Breaking News
Home / Amharic / ለአየር ትኬት በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ 16 ሚሊዬን ብር ወጭ ተደርጓል።

ለአየር ትኬት በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ 16 ሚሊዬን ብር ወጭ ተደርጓል።

ያሳዝናል በርቀት የተማሩ ሰዎች በርቀት እያስተዳደሩ ነው። የብአዴን ባለስልጣናት ክልሉን አዲስ አበባ ተቀምጠው በርቀት ለመምራት እየሞከሩ ነው። ከሀምሌ 01/2011 ዓም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር በአውሮፕላን እየተመላለሱ በደሀ ህዝብ ገንዘብ እየቀለዱ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ። ለአየር ትኬት በሰባት ወራት ውስጥ ብቻ 16 ሚሊዬን ብር ወጭ ተደርጓል። አዲስ አበባና ባህርዳር በተመሳሳይ ጊዜ ለእነዚሁ ባለስልጣናት 31 ሚሊዬን ብር የቤት ኪራይ ከአማራ ህዝብ ኪስ ወጥቷል። በአጠቃላይ ድምር 47 ሚሊዬን ብር ያለ አግባብ ለተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ ወጭ መደረጉን ሰምተናል። ባህርዳር የትኛውም ባለጉዳይ ወደ መንግስት ቢሮ ሂዶ ማንንም አያገኝም። ባህርዳር ናቸው ሲባል አዲስ አበባ አዲስ አበባ ናቸው ሲባል ባህርዳር እያሉ ምንም አይነት የመንግስትና የህዝብ ስራ እየሰሩ አይደለም። በቅርብ ቀንም ስለግለሰቦች ዝርዝር መረጃ ለማውጣት እሞክራለሁ።

የብአዴን ባለስልጣናት ከሰኔ 15 በኋላ በመሀከላቸው መተማመን የለም፤ ጠፍቷልም። ግማሹ ለአብይ አህመድ ብናድር ይሻላል በማለት ጅራታቸውን ሲቆሉ የሚታዩ አሉ የተወሰኑት ደግሞ ግራ ገብቷቸው ቁመዋል።

ልብ በሉ በ2011 ዓም በተጠና ጥናት መሰረት ክልል ተብሎ በሚጠራው ውስጥ ከሚገኝ ት/ት ቤቶች ውስጥ 84% ከደረጃ በታች መሆናቸው ተረጋግጧል። የአማራ ህዝብ በሁሉም መሰረተ ልማት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነው ። በክልሉ 8 ጤና ኬላዎች ብቻ መስፈርቱን አሟልተው አገልግሎት ይሰጣሉ። ህዝቡ በድህነትና በኋላ ቀርነት ይማቅቃል። ወጣቱም የማንነት ጥቃትና ስራ አጥነት አንገቱን አስደፍቶት ይታያል።

የአማራ ህዝብ በርቀት የሚያስተዳድሩት ህዝብ ነው ወይ?
ይኸነው የሸበሉ::

 

Check Also

AMHARA FANO in London at Ethiopian Embassy

የዲያስፓራ መንገደኞች የሚያጋጥማቸው መከራ!

በቦሌ አየር ማረፊያ በፍተሻ እና ጥበቃ አካላት ተጓዦች ላይ የሚፈፀም ውንብድና እና ዝርፊያ! ድርጊቱ የተፈፀመው …

One comment

  1. Girma Andualem Mitku

    እይታው ጥሩና የህዝባችን ሀብትና ንብረት እንዴት እየተበዘበረ እንደሆነ ያሣያል። መሠል መረጃዎች በወቅቱ ማግኘት እንፈልጋለን።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.