረጃ ቲቪ ለኢትዮጵያ። share!

መረጃ ቲቪ ለኢትዮጵያ። share!

መረጃ ቲቪ በአገር ቤት ይሰራጫል፣ ዜጎች እየሰሙት ነው #ግርማካሳ

አንዳንድ ነገሮችን ግልጽ ላድርግ። መረጃ ቴሌቪዥን ላይ የአቅሜን የቻልኩትን እሰራለሁ። በፍቃደኝነት። ለምን ሜዲያው ለአገርና ለሕዝብ ትቅ አስተዋጾ እያደረገ ነው ብዬ ስለማምን።

መረጃ ቲቪ ሜዲያው አለ፣ እንደገና የሳተላይት ቻናሉ አሉ። የሳተላይት ቻናሉ መረጃ ለብቻው ከመጠቀም ሌሎች ሜዲያዎች እንዲጠቀሙበት በማድረግ የተለያዩ ፕሮግራሞች ለሕዝብ በአየር እንዲቀርቡ እያደረገ ነው።

– በአቶ አበባ በላው የሚዘጋጀው አዲስ ድምድ
– የቀድሞ አስራት ጋዜጠኞች የሚያዘጋጁት መለከት ሜዲያ
– ሚኒሊክ ቴሌቪዥን
– ኢትዮ360
– ራሱ መረጃ ቲቪ
– የነጭ ነጩን የዘመድኩን ዝግጅት

ያሉ ፕሮግራሞች ያዘጋጃሉ። ይህ ቁትር ወደፊትም ሊጨምር ይችላል።

እነዚህ ሜዲያዎች ሁሉም የራሳቸው ቦርድ፣ ኤዲቶሪያል ፖሊሲዎች አሏቸው። አንዱ በሌላው ጣልቃ አይገባም ። አንዱ የሚያስተላልፈውን ሌላው ላይስማማ ይችላል። ቢያንስ ግን መረጃ ቲቪ ሳተላይት በርካታ አማራጮችን ለሕዝብ እያቀረበ ነው።

አንድ ሜዲያ የራሱ ሳተላይት ይኑረው ከተባለ ብዙ ነው የሚያስወጣው። በዚህ መልኩ ሜዲያዎች የአየ ሰ ዓት ሼር ሲያደርጉ የበለጠ ይጠቀማሉ።

አንዳንዶቻችን አንዱ ሜዲያ ላይ ችግር ሊኖረን ይችላል። ያ ማለት ግን ሁሉም ጋር ችግር ይኖረናል ማለት አይደለም። መረጃ ቲቪን እንደ ቢፌ ቁጠሩት። የተለያየ ምግብ አለ፣ እዚያ ውስጥ የማንፈለገው ምግብ ካለ እርሱ ትተን ሌላውን እንደምንመገበው፣ በመረጃ የሚተላለፉት ሜዲያዎች አንድይ ካልተመቸን ሌሎች ይኖራሉ። በአንዱ ምክንያት ሁሉን እንደ አንድ አድርገን አንውሰድ።

Mereja TV Satelite Broadcast

Eutel Sat 8 West B
Frequency: 11.636 Vertical
SR: 27.500
FEC: 5/6

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.